መንግስታት ፈለጉት ኣልፈለጉት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለወደፊት ትውልዶች የሚቀጥል የመዋሃድ ዝምድና መኖር ኣለበት” ኢሳያስ ኣፈወርቂ

ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ
ከኣሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ ያማርኛው ክፍል ከጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ  ጋዜጠኛ ኣዲሱ ኣበበ፥ እየተገባደደ የነበረውን የኣውሮጳውያን የ1992 ዓ.ም. ምክንያት በማድረግ በተገባደደው ዓመት  ከተከስቱ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹን ሲያስተናግድ፤ “1993 ዓ.ም. ላይ ደርሰናል፤ እንደ ኣውሮጳ ኣቆጣጠር… ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ስለ
ኤርትራ ሬፈረንደም፥ ማለትም ህዝበ ውሳኔ፥ ይህን ብለው ነበር።” በሚል መክፈቻ የስራ ባልደረባው የሆነቺው ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ  ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር ቀደም ሲል በድምፅ ያደረገችውን ቃለመጠይቅ ይለቃል።  ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ፤  በግዴታም ይሁን በውዴታ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስስራ ቆይታለች። እና፥ እንግዲህ፥ የነፃነት ጥያቄ፥ የመገንጠል
ጥያቄ ከማን? የሚለው [መልሱ] ከኢትዮጵያ ነው። እንግዲህ፥ [ኤርትራ] ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስራ ስለቆየች። እና፥ ይህ የሬፈረንደሙ ነጥብ  ራሱ ምንድንነው የሚለው፤ “ነፃነት ትፈልጋለህ? ኣዎን ወይም ኣይደለም” ዓይነት ነው። እና፥ ለምንድነው እንደዛ የጠበበው? ትንሽ ሰፋ ብሎ  ወይም ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ኣንድነት ወይም ኮንፌደረሽን ወይም ፌደረሽን ወይም ሰፋ ያለ የራስ ገዝ ኣስተዳደር ወይንስ ነፃነት ነው  የምትመርጠው? በሚል ሰፋ ባለ ይዘት ለምን ኣልቀረበም?
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፤  በመጀመሪያ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እየተገነጠለች ነው የሚለውን ጥያቄ እኛ በበኩላችን ከመጀመሪያውም  ኣልተቀበልነውም። የምንቀበለው ነገርም ኣይደለም። በኛ ኣስተያየት ጥያቄው ምንደንነው? ህጋዊ ያልሆነ ጋብቻ ወደ ፍች በሚያመራበት  ወቅት ወደ ህግ መልሶ ለማረጋገጥ የሚቻል ኣይመስለኝም። የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ስለመዋሃዱ ጉዳይ በህጋዊ መንገድ የተደረገ
ኣልነበረም። ስለዚህ ለኤርትራዊያን የሚቀርበው ጥያቄ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ትፈልጋለህ? ወይንም ኣትፈልግም? የሚል ሳይሆን፥ ነፃ ኣገር  እንድትሆን ትፈልጋለህ? ኣትፈልግም? የሚለው መሆኑ ባህሪያዊ የሆነ ነገር ይመስለኛል። ይህ ማለት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ትጠላዋለህ፥  ኣትወደውም፥ ከኢትዮጵያ ጋር ዝምድና የለህም፥ ኣይኖርህምም ማለት ኣይደለም።
ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ፤  ያኔ፥ ጋዜጣዊ መግለጫ በተደረገበት ጊዜ፥ የኤርትራ ህዝብ ወይም መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የኤኮኖሚ ውህደት ወይም
ኢንቲግሬሽን እንደሚፈልግ፥ ከዛም ኣልፎ እንዳውም እስከ በኮንፌደርሽን የመዋሃድ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ጠቅሰው ነበረ። እና ይህ  ኣባባል ምን ያህል እውነትነት ኣለው? ምን ያህልስ የሚገፋበት ነገር ይመስለዎታል?
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፤  ከዚያም በኋላ ደጋግሜ እንደገለፅኩት ሁሉ፥ ጥያቄው ስለቀረበ፥ ለረጅም ጊዜ በቆየው ኣመለካከታችን መሰረት  በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለያድግ ስለሚችል ዝምድና በሚመለከት ጭንቅላታችን ምን ጊዜም ቢሆን ክፍት ነው። በኤርትራና  በኢትዮጵያ መካከል ሊኖር ስለሚችል ማንኛውም ዓይነት ገንቢ መረዳዳት ገደብ የሚደረግበት ነገር ኣይሆንም። በኮንፌደረሽን መዋሃድ
የሚፈለግ ከሆነ፥ ለምን ኣይሆንም እንላለን። መንግስታት ፈለጉት ኣልፈለጉት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለወደፊት ትውልዶች  የሚቀጥል የመዋሃድ ዝምድና መኖር ኣለበት። በፍላጎትና በምኞት ላይ ብቻ ሳንወሰን በተጨባጭ ወደ መዋሃድ ወደሚያመሩን እቅዶች  መግባት ኣለብን። እንዲህ ሲባልም ምንልባት ኣንዳንዶቹ፥ እነዚህ ችጋራሞች የሚበላና የሚጠጣ ስለሌላቸው ሊጠቀሙብን ፈልገው ነው
ኣሁን ውህደት የሚሉት፤ ለጥቅማቸው ሲሉ ነው፤ ይሉ ይሆናል። ይህ ግን ገንቢ ኣይሆንም።”
ታሪካዊ ምክንያቶች በመነሳት የኢትዮጵያና  የኤርትራ ህዝብ ኣንድነት ከራሳችን ኣልፎ ለኣካባቢያችንና ለመላው ኣፍሪካ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በውል በመገንዘብ  የኢትዮጵያና የኤርትራ ፌደራላዊ ኣስተዳደር እንድንመሰርት ያለንን ፍላጎት ቀደም ኣድርገን ለወያነ መንግስት ኣቅርበናል። የወያነ  መንግስት በማናውቀው ምክንያት ሃሳባችንን ካለመቀበሉም ሌላ ይህንን ሃሳብ ካቀረብንበት ጊዜ ኣንስቶ በሁለቱም ኣገሮች  ለነበረው መልካም ግኑኝነት ሳንካ ለመፍጠር እንደተንቀሳቀሰ ኣስተውለናል። ለወደፊትም ቢሆን ስርዓት በተከተለና ኣግባብ
ባለው መንገድ ከህዝባችን ጋር መክረን በህዝባችን ፍላጎትና ውሳኔ ተመስርተን ይህንኑ ሃሳብ የምናራምድ መሆናችንን
ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።  በብሄር ከተደራጁ ድርጅቶች ብቻ ግንኙነት ታደርጋላችሁ ለተባለው ቅስቀሳው የወያነ ቅስቀሳ ከመሆኑ ባሻገር ትክክለኛ መረጃ  ኣይደለም። እኛ የምናደርገው ግንኙነት ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በብሄርም ሆነ በህብረ-ብሄራት ከተደራጁ ድርጅቶች ጋር  እንደሆነ ለማንም ግልፅ ሊሆንለት ይገባል። ከዚህ ውጭ ኣንተ በብሄር ኣንተ ደግሞ በህብረ-ብሄር ተደራጅ እያልን መመሪያ
የመስጠት መብት የለንም። ድርጅቶች በህብረት እንዲሰሩ ለማድረግ ሙሉ ፍላጎታችን ቢሆንም እጅ ኣየጠመዘዝን ድርጅቶችን  እንዲያብሩ ማድረግ ግን በድርጅቶቹ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ከመሆኑም በላይ ስራው የኢትዮጵያዊያኖች እንጂ የኛ ሊሆን  11  ኣይገባም። የኛ ዕቅድና ፍላጎት ኢትዮጵያን ለመበተን ቢሆን ኖሮ በደርግ ውድቀት ማግስት ልናደርገው እንችል ነበር።
የተበታታነች ኢትዮጵያ ደግሞ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለኛም ጠንቅ እንድምትሆን ኣጠያያቂ ኣይደለም። እኛ ግን በተቃራኒው  በሽግግሩ ጊዜ በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዲሰፍን ያበረከትነው ኣስተዋፅኦ ወዳጅም ጠላትም በሚገባ ያውቀዋል። በኢትዮጵያ  መበታተን የኤርትራ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል ብሎ የሚያስብ ካለ የታመመ ሰው ብቻ መሆን ኣለበት። ስለዚህ ወያነ ለራሱ  ህልውና ሲል የሚለፍፈውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ከመሆን በመታቀብ ታጋይ ኢትዮጵያዊያንና ባጠቃልዩም የኢትዮጵያ  ህዝብ የኤርትራ ችግር የተከሰተበትን ምክንያትና ለሰላሳ ዓመታት ያህል የተካሄደው ትግል ምንነት በማጤን ሁላችንም
ከስህተቶቻችን ተምረን ስህተቶች እንዳይደገሙ በውይይትና በመግባባት ህዝባችንን ለተሻለ ህይወት ለማብቃት ከመታገል ሌላ
ኣማራጭ የሌለን መሆኑን ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል።  በኢትዮጵያ ውስጥ ኣሳሳቢ ችግር ያለ መሆኑን እንገነዘባለን። ችግሩን በሚገባ ተረድቶ ዘላቂ መፍትሄ መሻት ደግሞ የሁላችን
ተሳትፎ እንደሚጠይቅ እናምንበታለን። ኣሁን የገባንበት የኢትዮጵያና የኤርትራ ችግር በኣንድ ተጨባጭ ፎርሙላ ማስተካከል  ከተቻለ ደግሞ ሌላው የውስጥ ችግር ህይወት ኖሮት ሊቀጥል ስለማይችል ወዲያውኑ እንደሚፈታ ለመገንዘብ ኣስቸጋሪ  ኣይደለም። ስለሆነም ችግሩ በተናጠል የኢትዮጵያ የውስጥ ችግር ተብሎ የሚቀርብ ሳይሆን የጋራ ችግር መሆኑን ተረድተን መፍትሄውን በጋራ ለማስገኘት በኤርትራ መንግስትና ህዝብ በኩል ይህ ቀረው የማይባል ትብብር እንዳለና ለወደፊቱም በዚሁ
እንደሚቀጥል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

Advertisements

Posted on January 29, 2014, in Andinet, Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: