አርሶ አደሩን እንደፈለገ ብናደርገው በኢህአዴግ ላይ አይነሳም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

ኢሳት ዜና :- የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ለመንግስት ሚኒስትሮችና ለከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች በተዘጋጀው የምርጫ ውይይትና ግምገማ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ እንደገለጹት አርሶ አደሩ እስካሁን በተሰረላት ስራ በመርካቱ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል….፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አርሶአደሩ ይህን መንግስት ምንም

አይለውም፣ ይሸከመዋል” ብለዋል።  30 በመቶ የሚሆነውን ወጪ የምንሸፍነው በውጭ እርዳታ በመሆኑ፣ ከውጭ ተጽእኖ ለመላቀቅ ወጪያችንን የሚሸፍን ገቢ ማግኘት አለብን ያሉት አቶ በረከት፣ “በ1997 ምርጫ ወቅት የውጭ ሃይሎች ጥፋት ያጠፉትን መሪዎችን ወደ ፍርድ ቤት የምትወስዱዋቸው ከሆነ እርዳታ እናቆማለን ባሉት መሰረት እርዳታ አቁመውብን ነበር” ሲሉ ለራሳቸው ባለስልጣኖች ተናግረዋል።

አቶ በረከት ”በ1884ቱ ድርቅ ጊዜ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ሃላፊው የመሬት ፖሊሲያችሁን ካልቀየራችሁ እርዳታ አንሰጥም” ብለዋቸው እንደነበር ተናግረዋል።

ኢህአዴግ ከዋናዎቹ አመራሮች ጀምሮ በተዋረድ ለሌሎች አመራሮችም ምርጫውን ስለሚያሸንፉበት ሁኔታ ስልጠና እየሰጠ ነው። ኢህአዴግ የገጠሩን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እንደሚያገኝ አቶ በረከትና ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ ተማምነዋል። ይሁን እንጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች በየገጠሩ በመዞር ያልተደራጀውን አርሶአደር በአንድ ለአምስት በማደራጀት፣ በመሬት እጥረት የተከፋውን ወጣት የወል መሬት እየሸነሸኑ በመስጠት ላይ መሰማራታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Posted on January 16, 2014, in Andinet party, ETHIOPIA ENGLISH, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: