መንግስት በሙስሊሙ መካከል ክፍፍል መፍጠርን በማሰብ በራሪ ወረቀቶችን መበተን ጀመረ! ~

ከድምጻችን ይሰማ

በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መንግስት ሙስሊሙን ለመከፋፈል ያግዘኛል ያለውን ወረቀት እየበተነ ይገኛል…. ባለፉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ሙስሊሞች በብዛት ይኖሩባቸዋል ተብለው በሚታሰቡ አካባቢዎች መንግስት እየበተነው የሚገኘው ወረቀት ሙስሊሙ ሊታገላቸው ይገባል ያላቸውን ወገኖች እንዲያጋልጥ ጠይቋል፡፡

ነሐሴ 17/2005
‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆናችሁ ሙስሊም ወገኖቻችን ሆይ!›› በሚል ርእስ እየተበተነ ያለው ወረቀት ‹‹የገንዘብ ምንጫቸው የተነካባቸው አክራሪዎች›› ባስነሱት ግርግር ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሊሳተፍ አይገባም በሚል ደጋግሞ ይጠይቃል፡፡
ይህ ወረቀት ሸሪአን የደፈሩ፣ ከሌሎች እምነቶች ጋር ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ፣ አሕባሾች ከአገራችን ይውጡ የሚሉ በማለት ‹‹አድመኞች›› በሚል ስያሜ የጠራቸውን ወጎች ሙስሊሙ አንዲታገላቸውና እንዲያጋልጣቸው ያሳስባል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ መንግስት በበተነው ወረቀት ‹‹የመውሊድን ስጋ መብላት ጥንብ እንደ መብላት ነው፡፡ በመውሊድ ፕሮግራም ላይ መገኘት ሀራም ነው እያሉ ሲያላዝኑ የነበሩ የነብዩ ጠላቶች›› የሚሉ አረፍተ ነገሮችን በማከል የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እና እንቅስቃሴ እንደተለመደው የክፍፍል አጀንዳ በመፍጠር ለማኮላሸት ጥረት አድርጓል፡፡ መጅሊስን ለማፍረስ ሌት ተቀን የሚንቀሳቀሱ መንግስትንም ለመገልበጥ ህልም ያላቸው በሚል ወረቀቱ የሚገልጻቸውን ወገኖች ሙስሊሙ ካልታገላቸው ነገ መዘዙ ለራሱ ለሙስሊሙም ይተርፈዋል በሚልም አክሏል፡፡
የዚህ አይነት መሰል መልእክት ያላቸው ወረቀቶች በተለያዩ ጊዜያት በመንግስትና በመንግስታዊ ሃይማኖት ባለሟሎች ሲበተኑ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በወረቀቶቹ በሙስሊሙ መካካል ውጥረት ሊፈጥሩ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ ሀሳቦችን በማጎን በሙስሊሙ መካከል ግጭት ለመፍጠር እና መንግስት እንደሚሻው ችግሩ በሙስሊሞች መካከል ያለ ችግር ነው የሚል ምስል ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ዘር ጾታና አስተሳሰብ ሳይለይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ህብረተሰብ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ ማሳተፉና ሙስሊሙ መንግስት በሚሰራው ተግባር ቁጣውን ያለማቋረጥ ለሁለት ዓመታት ሲገልጽ መቆየቱ የሚታወቅ ቢሆንም ይህን እውነታ ያልተቀበለው መንግስት ግን ተስፋ መቁረጥ በተጫነው ስሜት ሙስሊሙን ለመከፋፈል የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሎበታል – ፈጽሞ የሚሳካ ባይሆንም፡፡
ከሰሞኑ መንግስት በእስልምና እምነት ተከታዮችና በክርስትና እምነት ተከታዮች መካከል ግጭት ለመፍጠር ያለሙ ወረቀቶችን በክልል ከተሞችና በአዲስ አበባ ፖሊሶች ባሉባቸው አካባቢዎች ጭምር ሲበትን መቆየቱን መዘገባችን ይታወሳ፡፡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሙስሊሞች ያነሱትን የሕገ መንግስቱ ይከበር ጥያቄ በመረዳታቸው መንግስት በሚዲያው ሲሰራቸው የቆዩ መሰል ቅስቃዎች ዋጋ አልባ ሆነው ቆይተዋል፡፡ የተነሱ ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎችን ለማፈን መብት የጠየቁ ዜጎችን ማሰር፣ መደብደብ፣ መግደል እንዲሁም በሕዝቦች መካከል የግጭት እሳት ለማንደድ መጣር የችግሩን መሰረት የማይፈታና አገሪቷን ወደ ሌላ አሰቃቂ ሁኔታ የሚመራት መሆኑን መንግስት ታሳቢ ሊያደርገው እንደሚገባ ተደጋግሞ በተለያዩ ወገኖች ተጠይቋል፡፡
አላሁ አክበር!

Advertisements

Posted on August 23, 2013, in Andinet, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: