ፕሬዚዳንት ሆኖ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሊመረጥ እንደሚችል ተጠቆመ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም   ኢሳት ዜና :-ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መራሹ ራዲዮ ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው…… ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ  ፋና ዘገባ በድንገት የሆነ ሳይሆን ታቅዶበት የተደረገእንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠል፡፡

 በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኙት መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ከአንድ ወር በኋላ የሚያጠናቅቁ ሲሆን በመስከረም ወር 2006 መጨረሻ አዲስ ፕሬዚዳንት በፓርላማው አብላጫ ወንበር ያለው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ዕጩ አቅርቦ ያስመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በፓርላማ የግል ተመራጭ የሆኑት የጥርስ ሐኪም ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ሰፊ ግምት ተሰጥቷቸው የቆዩ ሲሆን እሳቸውም ለኢህአዴግ ያላቸውን ታማኝነት በየአጋጣሚው ሲያሳዩና ሲገልጹ መክረማቸው የሚታወስ ነው፡፡
ኃይሌ ሰሞኑን ፕሬዚዳንት እንደሚሆን መግለጫ የሰጠው ምናልባት ከኢህአዴግ ታጭቶና እሱም ዕጩነቱን ተቀብሎ ሊሆን እንደሚችልና ይህም ወሬውን አስቀድሞ ሕዝብ ውስጥ በማስገባት የልብ ትርታውን የማዳመጥ ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ጠንካራ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
Advertisements

Posted on July 12, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: