ሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰለፍ ያወጣዋል

ባለፈው ጊዜ አዲስ አበባ በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይም ለገዢው ግንባር ኢህአዴግ ተነግሮታል… የምጠራጠረው መስማቱን ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ሟች ጠቅላ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲናገሩ እንደሰማነው አንዲት እንስሳ አለች ትልልቅ አይን አላት ግን አታይም ትልልቅ ጆሮ አላት ግን በቅጡ አትሰማም ብለውን ነበር፡፡

1069387_203643919793903_873502461_n

ሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰለፍ ያወጣዋል

ይቺን የሰማቻቸው ጊዜ የአብዬን ወደ እምዬ ብላቸው ነበር አሉ… እስንስሳዋን ብዙዎቻችን እናውቃታለን… ለደህንነቷ ስንል ስሟን እንዝለለው…

ኢህአዴግዬ ትልልቅ መስሚያ ጆሮዎች ትልልቅ መመልከቻ ኤኖች አሏት ብዙ ጊዜ ግን በቅጡ ስታይ በቅጡ ስትሰማ አላየናትም፡፡ (የኔ እናት… እግዜር ቀላሉን ያደርግልሽ ብዬ ተቆርቋሪነቴን እገልፃለሁ)

ለማንኛውም እንዲህ የመስማት እና የማየት ችግር ያላለበት ሰው እንዲሰማን እና እንዲያየን ደመቅ ብሎ መታየት እና ጮክ ብሎ መጮህ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡

ትላንት በደሴ እና በጎንደር ህዝቡ ደምቆ ታይቷል ጮክ ብሎም ተናግሯል፡፡ አሁንም ኢህአዴግዬ መስማቷን አንጃ… ስለዚህ ዳግም ድምፃችንን ከፍ ማድረግ አለብን ማለት ነው፡፡

አንድነቶች እንደነገሩን በቀጣይም፤ በሃያ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰልፎች ይደረጋሉ፡፡

የሀገሬ ሰው፤ ሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰልፍ ያወጣዋል! ኢህአዴግ እስክትሰማን ድረስ ደጋግመን የሆዳችንን ልንነግራት ይገባል ያለ ይመስላል፡፡

ኢህአዴግ ሆይ ስሚ…!

Advertisements

Posted on July 15, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: