ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!

የህውሃት/ኢህአዴግ ጠንካራ ጎኑ እስከ ጥርሳቸው ድረስ የታጠቁት ፖሊስ፣ ድህንነት፣ ምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ካድሬ እና ቅጥረኛ ወርበሎችን ያካትታል። የሚያውቀው የፖለቲካ ትግል ዘዴ በጫካ መገዳደልን እንጂ በከተሞች ሰላማዊ ትግሎች ማድረግ አይደለም…

udj 4 19

  ስለዚህ ሰላማዊ ትግል ህውሃት/ኢህአዴግን በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል እንደሚያስገድደው እና የህዝብ ድጋፍ የሚያሳጡ ስህተቶች እንደሚያሰራው የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወለል አድርጎ አስተምሮናል።
ስለዚህ በእነዚህ ሶስት ወሮች ህውሃት/ኢህአዴግ ማለቂያ የሌለው ፖለቲካዊ እና ህገ-መንግስታዊ ስህተቶች ፈጽሟል። ከፈጸማቸው ስህተቶች ውስጥ ከግብር የሚሰበሰብ ገንዘብ የሚከፈላቸውን የከተማ አስተዳደሮች፣ ፖሊሶች፣ ደህንነቶች ፣ ካድሬዎች እና ቅጥረኛ ወረበሎች በመጠቀም እውቅና የሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ፣ ቅስቀሳ መከልከል፣ የቅስቀሳ መኪናዎችን ከማሰር አልፎ ጎማቸውን ማስተንፈስ፣ በቅስቀሳ ላይ የተሰማሩ ሰላማዊ የነፃነት ሐዋሪያትን ማሰር፣ መደብደብ፣ እጃቸውን መስበር እና መሰረተ ቢስ ምክንያቶች በመፍጠር በየፖሊስ ጣቢያው በማቆየት የቅስቀሳ ጊዜያቸውን ማቃጠል የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህ ስህተቶች ብዙዎች ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ምክንያት ሰጥቷቸዋል። ስለዚህ ህውሃት/ኢህአዴግ ቀደም ብሎ የፖለቲካ ጥንካሬ (የህዝብ ድጋፍ መጠን) ከነበረውም ባለፉት ሶስት ወሮች ሲሸረሽረው እና የአንድነቶችን የፖለቲካ ኃይል (የህዝብ ድጋፍ) ሲያሳድግ ቆይቷል። እራስን በመጉዳት የፖለቲካ ተቀናቃኝን አቅም ከፍ ማድረግ ማለት ይኽ ነው። በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል በመደረጉ ነው ይኽ ሊሆን የቻለው። ስለዚህ አንድነቶች የፖለቲካ ኃይል አቅማቸው እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ህውሃት/ኢህአዴግ ስህተት መስራቱን እንዲቀጥል ማድረግ አለባቸው። ሰላማዊ ትግላቸው ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ ብቻ! የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ሌሎች ሁለት ተጨማሪ ነገሮችን አስተምሮናል። እነሱም፥
(1ኛ) እርግጥም ዜጎች ነፃነት እንደሌላቸው በተግባር አስተምሮናል። ህውሃት/ኢህአዴግ ሰላማዊ ሰልፍ እና ህዝባዊ ስብሰባ በሚያደርግበት መስቀል አደባባይ ሳይቀር ተመሳሳይ ስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነት እንደሌለህ አስተምሮሃል። ስለዚህ የሰላማዊ ትግላችን ግቡ እራሳችንን ነፃ ማውጣትም መሆን እንዳለበት ባለፉት ሶስት ወሮች በተጨባጭ ተምረናል። እውቅና አግኝተን በነፃነት ቅስቀሳ ማድረግ ቢያቅተን ሊደንቀን አይገባም። በነፃ ቅስቀሳ ማድረግ አቃተን ብሎ ማልቀስ ትርጉም የለውም። ነፃ እስክንወጣ ድረስ ላለው ጊዜ ጽናት እና ብስለት ኖሮን ሰላማዊ ትግላችን ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ በመንገዳችን ላይ የሚደቅንብንን መሰናክሎች እየተራመድን ቅስቀሳ ማድረጋችንን መቀጠል ይገባናል። እራሱ ህውሃት/ኢህአዴግ በሚፈጽማቸው ስህተቶች ሰላማዊ ትግላችንን ከተቃውሞ እና ማግባባት (Protest and Persuasion) ወደ ትብብር መንፈግ (Non-cooperation) እና ጣልቃ መግባት (Intervention) ደረጃ እንዲያሸጋግረው መንገዱን በዘዴ ልንጠርግለት ይገባል።
(2ኛው) የሰላማዊ ትግል መሪዎችን ጀግንነት፣ ግንባር ቀደምነት፣ ለመታሰር ዝግጁነት፣ ሳይገድሉ ሞተው ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኛነት የአንድነት መሪዎች እራሳቸውን ምሳሌ በማድረግ አስተምረውናል። በዚህ ረገድ የአንድነቶች ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የማይረሳ እና ወደፊት ከፖለቲካ ትግል መሪዎቻችን የምነጠይቀው ታሪክ ሰርተዋል። ታሪኩ ባጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፥
መስከረም 16 ቀን 2006 ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ 28 ያህል የታሰሩ የፓርቲውን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ለማስፈታት ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሽሮ ሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣብያ በማምራት ለፖሊሶቹ ‹‹ልጆቹ የፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት የለም፣ ሲቀሰቅሱ የነበሩትም እውቅና የተሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ ቅስቀሳው ህገ ወጥ ነው የምትሉም ከሆነ እነርሱን የላኳቸው እኔ በመሆኔ እኔን ልታስሩኝ ትችላላችሁ ››ብለዋል፡፡ ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን በማሰር ወጣቶቹን ለቅቋቸዋል፡፡ ፖሊስ እሳቸውን ለአጭር ጊዜ አቆይቶ ከለቀቃቸው በኋላ ከዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ጋር ባደረጉት አጭር ምልልስም “ከዚህ በኋላ መታሰር ያለብን እኛ ነን እንጂ አባሎቻችን አይደሉም” ብለዋል።
Advertisements

Posted on October 3, 2013, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: