አምላክ ሆይ፥ አንተ እውነትም ፃድቅ ነህ!(from concerned Ethiopian)

እግዚአብሔር የድሆችና የስደተኛ ዓባት ነው፥ የድሃደጉን እንባ፣ የመበለቷንም ለቅሶ ዓዳመጠ፣ የችግረኞች ወዳጅ ሳኡዲ አረቢያን በቅጣት በትር ጎበኛት! የልጆቹን በደል፣ ግፍና፣ መከራ እግዚአብሔር ከላይ ተመለከተ፣ በቁጣ ከሰማይ ዓንጎዳጎደ፥ በሳኡዲ ዓረቢያ ከተሞች በበቀል ወረደ፥ ሰማያዊ ተግሳጽንም አዘዘ፥ ምድሯን በጎርፍ መታ፥ ልጆች ከወላጆች….

ሚስት ካባሏሳይገናኙ እንደ ወጡ ቀሩ፥ በብዙ ወርቅና ብር የተንቀባረሩትን የዓረቢያ ኩራቶች በጭብጥ የዝናብ ማእበል በተናቸው፥ ዳግም እንዳይነሱ አድርጎ ከምድረበዳው አሸዋ ጋር ቀላቀላቸው፥

በሰታታው የሳኡዲ ሜዳ ላይ ተንጠራርተው የቆሙት ታላላቅ ሕንጻዎች እንደ ሰም ቀለጡ፥ የሳኡዲን ውብ ከተማዎች ለማገናኘት የተንዥረገጉ ሽንጣም ድልድዮች እንደ ቸኮሌት ባር ተፍረክርከው ወደምድር ሆድ ገቡ፥ በግፍ ደም የተገነባች የክፉዎችና የዓመጸኞች ከተማ፣ በእንባ ጎርፍና በደም ጭቃ የተዋበ ባለጸግነት ከንቱ ሆነ፥ ዛሬ በማለዳ ዓይኖቸ ገና ከእንባ ዓልደረቁም፣ ውስጤ ደምቶ፣ የልቤ ስብራት በሃዘን እያመረቀዘ ባለበት ጊዜ፣ የሕዝበ ኢትዮጵያ ጠላቶቸ እለቅሶና የጣረሞት ድምጽ ከሞት ሸለቆ ከሳኡዲ ተሰማ፥ የዓመጻና የግፍ ብድራታቸውን ሳይውል ሳያድር በብዙ እጥፍ ሲከፍሉ ዓየሁ፥

ትላንት በፊቱ ሲመጻደቁበት ያየነውን የዓለም ሁሉ ፈጣሪ ዛሬ የወረደውን ዶፍ እንዲያቆረው ሕዝበ ሳኡዲ በሲቃ ድምጽ ሲማጸን ሰማሁ፥ ከንቱ መማጸን፥ አቤት ኣምላከ እስራኤል እንዴት ድንቅ ነው፥

ከጻድቁ እግዚአብሔር የፍርድ በትር የሚታደጋቸውስ ማነው?

ወዮልሽ ሳዑዲ ዓረቢያ፥ ይህ የማስጠንቀቂያው ደወል ነው፥ በዓደባባዮችሽ ላይ የንጹሃን ደም በግፍ ፈሶበታልና እግዚአብሔር ይበቀልሻል፥ ሰርተው ለመብላት በተሰደዱ ንጹሃን ሕዝቦች ላይ ለሰራሺው ግፍና በደል ገና ብዙ ዋጋ ትከፍያለሽ፥ ልጆችሽ ከትውልዳቸው፣ ዓዛውንቶችሽ ከዕርስታቸው ይነቀላሉ፥ ስሚ አንች የክፋት ከተማ፣ የእግዚአብሔር መርገም በዓንች ላይ ነው!

እነሱ በፈረሳቸው ይታመናሉ፣ እኛ ግን በዓምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን፥ ትዕቢተኛውን  ፈርኦን የቀጣ፥ ፈረሱን እና ፈረሰኛውን በቀይ ባህር ላይ የጣለ፣ የእስራኤራል አምላክ ቅዱስ  እግዚአብሔር  ለዘላለም  ስሙ ከፍ ይበል፥  አሜን!

Advertisements

Posted on November 19, 2013, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7 and tagged , , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: