ዋልያዎቹ—ከንስሮቹ ጋር ተመደቡ

(ኢሳት ዜና፦ሴፕቴምበር 16-2013)-በሚቀጥለው ኣመት በብራዚል ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ከምድቡ 1ኛ ሆኖ ያለፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለመጨረሻው የደርሶ መልስ ማጣሪያ ግጥሚያ ከናይጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተመደበ..

በርካታ ኢትዮጵያውያን ዋልያዎች-ከንስሮቹ ጋር መመደባቸውን እንደ መልካምና የተሻለ ድልድል የቆጠሩት ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ታልፋለች የሚል ተስፋ እንደሰነቁ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገፆች በሰጧቸው አስተያቶች እየገለጹ ነው። በአንፃሩ ንስሮቹ-ከዋልያዎቹ ጋር በመመደባቸው ናይጀሪያውያን ደስታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን የአገሪቱ ስፖርት ጋዜጦችና ድረ-ገፆች ዘግበዋል። ”ጎል” የተሰኘው የሀገሪቱ የስፖርት ድረ-ገጽ “ናይጀሪያ በመጨረሻው ማጣሪያ ጨዋታው ከማናቸው አገሮች ጋር ብትመደብ ትመርጣላችሁ?”በማለት ለናይጀሪያውያን ላቀረበው መጠይቅ፦ 13.8 በመቶው-ግብጽ 11.2 በመቶው ካሜሩን 23.7 በመቶው ቡርኪናፋሶ 10.8 በመቶው ሴኔጋል ሲሉ፤ 40 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያ ጋር ቢመደቡ እንደሚሻላቸው ነው ምላሽ የሰጡት። ቢቢሲ በበኩሉ የባለፈው የ አፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮና ናይጀሪያ -ዝቅተኛ ደረጃ ካላት ኢትዮጵያ ጋር ተመደበች ነው ያለው። ኢትዮጵያና ናይጀሪያ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን፤ከምድባቸው ባደረጉት የመጨረሻ ጨዋታ ንስሮቹ-ዋልያዎቹን 2 ለባዶ ማሸነፋቸው ይታወሳል። እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በካዱና ስታዲየም ከቡርኪናፋሶ ጋር ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ -ንስሮቹ በከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ 4ለ 1 በማሸነፍ በጠንካራ አቋም ላይ እንደሚገኙ አስመስክረዋል። ይሁንና በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ የተዘጋጀውን ጨምሮ ለሦስት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ያነሱት ናይጀሪያዎች- በአህጉራዊውም ሆነ በዓለም ዋንጫ በመሳተፍ የተሻለ ልምድና ከፍተኛ ብልጫ ያላቸው ቢሆኑም፤ ዋልያዎች ከወዲሁ በስነ ልቦና በመዘጋጀት የተቀናጀና የተጠናከረ ሥራ ከሠሩ በኢትዮጵያ እግር ኳስ የታሪክ መዝገብ ላይ ስማቸውን በደማቅ ቀለም የማይጽፉበት ምክንያት አይኖርም ይላሉ- ኢትዮጵያውያን የስፓርት ደጋፊዎች። ከዋልያዎች አጨዋዎት አኳያ ይህን ታሪክ ለመሥራት ከሌሎቹ ቡድኖች ይልቅ ከናይጀሪያ ጋር መመደባችን የተሻለ እንደሆነም-የስፖርት ተንታኞቹ የሁለቱን ቡድኖች የአጨዋዎት ስልቶች በመተንተን አስተያየት ሲሰጡ ተደምጠዋል። የንስሮቹንና-የዋልያዎቹን መገናኘት ተከትሎ ናይጀሪያውያንም፣ኢትዮጵያውያንም ተስፋቸውንና ደስታቸውን እየገለፁ ነው። የማንኛቸው ደስታ እውን ይሆናል?ሚለውን ጊዜው ሲደርስ የምናየው ይሆናል። በሌላ ምድብ አይቮሪኮስት-ከሴኔጋል፣ቱኒዚያ-ከካሜሩን፣ጋና፣ከግብጽ እና ቡርኪናፋሶ ከ አልጀሪያ ተደልድለዋል። የደርሶ መልስ ጨዋታው የሚካሄደው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከመጪው ኦክቶበር 11 እስከ 15 እና፤ከኖቬምበር 15 እስከ 19 ድረስ ባለው ጊዜ ነው። ዋልያዎች-ከንስሮቹ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት በአዲስ አበባ ነው።

Posted on September 17, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC, Sport News. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: