የአንድ ኪሎ ቲማቲም ዋጋ 25 ብር ደረሰ

በአትክልትና ፍራፍሬ አምራችነታቸው በሚታወቁት የምሥራቅ ሸዋ ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተው የቲማቲም እርሻ ውድመት ሳቢያ የቲማቲም ዋጋ ማሻቀቡን ቀጥሏል….

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የአንsድ ኪሎ ግራም ቲማቲም ዋጋ 25 ብር የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላም ዋጋው እየጨመረ ይሄዳል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በ25 ብር እየተሸጠ ያለውም ቢሆን ለቲማቲም እርሻ ውድመት ምክንያት በሆነው ቱታ አብሱሉታ በተባለው ትል የተወጋ ቲማቲም ነው፡፡

 በመቂ አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮች እንደሚገልጹት፣ ቱታ አብሱሉታ የሚባለው ትል ባይከሰት በአሁኑ ወቅት የአንድ ኪሎ ቲማቲም የችርቻሮ ዋጋ ከአምስት ብር አይበልጥም ነበር፡፡ ቱታ አብሱሉታ ከመስፋፋቱ በፊት በሚያዝያ 2005 ዓ.ም. አማካይ የአንድ ኪሎ ቲማቲም ዋጋ ስድስት ብር ነበር፡፡ ወዲያው ወደ 14 ብር ከዚያም ዋጋው እየጨመረ 25 ብር ደርሷል፡፡ ለአዲስ አበባ ገበያ ቲማቲም በማቅረብ ከሚታወቁት እንደመቂ ካሉ አካባቢዎች የሚገባው የቲማቲም ምርት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአውዳሚው ትል የተወጋ ነው፡፡

ከአካባቢው የቲማቲም አምራቾች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ተመሳሳይ የነበረው አብዛኛው የቲማቲም ምርት የጠፋ ቢሆንም በተወሰኑ ማሳዎች ላይ ያለና በቱታ አብሱሉታ የተወጋው ቲማቲም በከፍተኛ ዋጋ እየተሰበሰበ ለገበያ እየቀረበ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችን ለኪሳራ የዳረገው የቱታ አብሱሉታ ትል ማጥፊያ መድኃኒት ባለመገኘቱ፣ በትሉ የተወጋውና አሁንም ለገበያ እየቀረበ ያለው ቲማቲም ተለቅሞ ካለቀ በኋላ አዲስ ምርት ስለማይኖር ዋጋው ከዚህም በላይ ይሆናል፡፡

መድኃኒት ያልተገኘለት የቱታ አብሱሉታ መስፋፋት ሊገታ ባለመቻሉ፣ አርሶ አደሮች በአጠቃላይ ቲማቲም ከመትከል ተቆጥበዋል፡፡

ከምሥራቅ ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች ውጭ ከሌላ ቦታ የሚመረት ምርት ለገበያ የማይቀርብ ከሆነም ችግሩ የከፋ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ትሉን ሊያጠፋ የሚችል መፍትሔ በመንግሥት ደረጃ መታሰብ እንዳለበትም እኒሁ ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ግን ትሉን ለማጥፋት ፍቱን መፍትሔ ነው ከተባለው ባዮሎጂካል መፍትሔ ሌላ ትሉን የሚያጠፋ መድኃኒት አለን የሚሉ ባለሙያዎች በአካባቢው የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ ነው፡፡

Advertisements

Posted on July 15, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: