ሀገራችንንና ህዝባን ያዋረደ የዘመኑ የወንበዴ ስብስብ TPLF ( Aseged Tamene)

ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ አንድ ሀገር ሳትሆን በወሮ በላ ተከፋፍላ በክልል ታጥራ እንድትኖር በህወአት ማኒፌስቶ(ሕገመንግስት) ፅሑፍ ተረቆላት፣ ህዝቦቹ በፊት ያልነበሩ፣ እንደአዲስ ተፈጥረው ለመሬት፣ ለወደብ፣ ለዳርድንበር፣ ለቋንቋ…

ለባሕልና ለታሪክ፣ ለአንድነትና አብሮ መኖር እሴት ላይናገሩ እንኳንም በቁማቸው ስለሚኖሩበት መሬትና መብት ፣ሞተውም ኪራይ የሚከፍሉባት የመጤዎች መስፈሪያ ስትባል ህዝቡ ፣ባርኔጣውን ደፍቶ፣አንገቱን በሻርብ አስሮ፣ በቀን በቀን ዘፈን እየነገደ እንደከብት ሲፈነጥዝ 22 ኣመት አለፈ።

ወሮ በላው ኢህአዴግ ህዝቡን አሸበረው፣ ጭንቅላቱን አናወጠው ምን የዜግነት ከብር አለን ማንነታችን ከተዋረደ መብታችን ከተገፈፈ ኢትዪጵያዊነታችን ከላያችን ከተነጠቅን ቆየን እኮ ጐበዝ? የፈሰሰው ደም የሚፈሰውም ደም አይበቃም አልበቃቸውም ።እሄንን ጉድ ሳያዩ ያለፉ ጀግኖች አባቶቻችን እንዴት እድለኞች ናቸው እራሳቸውን ሰውተው ለልጆች ያቆዯትን ሀገርና ህዝብ አንገቱን እንዳይደፋ ቀና ብሎ እንዲሄድ እኮ ነበር አባቶቻችን የለፉት ዛሬ ታሪክ ተቀይሮ ።ስቦ ያስገቡት ስቦ ያወጣል እነረዲሉ እሄው ዛሬ የዜግነት ክብር ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በስደት ይሞታል አውሬ እንደበላው እንስሳ በየመንገድ ይጉተታል።እኔ በአረብ አልፈርድም መክኒያቱም ባለጌ ነው ለዚህ ላበቂን ባዳ ወያኔ ነው ።ሰው ቤቱን እራሱ ከላስከበረው ጉረቤቱ ሊያስከብረው አይችልም።ወገኔም ይሄው በችግር እስከ ሞት ድረስ ወጦ ቀረ ።እሄ ጉዳይ እኛው ካላቆምነው ይቀጥላል።የኛ ጠላት ወያኔ ነው አረብም አይደለ ቅማጩን እያንጠበጠበ በነጠላ ጫማ በቁምጣ ገብቶ ዛሬ እሱ ናሪ የኢትዮጵያ ልጆች ተሰደው የመከራው ቀማሽ የምንሆንበት ምክንያት አልገባኝም ።ለመሆኑ አንድ ጥያቄ አለኝ ለአንባብያን ሙሉ ኢትዮጵያ የማንናት?እኔ እደሚገባኝ የሁላችንም ናት ጀግኖች የሞቱልን ለሁላችንም ነው። ታዲያ ምነው በሀገራችን ሁለተኛ ዜጋ ከሁለተኛም በታች ስንሆን ዝም ብለን እናያለን ደሞ የኛን ሁለተኛም ከዛም በታች አደሆን የሚነግሩን ስበን ያስገባናቸው አሁን ስበው ብትንትን አድርገው ያስወጡን ምን እስኪያረጉን ነው የምንጠብቃቸው ምነው ጉበዝ ሞትኮ ክብር አለው እንደ ጀግኖቻችን እዴው ጨው ሲበዛ ይመራል እኮ አይበቃም! እነደዚህ አይነቱን እየሰማንና እያየን ከምንኖር ምናለ ያለቀው አልቆ ክብራችን አስመልሰን ለትውልድ ዜግነትን ሰጠን በናልፍ ወገን የተዋረደውን ክብራችን ምናስከብረው እኛ ን አንድ ሁነን ።ማንም አያስጠብቅልንም ወያኔማ አላማው እሄ ስለሆነ ተሳካለት ምን ብሎ ለዜጋ ያስባል አንዴ ባህር አዴ በበረሀ አሁን ደግሞ በሳውዴ እያለ ቁጥር ይቀንስ እጀ ለሱማ ሰርግና ምላሽ ነው ።መጀመሪያ መንግስት ሲኖር እኮነው?እና ወገን እነሱ ቡዙ ሲያደርጉን እኛ ምላሽ አንሰጥ ተስማምቶናል ግዙን የምንል እኮ ነው የሚመስለው። አሁንም የአንድ ሰሞን ዜና ሁኖ ያበቃል። ማለቂያም ለው ነው የምለህ ወገኔ ምናሳልቃቸው እኛ ካልሆን ያልቃል ብለህ እዳትሞኝ በያለህበት ተነስ ።ቀን እስኪያልፍያባትህ ባሪያ ይግዛህ ይባል የለ ። ደሞ ባንዳና ባሪያ በታሪክም የለ ኢትዮጵያን ገዝቶ አያውቅም በቃ እንበለው። ባለጌን ባለጌ ማለት ያስፈልጋል ። በርግጥ የኢትዮጵያ ልጆች ትግስ ፍቅር አስተማሪም ናቸው ባለጌ ግን ሁሌም አይ ማርም ። ለባለጌ መዳህኒቱ ሁላችንም ነን። መዳህኒቱም መሰጠት ያለበት አሁን ነው ቡዙ ሰው ታሟል ከመሞቱ በፊት መድረስ አለብን። የገርማል የሳት ለጂ አመድ እንዲሉ።እንዴው ወያኔ ወንድ ሆኖ ይሆን እዲህ የሚሆነው? ወይንስ እኛነን እድሜውን ምናራዝመው?<ዋና ጠላታችን ህወአት (የትግራይ ነፃ አውጭ!)ይሁን እንጂ ተተኪው አጥፊያችን የብሔር ብሔረሰብ ካድሬ ሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የከተማ አሸባሪ ሆኗል። ግን ነፃ ልንወጣ የነበረው ከማን ነበር? ለምን ነበር?ነጻነት ፈላጊ ጭቆና ያሰፍናልን? ሀገር ያጠፋል? ሕዝብ ያዋርዳል? ታሪክ ያበላሻልን? የሀገር ሉዓላዊነትን ያመክናል? በግለሰብ ራዕይ ሀገር ሸጦ፣ ሕዝብ አፈናቅሎ፣ወጣት አሰድዶ፣ጋዜጠኛ አስሮና ገርፎ ፣ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ የሚገድል፣የመጨረሻው መጨረሻ ቅኝ ግዛት፣ የባዕዳን ተልእኮ አስፈፃሚ፣ባንዳ፣ሊሆን ይሆን?
ሃይማኖት ካላቸው.. በእምነታቸው!ሕግ ካለ.. በሕግ አምላክ! ሰው ከሆኑ..ስለሰው ልጅ… ብለን ወይም በሚፈልጉት ትግል ታግለን ልንጥላቸው ይገባል።

Advertisements

Posted on November 23, 2013, in Andinet party, ETHIOPIA ENGLISH, Ginbot 7, OLF and tagged . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: