የግብፅ ጦር ፕሬዚዳንት ሙርሲ ለተቃዋሚዎች ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጡ 48 ሰዓታት ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብፅ  ጦር በአገሪቱ  ለተከሰተው ቀውስና  ለተቃዋሚዎች ጥያቄ ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ምላሽ እንዲሰጡ 48 ሰዓት  ሰጠ…. ጦሩ የፕሬዚዳንቱ  መንግስት አሁን ለተፈጠረው  ቀውስ  ፈጥኖ ምላሽ  መስጠት ካልቻለ ለሰላም ሲል የራሱን  ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ  እንደሚተገብር አስታውቋል ።

 

ይህ  የጦሩ መግለጫ  የወጣው  ተቃዋሚዎቹ  ከሰዓት በኋላ  በካይሮ  የሚገኘውን የፕሬዚዳንት ሙርሲ ፓርቲ የሆነውን ሙስሊም ወንድማማቾች ዋና መስሪያ ቤት  ከወረሩ በኋላ ነው ።

የፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት በእሳት የተቀጣጠለ ሲሆን ፥  በውስጡ  የሚገኙ  ንብረቶችም ተዘርፈዋል ።

በዋና ፅህፈት ቤቱ  አከባቢ  በነበረው  ግጭትም  ስምንት  ያህል  ሰዎች ተገድለዋል ።

 

ሚኒስትሮች ስልጣናቸውን  እየለቀቁ ነው

በፕሬዚዳንቱ ላይ  የተቀሰቀሰው  ተቃውሞ  በመላው  የግብፅ  ከተሞች የተቀጣጠለ ሲሆን ፥ እስካሁንም  አምስት ሚኒስትሮች ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል ።

የቱሪዝም ፣የውሃ ፣ የአከባቢ ፣  የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂ እንዲሁም  የህግና  ፓርላማ  ጉዳዮች ሚኒስትሮች የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ  ሚኒስትር ሂሻም ቃንዲል  አቅርበዋል ።

የግብፅ  የአገር  ውስጥ  ሚኒስቴር  እንዳስታወቀው በትናንቱ  የተቃውሞ ሰልፍ ላይ  ብቻ  ከ14 እስከ 17 ሚሊዮን  የሚጠጉ  ሰዎች  ለተቃውሞ  አደባባይ ወጥተዋል ።

በአንፃሩም  ትናንት  ሙርሲን ደግፈው አደባባይ  የወጡ  ሰዎች ነበሩ ።

በሁለቱ  ጎራ  በተቀሰቀሰም  ግጭት እስካሁን 14  ሰው   መገደሉንና  በ100  የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው  ተነግሯል ።

ተቃዋሚዎቹ  ፕሬዚዳንት  ሙርሲ እስከ  ነገ ስልጣን  እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ  ሰጥተዋል ።

ይህንን  ማድረግ ከተሳናቸው  ግን  በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን  እንደሚቀጥሉ  ነው የገለፁት ።

 

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisements

Posted on July 1, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC and tagged , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: