የሰሜን ጎንደር የእስር ቤት አዛዥ ተገደሉ፡፡!!!!!!

የሰሜን ጎንደር የእስር ቤት አዛዥ ተገደሉ

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢዎች ከጎንደር እንደገለጹት ኮማንደር አለባቸው የተባሉት የሰሜን ጎንደር ዞን የወይኔ ቤት አዛዥ የተገደሉት ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ነው… ኮማንደሩ በጥይት መመታታቸው ቢገለጽም ዘጋቢያችን ማን እንደገደላቸው ለማወቅ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። የግለሰቡ አስከሬን ወደ ተወለዱበት በየዳ ወረዳ መላኩ ታውቋል

አወጋን እየተባለ የሚጠራው ድርጅት ግድያውን መፈጸሙን ገልጿል። ድርጅቱ በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ባወጣው መረጃ ” የሰሜን ጎንደር የማረሚያ ቤት ሀላፊ ኮማንደር መተከል አያልሰዉ እርምጃ ተወሰደበት ” ብሎአል:: አርምጃዉ የተወሰደዉ ትናት ማታ ሰባት ሰአት ሲሆን በተደጋጋሚ ከግፍ ስራዉ እንዲቆጠብ መልክት ቢደረሰዉም አሻፈረኝ በማለቱ ተገድሏል ” ብሎአል።

የኢሳት ዘጋቢዎች ሟቹን ኮማንደር አለባቸው ሲሉት አወጋን ደግሞ ኮማንደር መተከል ብሎታል። በጉዳዩ ላይ የሰሜን ጎንደር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊን ለማነጋገር ሙከራ ብናድርግም አልተሳካልንም።

Advertisements

Posted on January 11, 2014, in Andinet, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: