“አርከበ የባቡር ሃዲድ ኮርፖሬሽን ስራ አስከያጅ ሆነ”

“አርከበ የባቡር ሃዲድ ኮርፖሬሽን ስራ አስከያጅ ሆነ” የሚል መልእክት ደረሰኝ። እንዳዉም አቶ ስብሃት ነጋና አቶ ቢተው በላይ ለሁለት ተከፍለው የነበሩትን የህወሓት አመራር አባላትን ካስታረቁ በኋላ አርከበና ስብሃት በህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እየተጋበዙ ይሳተፋሉ… አርከበ ዑቕባይ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ለማድረግ ሐሳብ ተነስቶ ነበር። ግን የማእከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ አባል አይደለም በሚል ሐሳቡ ዉድቅ ሆነዋል። ቀጥሎ ለትግራይ ርእሰ መስተዳደርነት የታጨው አቶ በየነ መክሩ ነበር። ግን አቶ አባይ ወልዱ ስልጣኑ ለበየነ መክሩ ለማስረከብ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርተዋል።

አሁን ህወሓቶች በአራት ጎራዎች ተከፍለው ይጨቃጨቃሉ። (ስለዚህ ጉዳይ ሌላ ግዜ እፅፋለሁ)። ካልተግባቡ አስቸኳይ ጉባኤ የመጥራት ሐሳብ አለ።

ስለዚህ አርከበ ብቻ አይደለም የተመለሰው። ከነስየ አብርሃና ገብሩ አስራት ጋ ከወሓት የወጣው ቢተው በላይም ወደ ህወሓት (በዕርቁ ሂደት) ተመልሶ ቁልፍ ስልጣን ይሰጠዋል። አርከበ ብቻ አይደለም ስልጣን የተሰጠው፤ አሜሪካ ገብቶ የነበረ የአርከበ ወንድም ጌታቸው ዑቅባይም ታርቆ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማናጀር ተደርጎ ተሹመዋል። ሌሎች አዳዲስ ገቢዎችም አዳዲስ ቁልፍ ስልጣኖች እያገኙ ነው። አርከበ በትግራይ ክልል ስልጣን ይሰጠዋል የሚል ግምት ነበረኝ። ግን አልሆነም።

አርከበ ከህወሓት ከወጣ በኋል ይዞት የነበረውን የሚኒስተር ዲኤታ ስልጣን ተነጥቆ ለሌላ ነበር የተሰጠው። አሁንም አልተመለሰለትም። ሌላ አዲስ ስልጣን ነው የተሰጠው። ምክንያቱም የድሮ ስልጣኑ ተቀምቷል።

It is so!!! Abraha Desta

Advertisements

Posted on February 11, 2014, in Andinet, Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: