የወገን ደራሽ ወገን ነው ታላቅ ሕዝባዊ ሰላሚዊ ሰልፍ ጥሪ በስቶክሆሎም ከተማ የሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ ፊለፊት !!

Flag-Pins-Ethiopia-Sweden

በሲዊድን የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የድጋፍ መሀበራት እና የሲቭል ማህበራት በጋራ በመሆን ሳውዲዓረቢያን በኢትዮዽያን ወገኖቻችን ላይ እያደረሱ ያለውን ግፍ እና ሰቆቃን በመቃወም በጋራ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶዓል በመሆኑም በሲዊዲን ስቶክሆሎም…

    የሰልፉ አንገብጋቢነት፣ መነሻና አላማ፡ ሰሞኑን በተለያዩ  የብዙሃን መገናኛዎች እንደተገለፀው ሁሉ በሳውዲ ዓረቢያ በተለያዩ   ከተሞች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውና  አሁንም በባሰ መልኩ እየተፈፀመ ያለው አስነዋሪ፣ አሳዛኝ፣ አሳፋሪ  የሆነ ኢሰብኣዊ  ድርጊትን በመቃወም፡

1.የሳውዲ ዓረቢያ አረሜናዊ መንግስት በወገኖቻችን  ላይ እየወሰደ ያለውን የግድያ፣ በእስር የማሰቃየትና የማንገላታት  እርምጃ  በማውገዝና ድርጊቱንም በአስቸኳይ እንዲቆም መልእክታችንን  ለማስተላለፍ ነው።

2. ይህ እርምጃ የዓለም አቀፍ የሰብኣዊ ፍጡር ነፃነት ድንጋጌዎችን የሚጥስ ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ የዓለም ማሕበረሰብና ሰብኣዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶችና ተቋሞች ሁሉ የጉዳዩን   አሳሳቢነትና ጥሰት በመገንዘብ  ለችግሩ መፍትሔ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ለማቅረብ ነው።

1441241_477494402369475_1830722221_n (1)

                                  የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን ሆይ!!

ባለቤቱ ያቃለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም እንዲሉ  በገዛ መንግስቱ የተረገጠ ህዝብን የሌላ መንግስት በዓክብሮት በንክብካቤ ይቀበለዋል ማለት ዘበት ነው  በገዛ ሀገሩ እንደባይተዋር ተቆጥሮ፣ ነፃነቱ፣ ሰብኣዊ ክብሩንና ማንነቱን ተነጥቆ፣

አውራ እንደሌለውንብ ስደት እንደ አማራጭ ወስዶ ራሱን ዝቅ አድርጎና ተበታትኖ የሚኖር  ህዝብ  በሚረባና  በማይረባ ሀይል እንደ አራዊት  እየታደነ  ሲቀጠቀጥ ዝም ብሎ እየታየ ቆይቶ አሁን አሳሳቢ  ሁኔታ ላይ መድረሱ እሙን ነው። የሰው ልጅ ሞተ የሚባለው መቃብር ከወረደ በኋላ አይደለም። ሞት የሚጀምረው እንደ ሰው ለመኖር የሚያስችለው ሞራል፣ ማሰብና ማድረግ ሲያቆም ነው ብለዋል የነፃነት ታጋዩ ማልቲን ሉተር ኪንግ ታዲያ!!   አንገታችንን  ደፍተን ዝም በማለት የዓረብ ቱጃሮች መጫወቻ እንድንሆን በገዛ ራሳችን  ስለፈቀድንላቸው ለዚህ ሁሉ ዕልቂትና መከራ ተዳርገናል።

በበረሃ ሲጉዓዝ በውኅ ጥማትና በዘራፊዎች  እጅ  ህይወቱን  ኣቶዓል በሰባራና  በታጨቀ  ጀልባ ባህር ሲሻገር የዓሳ እራት ሆኖኣል በበረሃ ሲጉዓዝ  በውኅ ጥማትና በዘራፊዎች እጅ ህይወቱን ኣቶዓል   ሴቶች እህቶቻችን ወንድሞቻችን ህፃናት ልጆቻችን ተደፍረዋል  ኣሁንም በሳውዲ ኣረመኔዎች እና ጨካኞች እየተደፈሩ ነው::

ዘረኛው እና ከፋፋይ የትግራይ ነፃ ዓውጪኝ ባይ ድርጅት ኢትዮዽያን በሓይል መግዛት ከጀመረበት ግዜ ጀምሮ ብብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የሚመራው ጨቜኝ መንግስት ለሃገሩ ህዝብ የስራ መስክ ለመፍጠር ፍላጎት ስለሌለው  እና ከህዝቡ በቀረጥ ከዓለም ባንኮች በብድር እና በተለያየ መንገድ የሚዘርፈውን ሀብት በባዕድ ኣገር ስለሚያከማች ለህዝቡ ምንም ኣይነት የስራ  ዕድል መፍጠር ዓቅሙ እጅግ በጣም ደካማ ነው

በሀገሪቱ ውስጥ  በትንሹ የሚገኘውንም የስራ ዘርፍ በዘር እና በፖለቲካ ዓባልነት የሚታደል ስለሆነ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሃገራችን ወጣቶች ወደ ባዕድ ሀገር ለመሰደድ ተገደዋል በሰሞኑ በሳዓውዲ ዓረቢያ መንግስት በወገኖቻችን ላይ የግድያ የግርፋትና የዕስራት ሴት እህቶቻችንን የመደፈር የዛ ውጤት ነው ኢትዮዽያዊነት በደም ውስጥ የሌለበት የዓንባ ገነኑ መንግስት ኢሰብዓዊ ውጤት ነው በዓሁኑ ሰዓት በዓገር ውስጥም ሆነ በባዕዱ ዓገር ለኢትዮጵያኖች ህልውና መቆም የለም ስለዚ ሃላፊነቱ የኛ ስለሆነ በዓሁኑ ወቀት በሳውዲዓረቢያ የዘላን መንግስት የሚያደርገውን ዓረመኔኣዊነትን እስራት ግድያና ሤት እህቶቻችንን ልጆቻችንን መድፈር መቃወም አለብን

በመላው  ዓለም ያሉ ኢትይፕዽያውያን ፒቴሺን  በማስፈረም  በፋክስ በዒሜል  እና በተለያዩ  ሚዲያዎች  በያሉበት ሀገር ባሉ የሳዐውዲ ዓረቢያን ዔምባሲ በመሔድ ቁጣቸውን እየገለፁ ነው

በዓሁኑ ሰዓት በዓገር ውስጥም ሆነ በባዕዱ ዓገር ለኢትዮጵያኖች ህልውና የሚቆም የለም  ስለዚ ሃላፊነቱ  የኛ ስለሆነ በዓሁኑ ወቀት በሳውዲ ዓረቢያ የዘላን መንግስት የሚያደርገውን ዓረመኔኣዊነትን እስራት ግድያና ሤት እህቶቻችንን  ልጆቻችንን መድፈር መቃወም ለዓለም ህዝብ የድረሱልን ጥሪና የሳውዲ ዓረቢያ መንግስት ከጨካኝ ድረጊቱ እንዲቆጠብ ወደፊትም እንዳይደግም ለማድረግ በህብረት መነሳት ዓለብን

አደባባይ ወጥተን ለያንዳንዳችን ነፃነት፣ ማንነትና  ክብር ስንል አኩሪ ታሪክና ወርቃማ ባህል ያለን ህዝብ መሆናችንን  ለሳውዲ ሰውበላ መንግስት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ህዝብም ካላሳየን በስተቀር ማንም ጥብቅና ሊቆምልን የሚችል ሀይል አይኖርም። ይህም የአሁኑ  ትውልድ መመለስ ያለበት የጋራ ሃላፊነት ነው ብለን እናምናለን።  አዎ!! እኛ ኢትዮጵያውያን በአፍሪቃ አህጉር የነፃነት፣  የኩሩና የአትንኩኝ ባይ የጥቁር ህዝብ ተምሳሌት ተብለን በዓለም ታሪክ እንዳልተመሰከረልን  ሁሉ  ዛሬ መሬታችንንና አንጡራ ሀብታችንን በሳውዲ ቱጃሮች  መወረሩንና መዘረፉን ሳያበቃ ሀገርና መንግስት እንደሌለን ተቆጥረን ወገኖቻችንን  እንደ ርካሽ ዕቃ ሲጣሉ፣ በአደባባይ ሲገረፉ፣ በጥይት ተደበድበው  ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ ሲቀር፣ እስር ቤት ሲበሰብሱ፣ ንብረታቸው ሲነጠቁ፣ ሰብእዊ  ክብራቸው ተደፍሮ ባዶ እጃቸው ሲባረሩ ማየቱና መስማቱ  እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን እንደ ህዝብም እንደ ሀገርም ተንቀናል ተዋርደናልም። ኢትዮጵያ የዜ ጎችዋን ድህንነት የሚጠብቅ መንግስት አላት ወይ ብሎ ደፍሮ ለመናገር ሀፍረት የሆነበት ጊዜ ላይ ነን ያለነው።

ዛሬ የሰው ልጅ  በሰለጠነበትና መብቱን ለማስከበር ግሎባል መነቃቃት  በተፈጠረበት በአሁኑ በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን ላይ ሆኖ ዘመናዊ ባርነትንና  ውርደትን አሜን ብሎ የሚቀበል ትውልድ እስካለ ድረስ ደግሞ  አደጋው እንዳየነው ሁሉ ከዚህም የባሰ ሊመጣ እንደሚችል አያጠራጥርም። ስለዚህ በየአካባቢያችን በሳውዲ ዓረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት  የምናደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የፓለቲካ ወይም የአንድ ቡድን ሰብኣዊ ርህራሄ  ጉዳይ ሳይሆን ሁላችንም የሚመለከት የኢትዮጵያዊነት ግዴታም ጭምር  ነው።

ማነኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል የሚመለከተው ስለሆነ ዲሴምበር 04/2013  ከቀኑ 13.00 pm   ሰዓት ስቶክሆልም ከተማ በሚገኘው  ሳዓውዲ ዓረቢያ ኢምባሲ ተቌውሞዓችንን ለማሰማት የፖሊስ ፈቃድ ኣግኝተናል የሠልፉ መነሻ  ከሳዊዲዓረቢያ ኢምባሲ   ሆኖ  የሠልፉ መድረሻ እና መጨረሻ   የኢትዮጵያ ኢምባሲ ይደረግ እና የሰልፉ  ማጠናቀቂያ፡  16:00 pm  ይሆናል ስለሆነም ኢትዮጵያዊያኖች በሙሉ ያለንን ጥቃቅን  ልዩነቶች ወደ ጎን ዓድርገን ለወገኖቻችን ከጎናቸው በመቆም በጋራ  በስዊድን አካባቢ በምትኖሩ ኢትዮጵየውያንና የአትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ ሁሉ በሠላማዊ ሠልፉ እንዲሳተፉ የአክብሮት   ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሠልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ

Advertisements

Posted on November 22, 2013, in Andinet party, ETHIOPIA ENGLISH, Ginbot 7, OLF and tagged , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: