መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከታሰሩ በኋላ ተፈተው የወጡት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢ እና ዩዋን ፐርሹን እንዲሁም ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች… ጋዜጠኞችና በስዊድን የሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ስዊድናውያን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፉትን የእስር ህይወት የሚተርከውን እና በቅርቡ ለህትመት የበቃው 438ቱ ቀናት የሚለው መጽሃፋቸው ኢትዮጵያውያንን የህሊና እስረኞችን ለማስታወስ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በከፍተኛ ስቃይ ለሚንገላቱት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እና ሌሎች የህሊና እሰረኞች የገቡትን ቃል ለማደሰ እንደሆነ በዝግጅቱ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል። በአሸባሪነት ተወንጅለው በእስር ላይ የሚገኙ የስራ ባልደረቦቻቸው በዓለም ዓቀፉ ሚዲያ በመዘንጋታቸው እና ይሄንን በመላው ዓለም ዘንድ ትኩረት እያጣ የሚገኘውን ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የመጣውን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አፈና እንዲቆም እርዳታ ለጋሽ አገሮች፡ አህጉራዊ እና ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች በኢህአዴግ መንግስት ላይ ግፊት በማድረግ በቃሊቲ፡ በቂሊንቶ፡ ዝዋይ እና ሌሎችም እስርቤቶች የሚገኙ ጋዜጠኞች፡የተቃዋሚ ፖርቲዎች መሪዎች እና በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች እንዲፈቱ ለማሰብ መጽሀፋቸውን በዝግጅቱ ላይ ይፋ ለማድረግ መወሰናቸውን ገልጸዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በህይወት ከተለዩ በኋላ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አፈና ይሻሻላል ሲባል ጭርሱን ተባብሶ መቀጠሉን በመጠቆም በቅርቡ ከማርቲን እና ዩዋን ጋር በተመሳሳይ ወራት እና ወንጀል ታስራ አሁንም በቃሊቲ እስርቤት ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባት ያለችውን ርዕዮት ዓለሙን እንደዓብነት አንስተዋል። ርዕዮት በእስር ላይ በምትገኝበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እየተፈጸመባት ያለውን ኢሰብዓዊና ኢህጋዊ በደሎች ለመቃወም ከመስከረም ፩ ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ መሆኗን በመጠቆም ይህ በገዥው ስርዓት ሎሌዎች በህሊና እስረኞች ላይ የሚካሄደው በደል እና ግፍ ቅጥ እያጣ መሆኑን አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም ውብሸት ታዬ ከእስር እንዲፈታ ያቀረበው የይቅርታ ደብዳቤ በገዥው መንግስት ተቀባይነት ካለማገኝቱም ባሻገር ከአራት ወራት በፊት ከቂሊንጦ ወደ ዝዋይ እስርቤት ሆን ተብሎ በመዛወሩ ልጁ እንዲሁም እድሜያቸው ከሰማኒያ ዓመት በላይ የሆናቸው ወላጆቹ ተመላልሰው ሊጠይቁት እንዳልቻሉ ተገልጿል። ኤቢፍ የተባለው የስዊድን የሲቪክ ተቋም፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ድንበርየለሹ የጋዜጠኞች ማህበር በስዊድን መስከረም 4፣ 2006 ዓም የተካሄደውን ዝግጅት በጋራ በመሆን ማዘጋጀታቸውን ቴዎድሮስ አረጋ ከስቶክሆልም ዘግቧል። በሌላ ዜና ደግሞ መንግስት በስዊድን ስቶክሆልም ያዘጋጀው የቦንድ ሽያጭ መርሀግብር በተቃውሞ እንዲጨናገፍ ተድርጓል። በኢትዮ ስዊድን መርሃግብር አስተባባሪነት ከጎትምበርግና ስቶክሆልም የተሰባሰበዉ የተቀዋሚ ኃይል የአዳራሹን መግቢያ በሰዉ በመዝጋትና የራሳቸዉን ቀስቃሽ ሙዚቃዎችን በማጫወት የአዳራሹን መግቢያና አካባቢዉን ተቆጣጥረዉት ስለነበር ይህን ጥሶ የሚገባ ባለመኖሩ አዳራሹ ከቦንድ አዘጋጆች በቀር ባዶዉን እንዲዉል መደረጉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በምሽቱ የሙዚቃ ፕሮግራም ላይ በተፈጠረ ረብሻም የሙዚቃ ዝግጅቱ እንደተጠበቀው አለመካሄዱን መረጃው አመልክቷል። በስዊድን መንግስት ያዘጋጀው የቦንድ ሽያጭ ሲከሽፍ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

32
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለፈው ዓመት የተመዘገበው የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) አፈጻጸም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ከኢንዱስትሪ ሚ/ር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡

በ2005 የኢትዮጵያዊያን በጀት ዓመት ከጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ከቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ከአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ከፋርማሲዩቲካልስና ከኬሚካል የወጪ ንግድ 542 ሚሊዮን 4 መቶ ሺ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው 281 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ዶላር ወይንም 52 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው፡፡ ዘርፉን ባለፉት ሁለት ዓመታት በ18 በመቶ ለማሳደግ በመንግስት በኩል እቅድና ፍላጎቱ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ይህን እቅድ ማሳካት የተቻለው በ12 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ለዚህ ከተሰጡ ምክንያቶች መካከል የአቅም ውሱንነት፣የምርት ጥራትና ምርታማነት ማነስ፣ዘላቂ የገበያ ትስስር መፍጠር አለመቻልና የተገኙትንም አሟጦ መጠቀም አለመቻል እንዲሁም የሰው ኃይል እጥረት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ከ2003-2007 ዓም መንግስት ባወጣው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ቀደም ሲል ኢኮኖሚው ግብርና መር ነው በሚል ሙጭጭ ያለበትን አቋሙን በማስተካከል እስከ 2007 ዓ/ም ድረስ ኢንዱስትሪው መሪነቱን ከግብርና የሚረከብበት ሁኔታ እንደሚኖር በእቅዱ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡

ሆኖም የአጠቃላይ ኢኮኖሚው ደካማ አፈጻጸም ኢንዱስትሪን እና ግብርናን በማዳከም በአንጻሩ ከእቅድ ውጪ የአገልግሎትን ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ደካማ አፈጻጸም አንድ ዓመት ገደማ የቀረውን የመንግሰት የትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደማይሳካ ከወዲሁ ጠቋሚ ሆኗል፡፡
ESAT

Advertisements

Posted on September 17, 2013, in Andinet, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: