የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በድምቀት ተካሄደ! (ፖሊስ ከ4 ኪሎ እንዳያልፉ አድርጓል)

በአሁኑ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ ከሶሰት ወር በፊት የጠራውን ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል:: ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ ነበር የሰልፉ መድረሻ መሰቀል አደባባይ ቢሆንም ሕዝቡ አራት ኪሎ አካባቢ ሲደርስ የአዲስ አበባ ፓሊሶች ሰልፈኛውን ወደ መሰቀል አደባባይ እንዳይሄድ ሲያግዱ የፌድራል ፓሊስ ደግሞ በርቀት እየተመለከተ ነው..ሰልፈኞቹ ወደ ስማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዲመለስ ተደርጓል ሕዝቡ ግን ድምጹን ከማሰማት ወደኋላ አላለም::

ርዮት ትፈታ! ውብሽት ይፈታ! እሰክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡበከር ይፈታ! ፍትህን መጠየቅ አሽባሪነት አይደለም!! ነፃነት እንፈልጋለን !! እኛ አሽባሪ አይደልንም! ፍትሕ እንፈልጋለን! የሙሰሊም ኮሚቴ ይፈቱ! ዜጎችን ማፈናቀል አግባብ አይደለም! አንለያይም! አንለያይም! ፍትህን ያሉ ቃልቲ ገቡ!! አሽባሪ አይደለንም! ፍትህ ናፈቀኝ! ድምፃችን ይሰማ!! ፍትሕ እያሉ ቃልቲ ገቡ! ውሽት ሰለቸን! ፍትህ ናፈቀን!

ሰማያዊ ፓርቲ ወያኔ የሚረግጡትን መሬትና የማይረግጡትን ምድር ወስኖ ሰልፈኛውን ከቦ እንዳሰቡት መስቀል አደባባይ መድረስና ከህዝብ መገናኘት እንዳይችሉ በማድረጉ ወደ ቢሮ በመመለስ የሰልፉን በሰላም መጠናቀቅ አብስረዋል፡፡ ይህ ትልቅ የአመራር ብቃትን፤ ሀላፊነትንና ለህዝብ ወገንተኝነትን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ወያኔዎች ሰልፉን ለማቆም ባትወስኑ ኖሮ ህዝብ ላይ መተኮስን እንደልማዳቸ ይፈፀሙት ነበር፡፡ብስለት የተሞላው አመራር በማድርጋችሁ አድናቆት ይገባችኀል፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ ህዝብ ያሸንፋል!

semayawi1semayawi2semayawi3
semayawi6semayawi4semayawi5
 

 

የዜና እና ፎቶ ምንጭ፡ ልዩ ልዩ ማህበረሰባዊ ድረ ገጾች

Advertisements

Posted on September 22, 2013, in Andinet, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: