መንግስት አሁንም ሀይሉን አጠናክሮ በሙስሊሙ ላይ ሌላ አዲስ ዘመቻ ሊከፍት እንደሆነ የፍትህ ሬዲዩ ምንጮች አስታወቁ፡፡

መንግስት አሁንም ሀይሉን አጠናክሮ በሙስሊሙ ላይ ሌላ አዲስ ዘመቻ ሊከፍት እንደሆነ የፍትህ ሬዲዩ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ለሶስት ቀን የሚቆይ ስልጠና ከትናንት ጀመሮ በሚኒስትር መ/ቤት ደረጃ መጀመሩ ተገለፇል …
ከባለፈዉ ሶስት ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች በሚገኙ የሚገኙ የክፍለ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ፣ አ.አ ፀጥታ ቢሮ፤ የአ.አ ፍትህ ቢሮ እና የአ.አ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በእስልምናና በሙስሊሙ ላይ አዲስ ዘመቻ ሊከፍቱ እንደሆነ ታውቋል ፡፡ ይህን በማስመልከትም በከፍተኛ የኢሃዴግ አመራሮች አማካኝነት በስልጠና መልክ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ተመልክቷል ፡፡ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለማወቅ እንደተቻለው ስልጠናው እንደ ዋና አላማ አድርጎ የተነሳው የተጀመረው የመስጂድ ነጠቃ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታና እስከዛሬ በተደረገው የመስጂድ ንጥቂያ የተገኙ ውጤቶችን መገምገም ፣ መስጂድ ነጠቃውንም ሆነ ሌሎች መንግስታዊ እርምጃዎችን ተከትሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከዚህ በኋላ ለሚያሰማው ህዝባዊ ቁጣ የመንግስት ሃላፊዎች ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው አቅጣጫ የሚያመለክቱ እንሆነ ታውቋል ፡፡ እነኚህን እቅዶች ለማሳካትም ከወረዳ ጀምሮ ለሚገኙ የአህባሽ መስጅሊስ አባላትን ደሞዝ በመጨመርና እስከዛሬ ለነሱ አላማ ተፈፃሚነት እንቅፋት ሆነው ነበር ያሏቸውን የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት በግምገማ መልክ በማባረር መዋቅሩን በአዲስ መልክ ለማጠናከር እንዳሰቡ አብሮ የወጣው መረጃ ያመለክታል ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ተሞክሮ የከሸፈዉ የወጣት ሴትና ወንድ አህባሾች ፤የአረጋዉያን እንዲሁም የአህባሽ ሱፊማህበር በአዲስ መልክ እንዲንቀሳቀስ እያደረጉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎል፡፡ የደመወዝ ጭማሪውና አደረጃጀቶቹን የማጠናከሩ እቅዶቹ የተፈለጉበት አላማም መንግስት ከዚህ በኋላ ለሚያካሂደው መስጂድ ነጠቃም ሆነ ሙስሊሞችን የመጨቆን እርምጃው ሙሉ ትብብር እንዲያደርጉለት እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት በኢትዮፕያዊያን ሙስሊሞች ላይ እያካሄደ ካለው በርካታ ጭቆናዎች በተጨማሪ የመስጅድ ነጠቃዉን ለማከናወን የሚከተሉትን አካሄዶች ነድፈዋል:- መነጠቅያለባቸዉን መስጅዶችን መለየት ፣ የየመስጅዶችን ኮሚቴዋች ፤ አሰጋጆችንና ሙኣዚኖችን በስም ዝርዝር መለየት ፡፡ መቀየር ያለባቸዉን የየመስጅዶችን ኮሚቴዋች፤ አሰጋጆችን ናሙኣዚኖችን በስም ዝርዝር መለየት ፡፡ በሚቀየሩት ሰዎች የሚተኩትን ኮሚቴዎች ፤ አሰጋጆችንና ሙኣዚኖችን መመልመል ና የመሳሰሉትን ተግባራት እንዲያከናዉኑ ለወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ፣ ለፀጥታ ጽ/ቤት ፣ ለወረዳ ኢህአዴግ ጽ/ቤትና ለወረዳ አህባሽ መስጅሊስ ተላልፈዋል፡፡ ይህ ሁሉ ከተከናወነ በሃላ በአጭር ጊዜ ወረራ መስጅዶቸን እንነጥቃለን የሚል አጀንዳ እንዳወጡ ምንጫችን ገልጠዋል፡፡ ስለሆነም ሙስሊሙ ማህበለሰብ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ራሱን በከፍተኛ መልኩ አደራጅቶ ለአንዴና ለመጨለሻ ጊዜ ለሚደረገው እጅግ መራራ ትግል ለማድረግ መዘጋጀት እንዳለበት አለበት የውስጥ ምንጮቹ ለፍትህ ሬዲዮ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል ፡፡

Advertisements

Posted on February 2, 2014, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: