የአና ጐሜዝና የኢህአዴግን “ፍቅር” እንመነው እንዴ?

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ..

anagomez

“ወሬኛም ያውራ ሃሜት ይደርድር
እኛስ ሆነናል ፍቅር በፍቅር
ሊያፈርስ አስቦ የሸረበውን
ተክቦ ሆኗል የሚያገኘው…”

ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!

አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡
እንዴ … የ97 ምርጫ ጊዜ አና ጐሜዝ በኢህደዴግ ላይ የሰነዘረችው ትችትና ነቀፌታ “ዓይንሽ ላፈር” የሚያስብል ነበር እኮ! እናም ኢህአዴግ “ዓይንሽ ላፈር” ብሏት ነበር፡፡ (በዓይኑ መጣቻ!)
ጊዜ ደጉ ግን ሁሉንም ገለባበጠው፡፡ በነገራችሁ ላይ በጐሜዝና በአፈጉባኤው ተቃቅፎ ፎቶ መነሳት መደንገጤ ሊገርማችሁ አይገባም፡፡ ለምን መሰላችሁ … ራሷ አና ጐሜዝም ብትሆን በአዲስ አበባ በሚካሄደው 26ኛው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክ አገራትና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ በሚያደርጉት የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት “ቪዛ አይሰጠኝም” የሚል ስጋት እንደነበራት ከእንግሊዝኛው ሪፖርተር ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልፃለች፡፡
እኔ የምለው ግን … አፈጉባኤው ከጐሜዝ ጋር ያወረዱት ሰላም በግል ነው ወይስ ፓርቲውን ወክለው? (ብዥታው ይጥራ ብዬ እኮ ነው!) በነገራችሁ ላይ እርቁና ሰላሙ ከአንገት በላይ ቢሆን እንኳን፣ ኢህአዴግ ስሙን በከባዱ ያደሰበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡ እስቲ አስቡት … በ97 ምርጫ ለተቃዋሚዎች “ተደርባ አሳቅላናለች” በሚል ኩርፊያ፣ ዛሬ በ2006 ይከናወን በነበረ ትልቅ የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቪዛ ቢከለክል ኖሮ እንዴት embarassing እንደሚሆን? (“ተጠቃሽ የአገር ገፅ ግንባታ” ብየዋለሁ!) እንዲያም ሆኖ ግን “ቂመኛ ነው” የሚባለው አውራው ፓርቲ፤ እንዴት ለአና ጐሜዝ “አንጀተ ቀጭን” (ርህሩህ ለማለት ነው!) ሆነላት? የሚለው ጥያቄ አሁንም ከልቤ አልወጣም። (ሴቲቱ ቆቅ ሳትሆን አትቀርም!) ይገርማል እኮ! እዚህ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች ከ97ቱ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ እርቅ ሳያወርዱ እንደተፋጠጡ አሉት፡፡ (አሁንም ድመትና አይጥ ናቸው እኮ!)
እኔ የምለው … ፎቶውን ትክ ብላችሁ ስታዩት ግን “ፍቅራቸው” ወይም የወረደው ሰላም የምር ይመስላል እንዴ? (የጐሜዝና የአፈጉባኤውን ማለቴ ነው!) እኔማ “እንዳንቺ አይደለንም!”፣ “ይብላኝ ላንቺ”፣ “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጐዳም” የሚል መልዕክት ኢህአዴግን ከወከሉት ሰውዬ ሳቅ ውስጥ የማነብ እየመሰለኝ ተቸግሬ ሰነበትኩላችሁ በነገራችሁ ላይ … የሁለቱን የፓርላማ ሰዎች የሳቅ ትርጉም በትክክል የገመተ ይሸለማል (በአውሮፓ ህብረት ስፖንሰር አድራጊነት!)
እናላችሁ … አና ጐሜዝ ከጉባኤው በኋላ በቤተመንግስት እራት ከመጋበዟም ባሻገር ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ዙሪያ መወያየቷን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፃለች። እንደውም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሃሳቧን ለመስማት ፈቃደኛ መሆናቸው ራሱ አስደንቋታል (“ምን ደግሰውልኝ ይሆን?” አለማለቷ ይገርማል!) እንዲህ ብላ ብቻ ግን አታበቃም – “ቅመሟ ጐሜዝ”! ከ97 ምርጫ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበና ዲሞክራሲው እየቀጨጨ መጥቷል ብላለች-በይፋ። በመጨረሻም በሽብርተኝነት ተፈርዶባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም መፈታት አለባቸው ያለችው ጐሜዝ፤ “የፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ዲሞክራሲን ለማቀጨጭ እየዋለ ነው” በማለት በድፍረት ተናግራ ወደ አገሯ ተፈተለከች፡፡ (እኛም እኮ ሌላ አገር ቢኖረን…)
እኔ የምላችሁ … የመስቀል በዓል በዩኔስኮ ስሙ መስፈሩን ሰማችሁ አይደል? የኢቴቪ “አለርጂክ” አለብን የምትሉ የዲሽ ወዳጆችም ብትሆኑ፣ ከሌሎች ሚዲያዎች ሳትሰሙት እንደማትቀሩ እገምታለሁ፡፡ “የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ” በሚል ዘርፍ ነው “መስቀል” የተመዘገበው ተብሏል፡፡ (ኩራት ቢጤ ተሰማኝ!) እንደሰማነው ከሆነ ታዲያ … መስቀል በቅርስነት መስፈሩ ወደ አገራችን የሚመጡ ቱሪስቶችንና ተመራማሪዎችን ቁጥር ያበራክታል ተብሏል፡፡ (ይሄማ ምን ያጠራጥራል!) የእኔ ጥርጣሬ ምን መሰላችሁ? እንግዶቹ የጠበቁትን መስተንግዶና አገልግሎት አግኝተው፣ ሳይቀየሙን፣ በሰላም ወደ አገራቸው ይሸኛሉ ወይ የሚለው ነው፡፡ ከምሬ ነው … ያማሩ የሆቴል ህንፃዎች እኮ መስተንግዶ አይሆኑም! (ብቁ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ ለማለት ነው!) ለመግባባት በቂ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው፣ ከሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ጋር በቅጡ የተዋወቁ የሆቴል ባለሙያዎች፣ አስጐብኚ ድርጅቶች ወዘተ … የግድ ነው፡፡ ያለዚያ የአገር ገፅ ግንባታው የአገር ገፅ እንዳያፈርስ ያሰጋል፡፡ (“አፍሶ መልቀም” አሉ!) የኢቴቪ ጋዜጠኞችም የመጣው ቱሪስት ሁሉ “Ethiopia is an amazing country; its people, its culture …፣” ወዘተ እንዲል መጠበቅ የለባቸውም፡፡ የቱሪስቶች ቁጥር የማይጨምረው ምናልባት የኢቴቪ ኢንተርቪው እያጨናነቃቸው ቢሆንስ? (ገራገር ግምት ናት!)
እናላችሁ … በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ስለሰፈረው የመስቀል በዓላችን እያብሰላሰልኩ ሳለ ድንገተኛ ሃሳብ ከአዕምሮዬ ተገፍትሮ ሲወጣ ተሰማኝ፡፡ ወዲያው ጅራቱን አንቄ ያዝኩት፡፡ ሃሳቡ እንግዳ ቢመስልም ክፋት ግን የለውም፡፡ ምን መሰላችሁ? ዲሞክራሲ ባህላችንን ለምን “ከማይዳሰስ ዘመናዊ” ቅርስነት” በዩኔስኮ አናስመዘገበው? … የሚል ነው፡፡
(“አና ጐሜዝ ዲሞክራሲያችሁ ቀጭጯል” የምትለውን መርሳት ነው!) በዚያ ላይ “democracy is a process” (በኢህአዴግ ቋንቋ “እየወደቅን እየተነሳን ነው”) የሚል አባባል አለ አይደል? እናላችሁ … አል ስሚዝ የተባሉ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ምን ይላሉ መሰላችሁ – ስለ ዲሞክራሲ፡፡ “የዲሞክራሲ ህፀፆች የሚታከሙት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው” (የ“ተማረ ይግደለኝ” ሳይሆን “በደንብ ያስተምረኝ” አልኩኛ!) ለእኛ አገር ቀረብ የሚል የመሰለኝን ደግሞ እነሆ – “ልማት ዲሞክራሲን ይፈልጋል፤ እውነተኛው የህዝብ ማሳተፍያ!” ይህን የተናገሩት ደግሞ የበርማ የፖለቲካ መሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡
እናንተ … ለካስ ኢህአዴግ “ዲሞክራሲ ለእኛ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው” የሚለው ወዶ አይደለም፡፡ (ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ተቦክቶ የሚጋገር ሳይሆን ሂደት መሆኑን ግን አትርሱ!) እኔ የምላችሁ … ግን ተቃውሞን አምርረው የሚጠሉ፣ ተቃዋሚዎችን እንዴት ብለን አይተን የሚሉ መንግስታትና ገዢ ፓርቲዎች እጅግ “ሰነፎች” አይመስሏችሁም?” “የለም፤ አምባገነኖች ናቸው እንጂ!” ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን ምን እላለሁ መሰላችሁ? የሚቀድመው ስንፍናቸው ነው! ከዚያ ነው አምባገነንነታቸው የሚከተለው፡፡
የምን ስንፍና መሰላችሁ? ለህዝብ ቅሬታ በቂ ጆሮና ተገቢውን ምላሽ ያለመስጠት ስንፍና!! የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮች በወቅቱ ያለመፍታት ስንፍና!! የስልጣን ኮርቻ ላይ ሲወጡ ለህዝብ የገቡትን ቃል ችላ የማለት ስንፍና!! የህዝብን መብትና ነፃነት በማን አለብኝነት የመደፍጠጥ ስንፍና!! ብዙ እንዲህ ያሉ … ስንፍናዎች ሲጠረቃቀሙ አምባገነንነት ይወለዳል ይላል-በልምድ ላይ የተመሰረተው ጥናቴ፡፡ በነገራችሁ ላይ … የህገመንግስት አንቀጽ ደልዞ ወይም የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ የስልጣን ዕድሜን ማራዘም የ“ሰነፍ መንግስታት” መገለጫ ነው፡፡ የሥልጣን ጥመኞች እኮ “ሰነፎች” ናቸው-ከቤተመንግስት ወጥተው ተራ ህይወት መኖር ሞት የሚሆንባቸው!! (ካላመናችሁኝ ራሳቸውን ጠይቋቸው!!) በመጨረሻ የዲሞክራሲ ዘብ ነኝ ለምትለው አና ጐሜዝና እጅ መጠምዘዝ አይቻልም ለሚሉት የፓርላማ አፈጉባኤ የንዋይ ደበበን ዘፈን ጋብዣቸው ልሰናበት፡፡

ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!

ኤልያስ
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ፡፡ አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡

Source/www.addisadmas.com

Advertisements

Posted on December 8, 2013, in Andinet, Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo and tagged , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: