መንግስት የረመዷን ተቃውሞዎች ስጋት ውስጥ ከተውታል! (ድምፃችን ይሰማ)

ለነገው የአውፍ መባባያ ስነ ስርአት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡  የረመዳንን መቃረብ ተከትሎ ኢባዳችንን ለማጠናከርና በአዲስ የተቃውሞ መንፈስ ለመጓዝ በተነደፈው መርሐግብር በተገቢው መልኩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆናቸው ታወቀ… በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚደረጉ ተቃውሞዎችን በረመዳን በአንድ እርከን በማሳደግ የሚደረጉትን ጥረቶች ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የተሳታፊዎችም ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡ ረመዳን ከመግባቱ በፊት ነገ በሚደረገው አገር አቀፍ የአውፍ መባባያ ዝግጅት የአገሪቱ ሙስሊሞች በአጠቃላይ በአዲስ አበባ በአንዋር መስጂድ በክልሎች ደግሞ በተለመዱ የተቃውሞ ማስኬጃ መስጊዶች በመገኘት እርስ በእርስ የተቀያየሙ ካሉ ቅሬታቸውን አውርደው እርስ በእርስ ይቅር በመባባልና በአንድነት መንፈስ ጾሙ ይጀምራሉ፡፡ ለዚህም ጥሪ ተደርጎ የቅስቀሳ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡Ethiopian Musilms

በክልልሎችና በአዲስ አበባ የሚደረጉ የረመዳን ዝግጅቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተከትሎ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ በመግባቱ በሁሉም ክልሎች ስብሰባ መጥራቱን የቀጠለ ሲሆን ስብሰባዎቹም በማስፈራሪያ የታጀቡ ሆነዋል፡፡ ተቃውሞ ተባብሶ ይቀጥልባቸዋል ተብለው በሚታሰቡ አካባቢዎች በዋነኝነት እየተጠሩ ባሉት የማስፈራሪያ ስብሰባዎች በሰብሳቢነት የሚገኙት የኢሕአዴግ የየአካባቢው ተወካዮችና የመንግስታዊው መጅሊስ ተወካዮች ሲሆኑ በረመዳን ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይደረግና በመስጊዶች ከሰላት ውጪ መቆየት እንደማይችልም በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የስብሰባ ታሳታፊ ሙስሊሞች ግን ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል፡፡ ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› ለምን ትላላችሁ ብለው ሰብሳቢዎቹ ጥያቄ የሚያቀርቡበት ይኸው የማስፈራሪያ ስብሰባ ብዙዎቹ ባለመስማማትና በሙስሊሙ እንቢተኝነት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

አላሁ አክበር!

Advertisements

Posted on July 4, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC and tagged , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: