Monthly Archives: April 2014

የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ከሕሊና እስረኞች ነጻ መሆን አለባቸው !

UDJ Headየኢህአዴግ ፖለቲካ ዜጎችን የማሰር፣ ዜጎችን የማሸበር ፖለቲክ ነው። በቅርቡ በዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የሚያሳየው፣ አገዛዙ ሃሳብን በሃሳብ መመከት ሲሳነው የሃይል እርምጃ ለመዉሰድ ወደ ኋላ የማይል መሆኑን ነው..

ኢሕአዴግ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ሳይሆን፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለማሸበር ሲል ያወጣዉ የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ በመጠየቅ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ማድረጉ ይታወሳል። በአገሪቷ ክፍሎች ያሉ ሚሊዮኖች፣ አገዛዙ ዜጎችን በማሸበር እንዲያቆም ቢጠይቁም፣ አገዛዙ፣ የሕዝብን ጥያቄ በመናቅ ፣ አሁንም ኢትዮጵያውያን እየታሰሩ ናቸው። አሁንም የግፍ ቀንበር በሕዝባችን ላይ እየተጨነ ነው።

የአንድነት አባላት፣ ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የማይታሰሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት፣ የታሰሩት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ለማድረግ ይታገላል። በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩ ወገኖቻችን፣ አገዛዙ እንደሚለው ሽብርተኞች ሳይሆኑ ፣ «ለመብታቸው፣ ለነጻነትናቸውና ለአገራቸው ክብርና አንድነት የቆሙ፣ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግኖች ናቸው» ብሎ ነው የሚያምነው።

የታሰሩ እስረኞችን ለማበረታታት፣ ለነርሱም መፈታት አንድነት ያለዉን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ከፍተኛ የአንድነት አመራር አባላት በሶስት እስር ቤቶች (ቃሊቲ፣ ቂሊንጦና ዝዋይ) አመርተው ነበር።

የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ አስቻለው እና አቶ አክሉ ግርግሬ በቃሊት እስክንደር ነጋ፣ ርዮት አለሙን እና አንዱዋለም አራጌን ለመጎነብኘት የሄዱ ሲሆን፣ ርዮት አለሙን እና እስክንደር ቢያገኙም አንድዋለምን ማነጋገር አትችሉም ተብለዉ ተመልሰዋል። ርዮት አለሙ፣ በአካል ጤንነቷ በጥሩ ሁኔታ ላይ ባይገኝም፣ በመንፈሷ ግን በጣም ትልቅ ጥንካሬ እንደሚታይበት ለማረጋገጥም ችለዋል።

በአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ፣ አቶ ስዩም ነገሻ የሚመራ ቡድን ደግሞ ወደ ቂሊንጦ እሥር ቤት ነበር ያመራው። ከአቶ ስዩም ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የነበሩ ሲሆን፣ በዚያም የታሰሩ ሰላማዊ የሙስሊም ችግር መፍተሄ አፍላላጊ ኮሚቴ አባላትን አግኝተው አነጋግረዋል።

የአንድነት ሁለቱ ሊቀመናብርት አቶ ተክሌ በቀለን እና አቶ በላይ በፍቅዱን፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራን፣ የሕዝብ ግንኙንተ ክፍል ሃላፊው አቶ ሃብታሙ አያሌውን፣ ደራሲና የአንድነት ደጋፊ አቶ አስራት አብርሃ ያቀፈ ወደ ሃያ የሚጠገ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ቡድን ፣ ወደ ዝዋይ በማምራት በዚያ ከሚገኙ በርካታ እስረኞች ጋር ሰፊ ዉይይት አድርጓል። ናትናኤል መኮንን፣ አንድዋለም አያሌው፣ ዉብሸት ታዬ፣ ጀነራል አሳምነው፣ ሻምበል የሺዋስ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ለሌሳ፣ አበበ ቀስቶ ..እንዲሁም በርካታ እስረኞች ለማነጋገር ተችሏል።

«እኛ በአካል ብንታሰርም፣ በመንፈሳችን ነጻ ሰዎች ነን። ነጻነት ያለ ትግል፣ ነጻነት ያለ ዋጋ አይገኝም። እኛ ዋና እየከፈልን ያለነው ለነጻነትና ለኢትዮጵያ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከፍርሃት፣ ከዝምታ፣ ከራስ ወዳድነት ተላቆ የድርሻዉን ለማበርከት ይዘጋጅ» ሲሉም፣ የሕሊና እስረኞች፣ ለኢትዮጵያውያን መልክት አስተላልፈዋል።

የአንድነት ፓርቲ የፊታችን ሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ የ«እሪታ ቀን» በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እንደጠራ ይታወቃል። በዚህ ሰልፍ ከዉሃ፣ መብራት፣ ትራንስፖርት ችግር በተጨማሪም፣ በቃሊቲ፣ በቂሊንጦና በዝዋይ ለታሰሩ ጀግኖቻችን፣ እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ የአገዛዙ የግፍ በትር ላረፈባቸውና በማእከላዊ ለሚገኙት ለዞን ዘጠኝ ወጣቶችና ጋዜጠኞች ያለንን አጋርነት የምንገልጽበት አጋጣሚ ተመቻችቷል።

ኑ ፣ እንነሳ ! ድምጻችንን እናሰማ ! የግፍ አገዛዝ በቃን እንበል ! ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን

Read the rest of this entry

Ethiopian Security Forces Open Fire on Students

There has been widespread protest by Oromo students in universities in Ethiopia against unpopular ‘Addis Ababa-Finfinnee surrounding integrated master plan’. Oromo students in Haromaya, Jimma, Ambo and Wollega universities held protests.. Read the rest of this entry

[Pictures] Semayawi Party Addis Ababa Rally

Ethiopian News: Semayawi Party held successful protest, rally in the capital Addis Ababa

Read the rest of this entry

ሠማያዊ ፓርቲ ያካሄደው ሠላማዊ ሰልፍ

የሠማያዊ ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው ሠላማዊ ሠልፍ መንግሥት እየተከተለው ነው ያለውን ብልሹ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ሙስናና ደካማ የመሠረተ-ልማት አቅርቦት ያሻሽል ሲል ጠየቀ… Read the rest of this entry

”ክቡር ፍርድ ቤት በሃይል የተገኘ ቃል ፍትህ እንዳያዛባ ውድቅ አንዲደረገልኝ አጠይቃለሁ።”

ዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው (ከፍርድ ቤት) ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ወዲያው ከ-ጸሃይ መሞቅ አንደገባሁ 22 ቁጥር ቢሮ ለምርመራ ተጠራሁ።በካቴና ታስሬ ነበር የመጣሁት። ”ኣለማየሁ መርማሪ ይለወጥልኝ ትላለህ ኣለ?..”….” ምን ዓይነት መርማሪ ነው የምትፈልገው” ኣለኝ። ዝም ኣልኩት… Read the rest of this entry

Ethiopia Prison Alert: Journalist in danger – An Urgent Appeal from Professor Mesfin Woldemariam

The UN Human Rights Commission  The African Union Human Rights Commission   The International Red Cross
Amnesty International   Human Rights Watch &    All Men and Women of GOOD WILL  Reeyot Alemu is a budding Ethiopian poet, essayist, and journalist… Read the rest of this entry

ካልገደሉ አያቆሙንም – ሃብታሙ አያሌዉ (የአንድነት አመራር) ሰልፉን በተመለከተ

ሀገር የመገንጠል ዓላማ ይዞ የተነሳው የህወሓት ጁንታ፣ በስውር እና በአደባባይ የጫካ ልማዱን መሰረት አድርጎ ሲገድል መኖሩ አዲስ ባይሆንም፣ ከሰሞኑ መረር ያለ እርምጃ ‹‹ግድያ›› ማሰቡን ከጓዳው የወጣ የወሬ ምንጭ ደረሰን…

Read the rest of this entry

Foreigners investors involved in land grabbing deals in Ethiopia.

Raswork MengeshaStockholm 

The fact that, wherever land acquisition by foreign investors has taken place, these “land grabs” have led to displacement, loss of livelihood and often death in the communities affected.. Read the rest of this entry

የተከብራችሁ የአንድንት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የድጋፍ ማህበር ዓባላትና ደጋፊዎች።

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!
 የአንድነት የድጋፍ ማህበር በስዊድን ከኢትዮጽያ ድምዕ ራዲዎ ጋር በመተባበር የሚለዮኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርሆ አንድነት ፓርቲ የጀመረው የቅስቀሳ ሥራ እንድትደግፉ ጥሪውን ያስተላልፋል…

Read the rest of this entry

አንድ ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? ሲፈቅድ ነው? ወይስ ሲፈቀድለት? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ …. Read the rest of this entry

%d bloggers like this: