ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከተመረጡ ከ8 ወር በኃላ በዛ ያሉ የአዲስ ሚኒስትሮች ሹመት አጸደቊ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት የሰየሟቸዉን የአዳዲስ ሚኒስትሮች ሹመት ዛሬ ምክር ቤት አጸደቀ። በአዲሱ ሹመት መሠረትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ሚኒስትሮች ተሹመዋል…

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በዚህ አዲስ በተፈጠረዉ የሥራ መስክ ተሿሚዎቹ የካበተ ልምዳቸዉን ተጠቅመዉ መንግስትንም አገርንም የበለጠ ያገለግላሉ ተብሎ እንደሚታመን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን እና የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ ሁለቱም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር አማካሪ ሚኒትሮች ሆነዋል። አቶ ጌታቸዉ ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የባለስልጣናቱ ሥራ በዓላማዉ ብቻ ነዉ የሚመሳለሰለዉ ይላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

አንዳንድ ዘገባዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ካቢኔ አወቃቀር ቀጣይ ሹም ሽሮች እንደሚጠበቁ ያመለክታሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በበኩላቸዉ የተወሰኑ የፌደራል መንግስት የስልጣን ቦታዎች ብቻ ሊሞሉ እንደሚችሉ በማመልከት እንዳስፈላጊነቱ የሚሾም ካለም ይሾማል የሚሻርም ካለ እንዲሁ ነዉ ባይናቸዉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ከያዙ ከስምንት ወራት በላይ ተቆጥረዋል። ካቢኔያቸዉን ያዋቅራሉ እየተባለ ቢጠበቁም የተወሰኑ ሚኒስትሮችን ከመሾምና ከመሻር በስተቀር የአሁኑ ዓይነት በርካታ ሹመት አልሰጡም። የአሁኑ ሹም ሽር አለመዘግየቱን የገለጹት አቶ ጌታቸዉ ጊዜዉ የሚወሰነዉ ሽግሽጉ በሚፈለግበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።

በዚሁ መሠረትም በአቶ በረከት ቦታ አቶ ሬድዋን ሁሴን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትርነቱን ተረክበዋል፤ በአቶ ኩማ ደመቅሳ ምትክ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሚሆኑት ደግሞ በአዲስ አበባዉ ምክር ቤት በፊታችን የሳምንት መጨረሻ እንደሚመረጡ አቶ ጌታቸዉ ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

ሊንኩን በመንካት ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ

Advertisements

Posted on July 5, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: