አንድ ለአምስት የተሰኘው የወያኔ አፈና መዋቅር?

አምባገነኖች ሥልጣናቸውን ዘለዓለማዊ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም። በተለይ እንደ ትግራይ ፋሽስቶች በራስ የመተማመን ብቃት የሌላቸው በዘር ላይ የተመሰረቱ ውህዳን ጥላቸውን ሳይቀር ስለሚፈሩ የአፈና መዋቅራቸውን በቤተክርስቲያን፣በመስኪድና በትምህርት ቤቶች ሳይቀር ይዘረጋሉ,,,, ከዚህም በተጨማሪ አፋኝ ሕጎችን በየጊዜ ያወጣሉ። የሚወጡት ሁሉ ሕጎቹ አሻሚና እጅግ በጣም የተለጠጠ ትርጉም እንዲሰጡ ተደርገው ነው። ምክንያቱም ሕጎቹ የሚወጡት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታስቦ ሳይሆን የወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም ታቅዶ ብቻ በመሆኑ ከሕጋዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ይላበሳሉ፤ሕብረተሰቡም የወያኔ እንጂ የኢትዮጵያ ሕጎች ብሎ አይቀበላቸውም።

የዚህ ጽሁፍ ዋና ዓላማ የወያኔን የማፈኛ ስልቶች ማጋለጥ በመሆኑ፤ ለዛሬ አንድ ለአምስት ስለተሰኘው የስለላ መዋቅር መጠነኛ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እሞክራለሁ። አንድ ለአምስት የተሰኘው የስለላ መዋቅር የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በምርጫ 1997 ከደረሰበት አሳፋሪ ሽንፈት ተነስቶ “በልማት” ሥም የፈጠረው አደረጃጀት ነው። ይህ አደረጃጀት ከመዋዕለ ሕፃና እስከ ዩኒቨርስቲ፣ከቤተክርስቲያንና መስኪድ እስከ መንግሥት መስሪያ ቤቶች በአጠቃላይ በገጠርና በከተማ በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ ተግባራዊ ተደርጓል። ዓላማውም ሕዝቡ እርስ በርሱ እንዳይተማመን በጥርጣሬ ዐይን እንዲተያይ፣ በሃገር ጉዳይ ላይ በጋራ እንዳይመክር፣ በስርዓቱ ላይ ታቃውሞ እንዳያነሳ፣ የስርዓቱ አራማጅ ፣ ደጋፊና አገልጋይ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ነው።

በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ውስጥ አንድ የወያኔ አባል አምስት የወያኔ አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን ይሰልላ። ከላይ እደተገለጸው ይህ ስለላው በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በዋናነት የወያኔ አባል ባልሆኑ መምህራንና ሰራተኞች እንድሁም ተማሪዎች ላይ ይካሄዳል። በተለይ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው በሚጠረጠሩ መምህራንና ሠራተኞች ላይ የጠነከረ ከመሆኑም ባሻገር በየዕለቱ በክፍል ውስጥ የሚናገሯቸው የትምህርት ይዘት ያላቸው ቃላትን እንደ ጸጉር እየተሰነጠቁ በየትምህርት ቤቶቹ ከተቋቋሙት የወያኔ ህዋሳት የሃይል መድረክ እስከ ከፍተኛው የወያኔ የፖለቲካ አመራር ድረስ ሪፖርት እየተደረገ በእያንዳንዱ መምህር ስም ባዘጋጁት የግል ማህደር መዝግበው በመያዝ የትምህርት፣ የሥራ፣ የሥልጠና የዕድገት ፣ … ወዘተ ዕድል ሲገኝ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዳይሆን ነጥሎ ለመምታት ይጠቀሙበታል።

በገጠርም አርሶ አደሩን አንድ ለአምስት በሚል በልማት ሥም በማደራጀት የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን አርሶ አደሮች ማዳበሪያ፣ምርጥ ዘርና ሌሎች የግብርና ግባቶችን በመከልከልና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተራችሁ ትነጠቃላችሁ ብሎ በማስፈራራት የወያኔ ደጋፊና አገልጋይ ሆነ እንዲኖሩ ያስገድዳል።

Posted on July 29, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: