ሳውዲ አረቢያን ያጠቃው መደሃኒት አልባ የግመል ጉንፋን «ኮሮና ቫይረስ» ለኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ ተገለፀ !

በሽታው የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን የሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ይፋ ካደረጉ ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራቶች ውስጥ በቫይረሱ ከተለከፉ ህሙማን መሃከል 500 ያህሉ ህይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ተችሏል…

 በዕድሜ የገፉ አዛውንቶች እና ተጓዳኝ የሆኑ እንደ ስኳር ደም ብዛት ኩላሊት ወዘተ መስል በሽታ ያሉባቸው እና በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅመ የሌላቸውን የቫይረሱ ተጠቂዎች በ 10 ቀናት ውስጥ በሽታው ለህልፈት ህይወት እንደሚዳራጋቸው ከሳውዲ አረቢያ ሆስፒታሎች የሚወጡ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ሳውዲያኑ ጨምሮ የተለያዩ ሃገር ዜግነት ያላቸው የቫይረሱ ተጠቂዎች መሞታቸውን በተለያዩ ግዜያት ከሚወጡ የሆስፒታሎች ዘርዝር መረጃ እስካሁን አንድም ኢትዮጵያዊ የቫይረሱ ሰለባ እንዳለሆነ ለማወቅ ተችሏል ።በሽታው ሲጀምር ጉንፋል መስል ባህሪ እንዳለው የሚናገሩ ባለሙያዎች ማስነጠስ ሳል ትኩሳት እና እራስምታት የሚታይበት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አካባቢው ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ቀርቦ በመርመር ከፋይረሱ ነጻ መሆኑንን ማረጋገጥ እንደሚገባው ይመከራል።

ለጥናቄ ይረዳ ዘንድ ማንኛውም ሰው እጆቹን በሳሙና ከመታጠቡ በፊት አፍንጫውን አፉን እና የአይኑን ሰውነት ክፍሎች በእጁ መነካካት እንደሌለብት የህክምና ጠበብቶች አክለው ይገልጻሉ ። በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ደማም ጣይፍ እና ሪያድ ከተማ ውስጥ በተለያዩ የስራ መስክ የተሰማሩ ከ1 ሚልዮን የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፤ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት እና በሪያድ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት በዚህ ዙሪያ የሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚ/ር መ/ቤት በአረብኛ ቋንቋ ለተማሪዎች ከሚያሰራጨው ጽሁፍ ባሻገር ለተመሪውም ሆነ ለወላጆች ስለበሽታው ተጨማሪ በሆነ ሀገርኛ ቋንቋ ግዝንዛቤ ለማስጨበጥ የተሰራ ነገር ባለመኖሩ ሊታሰብበት እንደሚገባ የሚያወሱ ወገኖች ኢትዮጵያኑ ማህበረሰብ የሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር መ/ቤት ለጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ ከሞባይል SMS መለዕክት ጀምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች የሚደርሱትን መመሪያዎች የአረብኛ እና የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማንበብ ለማይችሉ ወገኖች ሃስቡን በማካፈል ከበሽታው እራሳችንን ለመታደግ በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት እንደሚገባን ይናገራሉ ።

ይህ በዚህ አንዳለ የኮሮና ቫይረስ የስርጨት አድማሱን በከፈተኛ ድረጃ በማስፋት በመካከለኛው ምስራቅ ዱባይ ጆርዳን ኳታር እና ግብጽ መታየቱን የሚገልጹ ምንጮች በሽታው ለኢትዮጵያ ስጋት እንደሆነ በማውሳት ህዝቡ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባው ያሳስባሉ ። በቫይረሱ ስለተጠቁ ኢትዮጵያውያን መረጃዎች ያሏችሁ አካፍሉን
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Advertisements

Posted on May 16, 2014, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: