ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ መዘጋጀቷ ተሰማ

‹‹ሱዳን ከማን ጋር እንደምትነግድ በሉዓላዊነቷ ላይ ማዘዝ አንችልም፤›› -ኢትዮጵያ በተዘዋዋሪ መሸጡ አያሳስበኝም አለች….

የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ለመግዛት ከተስማማው አንድ መቶ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ መጠኑ ይፋ ያልተደረገ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡

የሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ ኩባንያን ዋቢ ያደረገው ኢነርጂ ቢዝነስ ሪቪው ድረ ገጽ ባስነበበው ዘገባ መሠረት፣ በምሥራቃዊ ሱዳን በኩል ከከሰላ ግዛት ተነስቶ ወደ ኤርትራ የሚዘረጋ የ45 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር መዘርጋት ተጀምሯል፡፡

ከሁለት ዓመት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የህዳሴው ግድብ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ግብፅና አሁን ደግሞ ኤርትራ ተጠቃሚ ይሆኑበታል ተብሎ ስድስት ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ባለፈው ዓመት ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ ኃይል ማሰራጫ መስመርን በጋራ ማስመረቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሱዳን ወደ ኤርትራ ልትሸጥ ዝግጅት መጀመሯን በማስመልከት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የኃይል ሽያጭ ስምምነቱ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተደረገ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ ‹‹ይህም ሆኖ ሱዳን ከኢትዮጵያ የገዛችውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማን እንደምታስተላልፍና ከማን ጋር እንደምትነግድ ለመቆጣጠር አንችልም፣ ሉዓላዊነቷም አይፈቅድልንም፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹ሱዳን ከማን ጋር እንደምትነግድ በሉዓላዊነቷ ላይ ማዘዝ አንችልም፤›› ያሉት አምባሳደር ዲና፣ ሱዳን ከኢትዮጵያ የገዛችውን ኤሌክትሪክ ኃይል በተዘዋዋሪ መንገድ ለኤርትራ መሸጧ ላይ ችግር የለውም ብለዋል፡፡ ‹‹የምንፈልገው የአካባቢው አገሮች ሀብቱን ተጠቅመው በሰላም መጎራበታቸውን ነው፤›› ከማለታቸውም ባሻገር፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻም ሳይሆን ሌላውም የኢትዮጵያ ምርት ከኤርትራ ባሻገር ለማንኛውም አገር ቢቀርብ፣ ኢትዮጵያ ችግር እንደሌለባት አስታውቀዋል፡፡

በቅርቡ ለኤርትራ ቴሌቪዥን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያ ከህዳሴው ግድብ ከምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል የመግዛት ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀው ነበር፡፡ ፕሬዚዳንቱ የኤርትራ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ ትልልቅ የመንግሥት ተቋማት በኃይል አቅርቦት እጥረት ሳቢያ በአግባቡ አገልግሎት መስጠት እንደተሳናቸውና ኃይል ከኢትዮጵያ ለመግዛት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይህንን ከተናገሩ ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላ ኤርትራ በሱዳን በኩል ኃይል ለመግዛት መዘጋጀቷ ግን የፕሬዚዳንቱን መግለጫ ግራ የሚያጋባ አድርጎታል፡፡ በሱዳን አማካይነት ኤርትራ የኤሌክትሪክ ኃይል ልትገዛ ነው የሚለው መረጃ መረጋገጥ አለበት በማለት አምባሳር ዲና ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሱዳን ከኢትዮጵያ ለምትገዛው ኃይል በኪሎ ዋት አወር 0.6 ዶላር እንደምትከፍል ይጠበቃል፡፡ በዚህ አነስተኛ መጠን ገዝታ ለኤርትራ በምን ያህል ዋጋ ልትሸጥ እንደምትችልና ምን ያህል ሜዋ ጋት ኃይል እንደምታቀርብላት ለማወቅ አልተቻለም፡፡ Reporter amaharic

Advertisements

Posted on May 14, 2014, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: