ይግባኝ ተጠይቆባቸው ከነበሩት 6ሙስሊሞች መካከል የ2ቱን ይግባኝ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገው

በዛሬው ዕለት አቃቤ ህጉ ይግባኝ ጠይቆባቸው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ከነበሩት 6 ሙስሊሞች መካከል የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል በሆኑት ኡስታዝ ጀማል ያሲን እና በ ኡስታዝ ሃሰን አሊ ላይ አቃቤ ህጉ አቅርቦት የነበረውን የይግባኝ ጥያቄ ማንሳቱ አስታውቋል…

በተቀሩት ላይ ግን ይግባኙን ያፀና ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ለማየት ለየካቲት 20 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በታህሳስ 3 ቀን የፌደራሉ ከፍተኛው ፍረድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት በኮሚቴዎቻችን እና በወንድሞቻችን ላይ የጥፋተኝነት ብያኔ ማስተላለፉ እና 10 የሚጠጉትን ደግሞ በነፃ እንዲፈቱ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡
ይህንንም ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ህጉ በ 6ቱ ላይ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን በመጀመርያው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ይግባኝ የተጠቀባቸው 6ቱም ሙስሊሞቸ መጥሪያ አልደረሳቸውመ በሚል ፍርድ ቤት ሳይገኙ በመቅረታቸው ፍርድ ቤቱ ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 19 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚህም ቀነ ቀጠሮ መሰረት ጉዳዩን የተመለከተው 6 ኪሎ መነን አካባቢ የሚገኘው ፍርድ ቤት ይግባኙን በመመርመር በ 2 ሙስሊሞች ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ ያደረገ ሲሆን በተቀሩት 4 ሙስሊሞች ላይ ግን ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ለየካቲት 20 መስጠቱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል በሆኑት በኡስታዝ ጀማል ያሲን እና በ ኡስታዝ ሃሰን አሊ ላይ አቃቤ ህጉ ያቀረበውን ይግባኝ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው ሲሆን በተቀሩት በሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣በሼህ አብዱራህማን፣በወንድም አሊ መኪ እና በወ/ሮ ሃባ መሃመድ ላይ ቀረበውን ይግባኝ ለመመርመር ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ለየካቲት 20 መስጠቱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ይግባኙ ውድቅ የተደረገላቸው
1.የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኡስታዝ ጀማል ያሲን
2. ኢስታዝ ሃሰን አሊ
ለየካቲት 20 ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ የተሰጣቸው
1. በሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ
2. በሼህ አብዱራህማን፣
3. በወንድም አሊ መኪ እና
4. በወ/ሮ ሃባ መሃመድ ናቸው
በተያያዘም ዜና ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላለፈባቸው የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እና የተቀሩት ወንድሞች ከ 3 ቀናት ቡሃላ በጥር 22 ፍርድ ቤት በመቅረብ የመከላከያ ምስክራቸውን ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ እንደሚጀምሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አላህ ፍትህን ያስፍንላቸው!!!
Advertisements

Posted on January 27, 2014, in Andinet, Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: