በጋምቤላ ክልል እየተፈጠመ ያለዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል አጥብቀን እናወግዛለን ባስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን!

ከመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ  የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እየሰራ ያለዉን ሀገር የማተራመስ እና የማፈረስ ስራ እንዲያቆም የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) ሲቃወም መቆየቱ የሚታወቅ ሃቅ ነዉ…

አማራ በደሙ እና በላቡ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ሀገር እንዳላቀና ወርቅ ላበደረ ጠጠር ሆነ እና ነገሩ ዛሬ በፋሽሽቱ የወያኔ መንግስት በየደረሰበት እየተገደለ እየተፈናቀለ ይገኛል፡፡ ትናንት በበደኖ በአርባ ጉጉ የተፈጠመበት ግፈ እና በደል ቁስሉ ሳይደርቅ ይባስ ተብሎ ከቀን ወደ ቀን እየባሰ በመምጣት ዛሬም እንደበግ እየታረደ ሜዳ ላይ ይጣላል ፡፡ ለብዙ አመታት ከኖረበት ቀየ እየተፈናቀለ ይገኛል፡፡ የወያኔ መንግስት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ካለዉ ጽኑ አላማ አንጻር የአማራዉ ህዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ በባሰ ሁኔታ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጠመበት ይገኛል፡፡

ወያኔ አማራዉን ትምክተኛ ነፋጠኛ ኦሮሞዉን ጠባብ ጉራጌዉን ተለጣፊ የሚል ቅጥል ሥም በመስጠት በፅኑ መሰረት ላይ አባቶቻችን ያስረከቡንን ሃገር ለመገነጣጠል ተግቶ በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡
የወያኔ መንግስት ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት የመዠንገር ብሄር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በሰላም እና በፍቅር የኖረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የመዠንገር ብሄርም በወያኔ ባለስልጣናት መሬቱን ተነጥቆ በድህነት አረንቋ ዉስጥ ነዉ፡፡ ይሁን እንጅ ከፍተኛዉን መሬት የያዙት የወያኔ ባለስልጣናት ተጨማሪ መሬት በመፈለግ የመዠንግርን ብሄር ከአማራ ከ ኦሮሞ ከደቡብ ጋር የተጋጨ በማስመሰል ወያኔ አንድም ያፈናቅላል ሁለትም አማራ ላይ የዘር ማጥፋት ይፈጥማል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነን 42 አማሮች ከሜጢ ከተማ ተረጋግቷል በሚል የወያኔ ባለስልጣን ወደ ቦታቸዉ እንዲመለሱ ካደረጉ በኋላ አርባዎቹ ባሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ማድረጋቸዉ ነዉ፡፡ በተጨማሪ አንቡላሶች ግጭቱ ከተከሰተበት ቦታ የተጎዳ ሰዉ ይዘዉ ከ መጡ ባኋላ ሲመለሱ የጦር መሳሪያ ይዘዉ እንደተመለሱ በግልጽ ታይቷል፡፡
ዛሬ በጋምቤላ እየተፈጠመ ያለዉን አይን ያወጣ የዘር ማጥፋት ወንጀል በጋራ ማስቆም ካልቻልን ነገ የችግሩ ገፈት ቀማሾች ሁላችንም መሆናችን የማይቀር ነዉ፡፡

መኢአድ በጋምቤላ ከ517 በላይ በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያዊያን ደም እንደቀልድ አያየዉም፡፡ ጉዳዩን ወደ አለም አቀፍ የ ጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ይወስደዋል፡፡
እነዚህ አረሜናዊ እና ጭራሽ ሰባዊነት የማይሰማቸዉ የወያኔ መንግስት ባለስልጣናትን መኢአድ እስከ ደም ጠብታ ድረስ ዋጋ በመክፈል ለፍርድ ያቀርባቸዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል በሜጢ ከተማ እና አካባቢዋ ፡፡በአማራዉ ላይ የተፈጠመዉ የዘር ማጥፋት እና ማፈናቀል በኦሮሞ እና በደቡብ ህዝቦችላይ የተፈጠመዉ ማፈናቀል በተጨማሪ ከ አንድ ሽ በላይ ቤቶች አንድ ቤተክርሲታን መቃጠል መኢአድን በእጅጉ አሳዝኖታል፡፡

መኢአድ ለተፈናቀሉት ወገኖቹም ያቅሙን አስቸኳይ እርዳታ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያዊያንን እና አለም አቀፍ ማህበረሱን በማስተባበር የሚቻለዉን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ለአለምአቀፉ ማህበረሰብም በችግር ላይ ላሉ ወገኖቹ በአስቸኳይ እንዲደርስላቸዉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዉን ያሥተላልፋል፡፡
መኢአድ ይህን የዘር ማጥፋት ወንጀል ሚዲያዎች ሁሉ ተገቢዉን ሽፋን እንድትሰጡት ጥሪዉን ያሰተላልፋል፡፡ በርግጥ በሃገር ዉስጥ የነበሩ ነፃ ሚዲያዎች ሙሉ በሙሉ በወያኔ ተዘግተዋል፡፡ በዉጭ ያላችሁ ሚዲያዎች ከአሁን በፊት ለሰጣችሁት ሽፋን በኢትዮጵያ ህዝብ እያመሰገንን አሁንም ተገቢዉን ሽፋን እንድትሰጡት እንጠይቃለን፡፡ በወያኔ መንግስት የሚመራዉ በቅርቡ ስሙን የቀየረዉ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በየሳምንቱ ከደህንነት ሰዎች ጋር በመሆን ካሜራህን ይዘህ ከበራችን ከምትቆም በጋምቤላ ወገን በግፍ እያለቀነዉ እና እንድትዘግብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
መኢአድ ዘረኛዉ እና የለየለት አባገነኑ የወያኔ መንግስት ወድቆ በምትኩ ህዝባዊ መንግስት በኢትዮጵያ እስኪሰፍን ድረስ በፅኑ ይታገላል ፡፡
በመጨረሻም መኢአድ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተላልፈዉ መዕልክት በያላችሁበት የወያኔን መንግስት በመቃወም በተግባር እንቅስቃሴ በመጀመር ለኢትዮጵያ አንድነት እና ድሞክራሲ መስፈን በፅኑ ከሚታገለዉ ከመኢአድ ጎን እንድትቆሙ ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡
16/1/2007
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Advertisements

Posted on September 26, 2014, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: