በቂልንጦ እስርቤት የእሰረኞች ደም በድብደባ እንደጎርፍ መፍሰሱን የአይን እማኞች ተናገሩ

ኢሳት ዜና :- አርብ ፣ ሀምሌ 6 2005 ዓም በእነ አቶ ተሻለ ኮርኔ መዝገብ : የተከሰሱ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ፍርድ ቤት የሚወስዳቸው ፖሊስ ያጣሉ። በቅጽል ስሙ ሻእቢያ እየተባለ የሚጠራውን የእስር ቤቱን ሀላፊ ሲጠይቁት ቀጠሮአቸው ለ4 ወር መራዘሙን ይነግራቸዋል..

እስረኞቹም ” ከ2 አመታት በላይ የላፍትህ ታስረን በመጨረሻ ብይን በሚሰጥበት ወቅት ለ4 ወራት ተራዝሟል መባሉ ተገቢ አይደለም”  በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የሚላክ ፊርማ ማሰባሰብ  ሲጀምሩ ማረሚያ ቤቱ መረጃው ይደርሰውና 69ኙ እሰረኞች በ20 ተከፋፍለው ወደ ተለያዩ የማረሚያ ክፍሎች ወይም ዞኖች እንዲበተኑ ይደረጋል።

አርብ ጧት ሌሎች እስረኞች ወደ ውጭ እንዳይወጡ ከተደረገ በሁዋላ ፣ ሻእቢያ በሚባለው የእስር ቤቱ ሀላፊና ከውጭ በመጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲደበደቡ ይደረጋል። አስተባባሪ ናቸው የተባሉትን 18 እስረኞችን እንደገና በማውጣት በሰደፍና እና በዱላ ከቀጠቀጡዋቸው በሁዋላ 8ቱ ራሳቸውን ሲስቱ ወደ እስር ቤቱ የህክምና ክፍል ይወሰዳሉ።  ችግሩ ከአቅሙ በላይ መሆኑን የእስር ቤቱ የህክም ክፍል በመግለጹ፣ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

የአይን እማኞች ለኢሳት እንደገለጹት እስረኞቹ የተደበደቡበት ቦታ በደም በመጨቅየቱ አርብ እለት በውሀ ሲታጠብ አርፍዷል።

ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል በላይ ኮርሜ ፣ ተፈሪ ቀብኔሳ እና መንግስቱ ግርማ የሚባሉ ይገኙበታል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአህኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና እሰረኞቹ መደብደባቸውንና የተወሰኑት ሆስፒታል መግባታቸውን መረጃው እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

ዶ/ር መረራ “ድርጊቱን በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተን መልስ በማጣታችን መንግስት ሆን ብሎ በፖሊሲ ደረጃ ይዞ የሚያካሄድ ይመስላል” ሲል አክለዋል።

የእስር ቤቱን ሀላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

Advertisements

Posted on July 16, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo and tagged . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: