በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ የ10 አመቷን ሶርያዊ ሕጻን ገደለች፡፡

*ሰራተኛዋ በመንፈስ ሃይል ተገፋፍታ ለመንፈሱ ስጦታ እንደገደለቻት ተናገራለች በሚስጥራዊ መንፈስ ተገፋፍቻለሁ የምትለዋ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ የ10 አመቷን ሶርያዊ ሕጻን ገደለች፡… የተባለችው ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ሶርያዊ አሰሪዎችዋ ወደ ስራ መሔዳቸውን አይታ እክፍሏ ውስጥ ተኝታ የነበረችው ሕጻን አልጋ ድረስ በመሄድ ጭንቅላቷን በብረት ከመታቻት በኋላ በተደጋጋሚ በመውጋት ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጋለች፡፡

ትንሿ ሕፃን ኢስራ በጎረቤቶቿ በተጠራ አንቡላነስ ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም እንደደረሰች ብዙ ደም ስለፈሰሳት ልትሞት ችላለች፡፡
ሳብክ ደይሊ የተባለው ዜና ዘጋቢ ሰራተኛዋ ሕጻኗ ወደ አልጋ እስክትሔድ ድረስ ጠብቃ ገድላታለች፡፡ ግድያውን እንደፈፀመች በፖሊስ ቀጥጥር ስር ብትውልም ምንም ነገር ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልሆነች ተናግራለች ብሏል፡፡
ግድያው በተፈጸመበት ወቅት ጎለቤት የነበረው አረብ መስካሪም እንዲህ ሲል ተናግሯል “ እቤቴ ውስጥ እንዳለሁ የኢስራ እናት ለእረዳታ መጣች በፍጥነት እቤታቸው ስገባ አባትየው ሕፃኗን ይዞ ያለቅሳል፡፡ በጣም ውጥረት ላይ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ እኔም በሩጫ ወደ አንቡላንስና ወደ ፖሊስ ስልክ ደወልኩ ነገር ግን ኢስራ ብዙ ደም ስለፈሰሳት ሕይወቷ አልፏል፡፡ ”
አልሳውዲ ደይሊ እንደዘገበው ደግሞ የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው ሕፃን አባት አል በቃይ እንዳሉት ሰራተኛዋ በቤተሰባቸው ጥሩ እንክብካቤ ይደረግላት እንደነበርና ከሕፃን ኢስራ ጋርም ጥሩ ግኑኝነት እንደነበራት ተናግረዋል፡፡ ቀጠሎም የኢስራ አባት “ ሰራተኛዋ ልጄን እንደልጇ ነበር የምትንከባከባት፡፡ ልጄን በጣም ትወዳት ነበር ኢስራም በተመሳሳይ ሁኔታ ሰራተኛዋን ትወዳት ነበር፡፡ ሰራተኛዋ ላይ ምንም ችግር አልነበረብኝም፡፡ ’’ ብለዋል፡፡ ቀጥለውም የሆነውን ሁኔታ ሲገልጹ “ ወደቤት ከጠዋቱ 4፡30 አካባቢ ተመልሼ ‘ ኢስራ የታለች ’ ብየ ሰራተኛዋን ጠየኳት፡፡ እሷም እሰካሁን አልጋ ላይ እንደሆነች ነገረችኝ፣ በተደጋጋሚ ልጄን ብጠራትም ምንም ማልስ ባለማግኘቴ ወደ መኝታ ቤቷ ገባሁ፣ ይህን ጊዜ ነው ልጄን በደም ተለውሳ ያገኘኋት፡፡ ሰራተኛዋ ልጄን በሆነ የመንፈስ ሃይል ተገፋፍታ ለመንፈሱ ስጦታ እንደገደለቻት ተናገራለች፡፡ ይሔ በጣም አሰቃቂና የተለየ አይነት ሀይማኖታዊነት ነው፡፡ በዚሕ ምክንያት ለማውቃቸው ሰወች በሙሉ ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ እንዳይቀጥሩ ተናግሪያለሁ፡፡ ’’ ብለዋል፡፡

Advertisements

Posted on July 18, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: