በሰማያዊ ፓርቲ አባላት በደረሰው ወያኔያዊ ጥቃት ተቆጭተናል!!! ወጣቶች መንገዳችሁን እንድትመርምሩ እንመክራለን!!!

ነሐሴ 25 ና 26 ቀን 2005 ዓ. ም. ወያኔ በአብዛኛው በወጣቶች በተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት ላይ ያደረሰው ወንበዴያዊ የመብት ጥሰት አሳዝኖናል፤ አስቆጭቶናልም.. ይህንን ጥቃት አጥብቀን እንቃወማለን። ከወራት በፊት በይፋ አስታውቀውና ደጋፊዎቻቸውን በይፋ ጠርተው ለሰላማዊ ተቃውሞ በዝግጅት ላይ የነበሩ ወጣቶችን በቅልብ ኮማንዶዎች ማስደብደብ ተራ የመንደር ወንበዴ እንኳን የማይፈጽመው ወራዳ ተግባር ነው፤ ወያኔ ግን አድርጎታል። የመፈክር መፃፊያ ቡርሾችና ማርከሮች ካልሆነ በስተቀር ራሳቸውን መከላከያ ዱላ እንኳን ያልያዙ ወጣቶችን በጠመንጃዎች ሰደፍ፣ በጁዶና በካራቴ ተደብድበዋል። ልጃገረዶች ጤንነታቸውን ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን በሚነካ መንገድ እተሰደቡና እየተደበደቡ ጭቃ ውስጥ እንዲከባለሉ ተደርገዋል። ጋጠወጦቹ የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ከወያኔ ሹማምንት ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተላከውን መልዕክት በቃልም በተግባርም አድርሰዋል። የመልዕክቱ ይዘት ባጭሩ የሚከተለው ነው።

ሞተን አጥንታችንን ከስክሰን ያገኘነው ሥልጣን ትንፋሻችን እያለ ከእጃችን አይወጣም። እንኳንስ በሰላማዊ ትግል የመንግሥት ሥልጣንን ልትይዙ ቀርቶ፤ እኛ ሳንፈቅድላችሁ እደጅም አትወጡም። እንገዛችኋለን!!! እንረግጣችኋለን!!! ሕግ አያግደንም። እኛ ራሳችን ሕግ ነን። ምን ታመጣላችሁ? ምን አቅም አላችሁ?

ይህ መልዕክት ለሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላት በዱላና እርግጫ ታጅቦ ቃል በቃል ተነግሯቸዋል። ወጣቶች ምን ትላላችሁ? ጥንካሬያችሁን እናደንቃለን፤ ሆኖም የያዛችሁት መንገድ የባላንጣችንን ባህሪይ እግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለን። ዛሬ ጥያቄው ከመቼውም በላይ አፍጦ መጥቷል። ባርነትን ትቀበላላችሁ ወይስ አማራጭ የትግል ስልቶችን ለመመርመር ትደፍራላችሁ? ባዶ እጆቻችሁን እያሳያችሁት እየረገጠና እያዋረደ “መንግሥት” ነኝ ብሎ የሚኮፈስ እኩይ ጋጠወጥ ጋር ሰላማዊ ትግል ያዋጣል ትላላችሁ? ፍርዱን ለእናነተ እንተዋለን። ወያኔ ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የላከው መልክት ለፓርቲው አባላት ብቻ የተላከ አይደለም። መልዕክቱ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ምላሽህ ምንድነው? እስከ መቼ የወያኔን እብሪት እንታገሳለን? ያለን ምርጫ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሲል የደነገገልን ማነው? ግንቦት 7፤ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁለገብ የትግል ስልትን ሲመርጥ የሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት በማመን ሆኖም ግን ብቻውን የትም እንደማያደርሰን በመገንዘብ ነው። ስለዚህም ሁለቱም የትግል ስልቶች ተደጋግፈው መሄድ አለባቸው ይላል። ግንቦት 7 ይህንን የትግል ስልት የቀየሰው በወያኔ ባህሪ ላይ ተመሥርቶ ነው። የወያኔ ዓይነቱ እብሪተኛ ሥልጣን በያዘበት አገር ሰላማዊ ትግል ከአመጽ ትግል በላይ ዋጋ የሚያስከፍል ሊሆን ይችላል። ከዚህም በላይ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ብቻውን ድል ማቀዳጀት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ሰላማዊ ትግልና የአመጽ ትግል ውሃና ዘይት ወይም እሳትና ጭድ አይደሉም። እንዲያውም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እና ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ አንዱ ያለሌላኛው ዋጋ የለውም። ስለሆነም ከደረሰባችሁ ወንበዴያዊ ጥቃት ትምህርት በመውሰድ፤ ወደፊት ደግሞ ከዚህ የባሰ ሊመጣ እንደሚችል በመገንዘብ፤ ሁኔታዎችን መርምራችሁ በግል የስትራቴጂ ለውጥ ለማድረግ የወሰናችሁ ወጣቶች ግንቦት 7ን ማግኘት አይቸግራችሁም። ሆኖም ጊዜ የለም። በወያኔ ዓይን እና በወያኔ ፍርድ ቤት እይታ መብቱን የጠየቀ ሁሉ የግንቦት 7 አባል ነውና የምታጡት ነገር የለም። ዛሬውኑ ወስኑ!!!! ግንቦት 7፤ በዚሁ እለት ክርስቲያኑንና ሙስሊሙን ኢትዮጵያዊያንን ለማቃቃር ወያኔ የጠራውን ሰልፍ ጥበብ በተሞላበት ስልት ላከሸፈው “የድምፃችን ይሰማ” አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Advertisements

Posted on September 4, 2013, in Andinet, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: