የኢህአዴግ/ሕወሓትን አስቀያሚ እና ኢ-ሰብዓዊ ድራማዎችን ሲጋለጥ

የኢህአዴግ/ሕወሓትን አስቀያሚ እና ኢ-ሰብዓዊ ድራማዎችን እናጋልጥ – እስላም ክርስቲያኑ፣ መላ ብሔር ብሔረሰቦች በኢህአዴግ ድራማ ሳትታለሉ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክረን መቀጠል አለብን…

 

1-ጫካ እያሉ የትግራይ ሕዝብ አልተከተለንም በሚል የሓውዜንን ከተማ በጭካኔ በደርግ የአውሮፕላን ቦምብ እንዲደበደብና ሕዝባቸው በግፍ እንዲጨፈጨፉ ሴራውን አቀነባበሩ፣

2-ኦነግን አሸባሪ ነው ብሎ ለማስጠላት ፣ አዲስ አበባ በሚገኘው የትግራይና ግዮን ሆቴሎች ላይ ቦንብ ራሳቸው በማፈንዳት ንጹሃን ዜጎችን ገደሉ፣

3-የቀድሞው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር የነበሩትን ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያትን ለማሰርና ማህበሩን ለማፈራረስ ራሳቸው ያስቀመጡትን የጦር መሣሪያ እነ ዶ/ር ታዬ ለሽብር ሊያውሉት ሲሉ ተያዙ በማለት የሃሰት ክስ መሠረቱባቸው፣ በሃሰት ምስክርም አሠሯቸው፣

4-በምርጫ 97 ቅንጅትና ህብረት በመላው ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝተው ኢህአዴግ በዜሮ ሲሸነፍ – የምርጫ ኮሮጆ በመገልበጥ ተሸንፎ አሸነፍኩ ሲል፣ በታክሲዎችና በአንበሳ አውቶብስ ላይ ራሳቸው ፈንጅ አጥማጅ፣ ራሳቸው ጠቋሚ፣ ራሳቸው የተጠመደ ፈንጅ አምካኝ በመሆን የሽብር ድራማቸውን ሲያሳዩን ቆይተዋል፣

5-የሙስሊሙን እና የክርስቲያኑን ተቻችሎና አብሮ የመኖር የረጅም ጊዜ ታሪክ ለመበጥበጥና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር፤ በኢህአዴግ ካድሬዎች አማካይነት በርካታ ቤተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ፣ በጅማ በሻሻ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ላይ እሳት በመስደድ በርካታ ክርስቲያኖች በእሳት ተቃጥለው በገጀራ ተጨፍጭፈው እንዲገደሉ ተደረገ – (ግን በወቅቱ እንደ ሼህ ኑሩ ኢማም የድራማ ግድያ አንድም ቃል አልተተነፈሰም ነበር)፣ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ ግን ድርጊቱ የኢህአዴግ ቆሻሻ ድራማ መሆኑን ስላወቀባቸው የታሰበው የሃይማኖት ግጭት ሳይሳካላቸው ቀረ፣

6-በኦሮሞው እና በአማራው፣ በሐረሪውና በአማራው፣ ላይ የብሔር ግጭት ለማስነሳት በበደኖ በአርባ ጉጉ እና በሌሎችም ቦታዎች አማራዎችን በግፍ እንዲጨፈጨፉ ተደረጉ፣ በአኝዋኮችና በኑኤሮች መካከልም የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተካሄደ

7-የፀረ-ኢትዮጵያውያኑ የጣሊያን ባንዳዎቹ የሹምባሽ አስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ እና የሹምባሽ ዜናዊ አስረስ ልጅ፤ የተባበሩት መንግሥታት ጸሐፊ ለነበሩትና ለኢትዮጵያ ድህነትና ውድቀት እድሜ ልኳን ያለመታከት ስትለፋ የኖረችው የግብጽ ዜጋ ለነበሩት ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሌ ኤርትራ እንድትገነጠል የተማጽኖ ደብዳቤ ለፃፈው፤ አሰብን ለኤርትራ ሰጥቶ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጎ ለኑሮ ውድነት ለዳረጋት፤ ባድሜ ላይ ከ 60 ሽህ በላይ ንጹሕ ዜጎች እና ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ በጦርነት እንዲወድም አድርጎ ባድሜን ለኤርትራ አሳልፎ ለሰጠው ፀረ-ኢትዮጵያዊው መሪ ለመለስ ዜናዊ – የግዳጅ ለቅሶ እንዲለቀስ፣ በየ ቀበሌውና በየእድሩ ድንኳን እንዲጣል፣ ድህነት አባሯቸው ሳይሆን መለስን ተማምነው ጎዳና ተዳዳሪ እንደሆኑለት የማስመሰል ድራማውን ያለእፍረት ሲያሰማን ኖሯል ፣

8-የሙስሊሙ ኅብረተሰብ ስለሃይማኖቱ መከበር የሚያደረገው ሰላማዊ ትግል ሲያስፈራው ጀሃዳዊ ሓረካት የሚል የተቀነባበረ ኢህአዴጋዊ ሓረካት የድራማ ፊልም ሠርቶ በሚዲያዎቹ ቢያሠራጭም የሙስሊሙን ትግል ሊገታው ባለመቻሉ የደሴውን የሃይማኖት አባት ሸህ ኑሩ ኢማምን በኢህአዴግ ካድሬዎች በማስገደልና የእርሳቸውን ግድያ በግድ ተቃወሙ እየተባሉ ሙስሊሙ ሰልፍ እንዲወጣ በማድረግ ሙስሊሙ ደግፎናል የሚል ድራማ እየሠረሩ ናቸው፣ ሐምሌ 19 ቀንም በአንዋር መስጊድ ላይ ሙስሊሙ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ሲያቀርብ የሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ ሕገወጥ ለማስመሰል የኢህአዴግ ካድሬዎች ባንዲራ እንዲቀድዱ አስደረገ፣

Advertisements

Posted on August 2, 2013, in Andinet, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7 and tagged . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: