እነ አንዷለም አራጌ ነገ ሰበር ሰሚ ችሎት ይቀርባሉ፤ ሕዝብ ችሎቱን እንዲከታተል ጥሪ ቀረበ፤

andualem-arage[1]

አንባቢዎች ዘንድ የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚለውን ስያሜ ያገኘው የሕሊና እስረኛው አንዷዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንንና ክንፈ ሚካኤል ደበበ ነገ ጥር 16 ቀን 2006 (ጃንዋሪ 24 ቀን 2014) በሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርቡ ከቤተሰቦቻቸው አካባቢ የተገኘው መረጃ አመለከተ… እነዚህን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚፈልጉ ወገኖች 6 ኪሎ የሚገኘው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

በአንካሳው የኢትዮጵያ የሽብር ሕግ ከግንቦት 7 ጋር በማያያዝ ሽብር ለመፈጸም በማቀድ በሚል እድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷአለም አራጌ በእስር ቤት በመሆንም በጽናት በመታገል የሰላማዊ ትግል አርማ ሆኗል በሚል በብዙዎች ዘንድ ይወደሳል። ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷዓለም አራጌ የተላለፈበትን ዕድሜ ልክ እስራት ፍርድ፤ እንዲሁም ናትናኤል መኮንን እና ክንፈሚካኤል ደበበ የተላለፈባቸውን ቅጣት ለታሪክ ለመተው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲታይ የወሰዱት ሲሆን ነገ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሚሰጠው ውሳኔም በቤተሰቦቻቸው ዘንድ በትልቅ ተስፋ እንደሚጠበቅ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ነገ በስድስት ኪሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ሲሰየም እነ አንዷለም አራጌም አብረው የሚቀርቡ ሲሆን የሚታገሉለትና መስዋዕትነት እየከፈሉለት የሚገኘው ሕዝብ በችሎቱ በመገኘት ይህን «ፍትህ የምትዋረድበትን
ወይም ፍትህ የምትታይበትን» ታሪካዊ ቀን እንዲመለከት ከቤተሰቦቻቸው እና ከወዳጆቻቸው ጥሪ ቀርቧል። ይህን ተከትሎም በፌስቡክና በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች «እነ አንዷለም ፍትህ ያግኙ፤ ይፈቱ» የሚለው ቅስቀሳ ቀጥሏል።

Advertisements

Posted on January 24, 2014, in Andinet, Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: