ኢህአዴግ ልብ ቢኖራት ፕሮፍን ተንበርክካ ይቅርታ በጠየቀቻቸው፤

379831_654719927888342_925324696_nከሰሞኑን መነጋገሪያ ጉዳዮች አንዱ ለሱዳን ተሰጠ የተባለው መሬት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ከመሰንበታቸውም በላይ ሰማያዊ ፓርቲ ይሄንኑ የሚያወግዝ ተቃውሞ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ለጥር 25 ጠርቷል… በነገራችን ላይ ስለ ሰማያዊ ፓርቲም ሆነ ስለ ሌሎቹ ተቃዋሚዎቻችችን ምርጫው ጨክኖ ከመምጣቱ በፊት የሆነ ቀን በፌስ ቡክ ዙሪያ ቁጭ ብለን በቅጡ መነጋገር ያለብን ይመስለኛል፡፡ መገማገም ይሉታል እነ እንትና!

የሆነው ሆኖ ኢህአዴግዬ ሰጠች ስለተባለው መሬት ማብራሪያ እንዲሰጡ ሰማያዊዎቹ በጠሩት ስብሰባ ላይ የተገኙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪም፡፡ ኢህአዴግ መሬቱን ለሱዳን መስጠቷን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ የለም ካለ፤ ይሄ መሬት ተሰጥቷል ብላችሁ እስቲ በካርታ ላይ አሳዩን ብለው ሰማያዊዎቹን ሞገቷቸው፡፡ አክለውም ይሄ ጉዳይ ለበርካታ ጊዜያት ሲያጨቃጭቅ መቆየቱን እና ጥርት ያለ ምላሽ እንዲገኝለት ጥርት ያለ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል ለዚህም ማንም ሳይሆን ራሳችን ሃላፊነት መውሰድ አለብን አሉ…

ፕሮፌሰር መስፍን ማለት እንግዲህ እንዲህ ናቸው፡፡ ኢህአዴግዬ (እርሳቸው ወያኔ ይሏታል) “የጭፍን ጥላቻ ፖለቲከኛ” ከሚለው አንስቶ  የማትላቸው ነገር፣ የማትሰጣቸው ስም የለም፡፡ እርሳቸው ግን ሁላችንም ከምንላቸው በላይ ናቸው፡፡ በተለይ ኢህአዴግን ይከብዷታል! ኢህአዴግ ልብ ቢኖራት የፕሮፍን ነገረ ስራ ጥሞና ሰጥታ በመከታተል እግራቸው ስር ተንበርክካ ይቅርታ መጠየቅ ከዛም ወፈር ወፈር ባሉ ጉዳዮች ላይ እንደ ሱዳን ድንበር እንደ አባይ ግድብ የመሳሰሉት ላይ ምን ይበጃል ብላ ብታማክራቸው ለራሷም ለእኛም ጥቅም ነበር፡፡ (እኛ ተብሎ የተጠቀስነው ሰፊው ህዝብ ነው)

ፕሮፍ ብዙ ብዙ ያኑሮት!

Advertisements

Posted on January 31, 2014, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: