“ፊርማችን ለራሳችን!”

994766_669621469720984_194746518_n

“ፊርማችን ለራሳችን!”

የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ እንዲሻር አንድነት ፓርቲ ፊርማ እያሰባሰበ ይገኛል፡፡ እኔም ይሄንን ፊርማ ድብን አድርጌ ፈርሜያለሁ፡፡ ለመሆኑ ለምን ፈረምኩ… ምንያቱም፤ በፀረ ሽብር አዋጅ ስም በርካታ ንፁሃን ኢትዮጵያውን ታስረው መከራቸውን እያዩ እንደሆነ ስለማውቅ…

ምክንያቱም፤  እኔ ራሴ ወይም የልብ ወዳጄ ወይም ዛሬ ወይም ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ይህ የፀረ ሽብር አዋጅ እስካለ ድረስ እንደማንከሰስበት ምንም ዋስትና ስለሌለኝ፡፡

ምክንያቱም፤

አዋጁ በሰዎች ሰው መሆን ላይ የተመዘዘ ሰይፍ መስሎ ስለሚታየኝ ነው፡፡

እንግዲያስ የሰው ልጅ የወደደውን ካላመሰገን፣ የጠላውን ካልነቀፈ፣ ከመሰለው ጋር አብሮ ሆኖ ያልመሰለውን በነፃነት “ወግድልኝ” ማለት ከተከለከለ ሰው መሆኑ እንደተከለከለ ያክል አይደለምን…!

በፀረ ሽብር ህጉ መንግስት የተጣላቸውን ሰዎች በሙሉ እኛም አብረን ካላኮረፍን እንደ ሽብርተኛ እንቆጠራለን፡፡ በፀረ ሽብር ህጉ መንግስት የተጣላቸውን ሰዎች የፈለገ ቀልባችን ቢወዳቸው ሌላው ቀርቶ ማመስገን እና “እሰይ የኔ አንበሳ” ብሎ ማሞካሸት አይፈቀድልንም፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የፀረ ሽብር ህጉ ትኩር ብለን ካየነው፤ መንግስትን እና ቤተዘመዶቹን መቃወም ቀርቶ “ኤጭ አሁንስ በዛ…” ማለት ራሱ ያሰፈራል…!  ታዲያ ይህ ሰው መሆንን ከመከልከል ምን ያንሳል…!

እንደ እውነቱ ከሆነ መንግስታችን ያለ አዋጅ እና ያለ ህግም ያሻውን ያደርግ ዘንድ ችሏል፡፡ እንደ ምሳሌ፤

“የአይኑ ቀለም ካስጠላን ከሀገር ልናባርር እንችላለን”

“አንድ ሰው ኦነግ ሆኖ ከተገኘ ብቻ ወንጀል ሰርቷል ማለት ነው”

የሚሉት የእኒያኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ታሪካዊ ንግግሮች፤ በሞቅታ ካልሆነ በስተቀር በምን ህጋዊ መነሾ እንደተባሉ የሚያውቁት ራሳቸው ብቻ ናቸው፡፡

ቢሆንም… እንዲሉ ሃምሳ አለቃ ገብሩ… ቢሆንም፤ ህገወጥ ዱላ በህጋዊ ከለላ ከሚደረግ እንደተለመደው በሞቅታ ቢደረግ ይሻላል፡፡

ስለዚህ አሸባሪው የፀረ ሽብር ህግ እንዲሰረዝ እኔ ፈርሜያለሁ፡፡ ወዳጄ ልቤ… እርስዎም ዛሬውኑ ይፈርሙ! በዚች ማስፈንጠሪያ http://www.thepetitionsite.com/174/997/377/millions-of-voice-for-freedom-/?cid=FB_TAF  ተስፈንጥረው ይፈርሙ፡፡ ይህ ነገር ማስታወቂያ አይደለም፡፡ ምክር ነው እንጂ… ማስታወቂያ ቢሆን ኖሮ ግን…

“ፊርማችን ለራሳችን!”

ብለን እንዘጋው ነበር፡፡

Advertisements

Posted on July 3, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: