የሕዝብ ተስፋ የሆነው አንድነት ፓርቲ ትልቅ አደጋ ላይ ነው (አማኑኤል ዘሰላም)

ያለፈው የ2006 ዓ.ም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ከዘጠና ሰባት አመት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ፣ ለሕዝቡ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ፣ ከፍተኛ አገር አቀፍና ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ሲያደርግ እንደነበረ ይታወቃል…

በባህር ዳር፣ በአዳማ፣ በጊዶሌ፣ በጂንካ, በአርባ ምንጭ ፣ በደሴ፣ በጎንደር፣ በወላይታ ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍቼ በመሳስሉ ከተሞች የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል ንቅናቄ ፣ ብዙዎችን ለትግሉ ለማነሳሳት የቻለ ሲሆን፣ የፓርቲው ተቀባይነት እጅግ በጣም ከፍተኛ እንዲሆንም አድርጎት ነበር።

ጠንካራ ፓርቲ እንዲኖር የማይፈልገው ሕወሃት/ኢሕአዴግ በፓርቲው ጠንካራ አመራር የሆኑትን በማሰር የአንድነት ፓርቲን እንቅስቃሴ ለመግታት መሞከሩ አልቀረም። እንደ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ ያሉ ወጣት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ክስ ሳይመሰርትባቸው በማእከላዊ እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡

የአገዛዙ እኩይ ተግባር እንደተጠበቀ የአንድንት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፍፈራው፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አባላትን እና ደጋፊዎች አሰባስበው ትግሉን ከማስቀጠል ይልቅ፣ በአባላት ዘንድ መከፋፈሎች እንዲመጡ፣ ሊሰሩ የሚችሉ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሸሹ በማድረግ፣ አንድነት ፓርቲን ትልቅ አደጋ ላይ እየጣሉት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡።

የሚሊዮኖች ንቅናቄ ሐሳብ አመንጪና በአባላትና ደጋፍፊዎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ያለውን ፣ አቶ በላይ ፍቃዱን ጨምሮ፣ በርካታ የሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከኢንጂንር ግዛቸው ጋር ልንሰራ አንችልም በሚል ከሥራ አስፈጻሚ ሃላፊነታቸው የለቀቁ ሲሆን፣ በምክር ቤት አባልነት ብቻ ለፓርቲው የድርሻቸውን ለማበርከት ተወስነዋል።

ያለፈው ሰኔ 8 ቀን 2006 በአዳማ እና በደብረ ማርቆስ ፣ ተጠሪነቱ ለምክርር ቤቱ በሆነውና ሃብታሙ አያለው በሚሰበስበው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል አመራርነት ፣ ከተደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ዉጭ ፣ ላለፉት ሶስት ወራት ከአሥራ አምስት ቀናት ምንም አይነት እንቅስቃሴ የአንድነት ፓርቲ ከማድረግ ተቆጥቧል። ፓርቲው እንደነ ዶር በየነ ፓርቲ በቢሮ ዉስጥ መገልጫዎችን በማወጣት ላይ ብቻ የተወሰነ ፓርቲ ሆኗል።

በቅርቡ የፓርቲዉን መፍዘዝ ያዩ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ወጣቶች፣ ከሌሎች ድርጅቶች ወጣቶች ጋር በመመካከር ፣ የታሰሩ ወገኖችን ለማሰብ የሻማ ማብራት እና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች ቢጀምሩም፣ ኢንጂነር ግዛቸው ከኢሕአዴግ ጋር መጋጨት አያስፈልግም በሚል፣ መግለጫ በመስጠት ብቻ በመወሰናቸው፣ በርካታ ወጣቶችን ከማሳዘን አልፈው ተስፋ እያስቆረጡ ነው።

በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ያሉ በርካታ አባላት፣ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑ በፓርቲው ዉስጥ ትልቅ አስተዋጾ አድርገው አሁን ከጀርባ ሆነው የሚያገለግሉ ወገኖች፣ ምሁራን፣ የተከበሩ ኢትዮጵያዉያን ፣ የኢንጂነር ግዛቸው አመራር ስላሳሰባቸው ፣ ሕዝቡ ተስፋ የጣለበትን ፓርቲ ለማዳን ሲባል፣ ኢንጂነሩ እንዲለቁ መጠየቃቸውንም፣ አንዳንድ ዜናዎች ይጠቁማሉ። ከነዚህ የተከበሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል ፣ ከኢንጂነር ግዛቸው ጋር አንድነት የመሰረቱትና ከኢንጂነሩ ጋር የብዙ አመታት የትግል አጋር የሆኑት ዶር ያእቆብ ወልደማሪያም፣ የተከበሩ አቶ ይልማ ይፍሩ፣ ዶር ዳኛቸው ይገኙበታል።

በዉጭ አገር የሚገኙም፣ አንድነት ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ፓርቲው ሲደገፉ የነበሩ፣ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች፣ የፓርቲው አቅጣጫ እንዳሳሰባቸው በመገልጽ ፣ አንድነት ከቢሮ ፖለቲካ ወጥተው ሕዝቡን ወደ ማንቀሳቅቀስ እንዲመለስ በማሳሰብ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በኢንጂነሩ አመራር ትግሉ ዉጤት ያመጣል ብለው እንደማያምኑም እየገለጹ ነው።

በቅርቡ የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ግርማይ ግዛው፣ ለኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በላኩትና ለደጋፊዎች ግልባጭ ባደረጉት ደብዳቤያችው፣ ኢንጂነር ግዛቸው ለትግሉ ሲሉ ሃላፊነታቸው እንዲለቁና ፣ ሊሰሩ ለሚችሉ አዳዲስ አመራሮች እንዲያስረክቡ ተማጽነዋል።

“I plead with you for the sake of your legacy and honor as well as for UDJP, step down nowand with dignity, honor and the love of the country, please transfer your leadership for a new bread of leaders. You have many unchartered opportunities such as to be a member of the council of elders and advice and mentor many young leaders for years to come like Dr. Hailu Araya”

ሲሉ ነበር አቶ ግርማይ ትልቅ ተማጽኖ ያቀረቡት። ኢንጂነር ግዛችው በአስቸኳይ ከሃላፊነታቸው ተነስተው ፣ የፓርቲዉን አባላትና ደጋፊዎች በቶሎ በማሰባሰብ፣ ፓርቲው ሕዝቡን ወደ ማደራጀት ሥራ በቶሎ ካልተመለሰ፣ የአንድነት ፓርቲ ትልቅ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችልም ይገመታል። በመሆኑም አባላትና ደጋፊዎች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለጽ፣ አቶ ግርማዬ ግዛዉ እንዳደረጉት፣ መልእክታችንን ለኢንጂነር ግዛቸው እናስተላልፍ። ” የወያኔ ተጠቃሚ እንደሆነው፣ በሕዝብ እንደቀለለው ፣ እንደ አየለ ጫሚሶ አይሁኑ። የዶር ኃይሉ አርአያ ፈልግ ተከትለ፣ ስምዎትን በክብር ቦታ ያስፍሩ እንበላቸው” ። አንድነት እንደ ዶር በየነ ፓርቲ፣ ሕዝባዊ ሳይሆን የግለሰቦች ፓርቲ ሆኖ እንዲቀር፣ እንዲሞት የማንፈልግ ከሆነ፣ አሁን ድምፃችንን እናሰማ። አንድነትን እናድን !!!

የኢንጂነር ግዛቸው ኢሜል የሚከተለው ነው ፡

Gizachew Shiferaw (president) <gizshif@gmail.com>

Advertisements

Posted on October 7, 2014, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: