የህወሃት ኤፈርት ባለስልጣኖች ወደ ውጪ ሀገር በመሄድ የንግድ ድርጅት በግለሰብ ደረጃ እየገዙ ነው ተባለ

(አባይ ሚዲያ) የኢትዮጵያ መንግስት የሆነው ህወሃት በሀገራችን ሰላምና ፍትህ፣ ልማትና እድገት እየመጣ ነው እያለ የተረጋጋ መሆኑን በማስመሰል በየጊዜው ይናገራል። ነገርግን የሀገሪቱን ገንዘብ በተዘዋዋሪ በውጪ በሚኖሩ የስርአቱ አግልጋዮች ስም የቦታና የንግድ ግዢ በውጪ ሀገር የማድረግ ስራ በሰፊው እየተፋፈመ መሆኑን የውስጥ ዜና ምንጮቻችን ገልፀዋል… በተለይም በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች በጉብኝት ስም ታማኝ ሰዎችን በመላክ የሀገሪቱን ገንዘብ በማሸሽ ቦታና የንግድ ማእከሎችን እንዲገዙ እየተደረገ ነው። ህወሃት ራሱ ያልተረጋጋ እና አደጋ ያንጃበበት በመሆኑ ውስጣቸው መረጋጋት እንደሌለበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ታዲያ ይህንን ፍርሃት በመሸፈን በበላይነት የህወሃት ኤፈርት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን ገንዘብ የማሸሽን ዘዴ እንደ አንድ አማራጪ ወስደው ራሳቸውንና ንብረታቸውን ለማሸሽ እየተዘጋጁ ነው ሲል መረጃውን የላከልን ዘጋቢያችን አስታውቋል። በቅርቡ ከሁለት ወር በፊት የኤፈርት ልኡክ ቡድን ወደ አሜሪካ ተልእኮ እንደነበርም አስረድቷል። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የህወሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው ሲል የግንቦት 7 ሬዲዮ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።

Advertisements

Posted on January 15, 2014, in Andinet, Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: