ማን ነው የሚለየው ይህ ትውልድ ለወያኔ ፍም እሳት ነው !!! የዕለቱ ምርጥ ዘፈን በኖርዌይ ኦስሎ ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ !!!!

በኖርዌይ የሚገኘው ይህ የምትመለከቱት ዌብሳይት ትላንት ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ የተደረገውን ለግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በ26.09.2013 13:23 ላይ የተለመደውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የነዛበት ሊንክ እና ፕሮግራሙን እንዳይካሄድ ለማድረግ ብዙ የደከመበት ስራ ይህን ይመስል ነበር….

ይቺን ሊንክ ይጫኑ               http://www.abesha.no/P%C3%A5-Amharisk/1372

ወያኔ ጥጋብ በወለደው እብሪቱ በማንአለብኝነት የህዝብን መብትና ነጻነት ረግጦ በአፈና ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አለኝታየ በሚላቸው የፖሊስ፣ የደህንነትና ወታደራዊ ኃይሎች እስከ መጨረሻው አጠናክር ለመቀጠል የሚችል አድርጎ ያስባል። በዚህም ምክንያት እስካፍንጫው ባስታጠቀው ወታደር ብዛትና በነዋሪው ቁጥር ልክ ህዝብ መሃል ባሰማራው ሰላዮች የተገነባው የፍርሃት ግምብ የሚናድም መስሎ አይታየውም። ሃቁ ግን በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተሰባሰቡ ወጣቶችም ሆኑ መላው አለም ላይ የሚገኙ በተለይም በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች እና ወያኔን በአራቱም የአገራችን ማዕዘናት ለመግጠም ጠመንጃ ያነሱ ሃይሎች ወያኔ ህዝባችንን ሊያስፈራራ የሚችልበትን ሁሉ በጣጥሰው ለመውጣት ምንም ችግር የሌለባቸው መሆኑን በትላንቱ  በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል  የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ግንባሩን ወክለው የመጡት እንግዳ እና ኢትዮጵያኖቹ በኩራት እና በቁርጠኝነት ተናግረዋል። በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው  ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የተገደዱት የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን በገንዘብ ለመርዳት ታስቦ የነበረውን ቀን በኖርዌይ የሚገኙ ጸረ ኢትዮጵያን የወያኔ ደጋፊ ጉጅሌዎች ለተወሰነ ሰዓታት ባደረጉት የተሳሳተ ወይንም ያልተገባ ውሸት በደስታ የተፍነከነኩበት በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያን ቁርጥ ልጆች ድል  ተጠናቋል

Norway G7 fundrise

ትላንት ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ።  በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። በመጨረሻም በኖርዌይ የምንገኝ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የምናስተላልፈው ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው።

፦ ወያኔ ገንብቻለሁ ብሎ የሚኮፈስበትን የፍርሃት ግምብ ደርምሰው ለነጻነታቸው ሲሉ ውድ የህይወት ዋጋ ለመክፈል በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ዙሪያ መሰባሰባቸውን ይፋ ያደረጉ እነዚህ ወጣቶችን በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች  የተነሱለትን ክቡር አላማ ያደንቃል። በዚህም ምክንያት ለነጻነቱ ቀናኢ ለሆነው ለህዝባችን ያቀረቡትን የትግል ጥሪ ወቅታዊነት ሁሉም እንዲረዳው እና በመላው ዓለም ላይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ  የበኩሉን አሰተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን ። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር

Posted on September 29, 2013, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: