የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኢሃዴግ ፅህፈት ቤትና ህግና ፍትህ ቢሮ በክፍለከተማው ህገ ወጥ መጅሊስ አባላት ላይ ስለላ ማካሄድ ጀመሩ፡፡

በመጪው ረመዳን የሙስሊሙ ተቃውሞ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይችላል ፣ በዚህም ሳቢያ የክፍለ ከተማው መጅሊስ አባላት በጾም ወንጀል ለመስራት ሃራም ነው በሚል ፈሊጥ የመጅሊሱ አባላት ላይተባበሩን ይችላሉ በሚል ስጋት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኢሃዴግ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ አበባ እሸቴ እና የክፍለከተማው ህግ እና ፍትህ ቢሮ ሃላፊው ባደረጉት ውይይት ….“ በመጪው የሙስሊሞች ፆም ከባድ ተቃውሞዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እንደ ክፍለከተማችን ተጨባጭ ሁኔታ የክፍለ ከተማችን መጅሊሶችን ብቻ አምነን ቁጭ ማለት የለብንም ፡፡ ዞሮ ዞሮ እነሱም ሙስሊሞች ስለሆኑ ለወገኖቻቸው በማድላት መረጃዎችን ከመሸሸግ ጀምሮ መንግስት በሙስሊሙ ላይ እየተገበረ ያለውን ፖሊሲ ለማስፈፀም ዳተኛ ሊሆኑ ስለሚችሉ ከወዲሁ እነሱን የሚከታተል አንድ ቡድን ማቋቋም አለብን “ እንዳሉ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡

እነዚህ በኢሃዴግ የሚቋቋሙት የስለላ ቡድን አባላት የመጅሊሱ አባላት በግልም ሆነ በስብሰባ ወቅት የሚያወሩትን ወደ መንግስት የሚያስተላልፉ ሲሆኑ መንግስት ወደ መጅሊሱ የሚያወርደውን መመሪያም ያለምንም ተቃውሞ እንዲያስፈፅሙ ለማስፈራራትም ጭምር እንደሆነ ታውቋል ፡፡

በተጨማሪም ከፌዴራሉ መጅሊስ ጀምሮ እስከ ወረዳ መጅሊስ ድረስ የመጅሊሶቹን የፅሁፍ ስራ የሚያከናውኑ ሙስሊም ያልሆኑና የኢሃዴግ አባላት እንዲሆኑ በኢሃዴግ ፓርቲ ፅህፈት ቤት በተወሰነው መሰረት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህግና ፍትህ ቢሮ ለክፍለከተማው መጅሊስ የኮምፒዩተር ፅሁፍ የሚፅፉ እና የመጅሊሱን ስራ ለመሰለል እዲያመቸቸው ሙስሊም ያልሆኑ የኢሃዴግ ካድሬ አባላትን ለማስገባት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ታውቋል፡፡

ይህ መረጃ የደረሳቸውና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የክፍከተማው መጅሊስ አንድ አመራር ለፍትህ ሬዲዮ እንደገለፁት “ የነወይዘሮ አበባ እሸቴ ድርጊት አሳፋሪ ነው፡፡ ለመሆኑ እራሳቸው አስመርጠውን ካበቁ በኋላ ዞሮ ዞሮ እነሱም ሙስሊም ናቸው ሲሉ ምን ማለታቸው ነው ? እኔ በበኩሌ በታላቁ ረመዳን ወቅት ሙስሊሙን ኡማ አውፍ በሉኝ ብዬ ፊቴን ወደ ኢባዳ እንጂ በታላቁ ወር ከመንግስት ወግኜ ከባድ ወንጀል አልሸከምም፡፡ ከፊት ለፊቴ ሞት አለና ” ብለዋል፡፡

አመራ ሩ አያይዘው “ ይህ መረጃ የደረሳቸው በክፍለከተማው ስር ያሉ የየወረዳ መጅሊስ አባላት ጨምሮ ሌሎች የህገ ወጡ መጅሊስ አመራሮች እንዴት አልታመንም በሚል ግራ የመጋባትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እንደታየባቸው የታወቀ ሲሆን፡ ከአላህም ሳንሆን ፣ መንግስትም ካላመነን እንዴት ነው የምንኖረው እያሉ እያጉረመረሙ እንደሆነ የውስጥ ምንጮች ለሬዲዮ ፍትህ ገልፀዋል፡፡

ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!!

አላሁ አክበር!!!

Posted on June 25, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC and tagged , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: