ስለ ባቡር ፕሮጀክቶች እስቲ አንድ ሁለት ልበላችሁ

አቶ ኃይለማሪያም እና የተከበሩ የአንድነት አመራር አቶ ግርማ ሰይፉ በባቡር ግንባታው ዙሪያ በፓርላማ አንድ ሁለት ተባብለዋል። ኢሕአዴግ ከአራት አመታት በፊት የአምስት አመት የትራስፎርሜሽን እቅድ በሚል አንድ ሰነድ አዘጋጅቶ ይፋ አደርጎ ነበር። መቼም ሁላችንም ያንን ሰነድ የምናስታወሰው ይመስለኛል..

issa tog

ሰነዱ በርግጥ ጥሩ ሰነድ ነበር። አንዳንድ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም፣ ኢሕአዴግ በሰነዱ የተቀመጡትን አደርጋለሁ ብሎ መነሳቱ ሊያስመሰግነው ይገባል።

ነገር ግን እሰራለሁ ብሎ ደግሞ ካልሰራ ወይንም በበቂ ሁኔታ መስራት ከተሳነው ፣ ሃላፊነነት መዉሰድ አለበት። አቶ ግርማ ሰይፉ በተሰጠቻቸው ትንሽ ደቂቃ፣ አገዛዙ በባቡር ረገድ ከ2300 ኪሎሜትር የባቡር መስመር ከመቶ የማይበልጥ እንደሰራ በመግለጽ፣ ቢተቹም፣ አቶ ኃይለማሪያም ሌሎች ላይ ከማላከክ ዉጭ የሰጡት በቂ መልስ የለም። እንደዉም 1500 ኪሊሜትር ሥራ ተጀመሯል ብለዉናል በቁጣ። አንዴ ብራዚልን፣ አንዴ ደግሞ ሩሲያን ሲወቅሱ ተሰምተዋል።

ጉዳዩን ለማታወቁ በትራንስፎርሜሽን እቅዱ የተቀመጡ የባብሩ መስመር ፕሮጀክቶችን እንመልከት። በአዲስ አበባ ያለው የመልስተኛ ባቡር በኋላ የመጣ ነው። (እርሱም ቢሆን ተጀመረ እንጂ ሥራ ላይ አልዋለም) መጀመሪያ የታሰቡት በአምስት ኮሪደሮች ግንባታውን ምርጫ 2007 ከመድረሱ በፊት ለማጠናቀቅ ነበር።

1. በአጼ ሚኒሊክ ዘመን የነበረዉን የአዲስ አበባ ጅቡቲ መስመር በአዲስ መልክ ማደስና መስራት ነው አንደኛው መስመር ። እዚህ ላይ አዲስ መስመር ከሰበታ አዲስ አበባ ሲቀጠል፣ ከአዲስ አበባ አዳማ ደግሞ ድረብ መሰመር ነው የሚሆነው። መስመሩ 656 ኪሎሜትር ሲሆን ፣ ወጭው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ነው። ማለቅ ከነበረበት ቆይቷል፤ ግን እስከአሁን አላለለቀም። ምን ደረጃ ላይ እንዳለም በግልጽ አይታወቅም።የድሮዉን ሃዲድ ነቅሎ አዲስ መትከል ነው። የሚቆፍሩት፣ የሚጠርጉት ምንም አይነት መንገድ አይኖራቸውም። ይሄ መስመር በቶሎ መጠናቀቅ ያለበትና ጠቃሚ መስመር ነው ብዬ ነው የማስበው።

2. ከአዋሽ – ወልዲያ መስመር ያለው ደግሞ ሁለተኛ መስመር ነው። 375 ኪሎሜተር እርዝመት ሲኖረው፣ የቱርክ ኩባንያ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ኮንትራት ወስዷል። አሁን ይሄ መስመር መጠናቀቅ ነበረበት፤ ግን ስራዉ ገና አልተጀመረም።ያው በእቅድና በዝግጅት ላይ ናቸው እንጂ።

3. ከመቀሌ-ወልዲያ-ታጁራ (የጅቡቲ ሌላ ወደብ) የሚወስደው መስመር ፣ ሶስተኛው ነው። ከመቀሌ -ወልዲያ ፣ 260 ኪሎሜትር ለሚሆነው ብቻ ከቻይና ኩባንያ ጋር 1.5 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተደርጓል። አስቡት፣ ከአዋሽ ወልዲያ ያለውን መስመር ብንከት፣ መቀሌን በባቡር ከአዋሽ ጋር ለማገናኘት ቢያንስ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተደረገ ማለት ነው። እስከአሁን ለባቡር ወጭ ከታሰበው 4.8 ቢሊዮን ዶላር 60 % ማለት ነው። (ቢያንስ ያልኩት ከወልዲያ ታጁራ ያለው መስመር ወጫን ስላልጨመርኩ ነው)

ከአዲስ አበባ – ጅቡቲ ያለው 656 ኪሎሜትር 1.2 ቢሊዮን ብቻ ፈጅቶ ፣ ከመቀሌ ወልዲያ ያለው 260 ኪሎሜትር 1.5 ቢሊዮን ዶላር የፈጀበት ምክንያት አለ። ወደ መቀሌ ባቡሩን ለማስገባት 29 ትላልቅ ድልድዮች፣ 19 ኪሌሜትር የሚሆን በተራራ ዉስጥ የሚያልፍ ታነል ወይንም ቀዳዳ መንገድ ስለሚያስፈልግ ነው። እንድ አምባላጌ ያሉ ቦታዎችን ማለፍ የግድ ስለሆነ።

እንግዲህ በዚህ ላይ ሊነሱ የሚገባቸው መሰረተዊ ነጥቦች አሉ። መቀሌ ከሁለት የጅቡቲ ወደቦች ጋር ልትገናኝ ነው ማለት ነው። አንደኛው በአዋሽ በኩል ከጅቡቲ ጋር ፣ ሌላው ደግሞ በሰመራ በኩል ከታጁራ ጋር። አንድ በሉ።

ለ260 ኪሎሜትር ያህል ወጭ ማውጣቱ፣ ከዚያ አካባቢ ፖታሽ ለማመላለስ ነው የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ አሉ። ተራራዎችን መብሳቱን ትተን፣ የባቡሩ መስመሩን እስከ አላማጣ በማርዘም ፣ ፖታሹ እስከ አላማጣ በመኪና ማመላለስ አይቻልም ነበር ወይ ? ደግሞስ ፖታሽ ምን ያህል የዉጭ ምንዛሮ ቢያሰግኝልን ነው ቢሊየን ዶላሮች ለርሱ አሁን የምናፈሰው ? የፊሲቢሊቲ ጥናት ተደርጓል ወይ ? ሁለት በሉ።

ከኤርትራ ጋር ያለው ችግር ለዘላለም አሁን እንዳለው አይቆይም። በመሆኑም ትግራይንና ጎንደርን በቀላሉ ከምጽዋ ጋር ማገናኘት ሲቻል፣ አሁን 3.2 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ማድረጉ ምን ይባላል ? በአስመራ ጥሩ መንግስት ሲመጣ ምጽዋን በሚገባ መጠቀም ይቻላል። ይቅርታ ይደረግልኝና ትግራይ፣ ጎንደር፣ ጎጃም ከአሰባን ጅቡቲ ይልቅ የሚቀርቡት ለምጽዋ ነው። ከምጽዋ አሰመራ፣ ጣሊያን የሰራው መስመር አለ። ያንን ማደስ በቀላሉ ይቻላል። ከአስመራ ፣ በሰናፈ፣ አዲግራት አልፎ ወደ መቀሌ የሚደርስ መሰመር መዘርጋት ይቻላል። ከአስመራ እሰከ ዛላንበሳ ኤርትራውያኖች ሲገነቡ እኛ እስከመቀሌ የምንገነባው 160 ኪሌሜግትሮች ብቻ የሚሆነው።

አሁን መቀሌን ከጅቡቲ ብናገናኝ፤ ኢሳያስ ሲለወጥ ፣ ከ ኤርትራዉያን ወንድሞቻችን ጋር ሰላም ስንሆን ፣ ኢኮኖሚካሊ የሰሜኑ ክፍላችን ፊቱን ወደ ምጽዋ ማዞሩ አይቀሬ ነው። ስለዚህ ለምን ጭፍን ሆነ፣ ነገ ለማንጠቀምበት ነገር የሕዝብን ገንዘብ እንበትናለን ?

4. የአዲስ አበባ- ኢጃጂ- ጂማ- በደሌ መስመር አራተኛው ነው። የምእራቡን የአገራችን ክፍል የሚሸፍን ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መስመር ነው። ላለፉት 20 አመታት ያላደገው የአገራችን ክፍል ቢኖር ምእራብ ሸዋ፣ ወለጋ፣ ኢሊባቡር ያሉ ቦታዎች ናቸው። ለነዚህ ቦታዎች ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባው ነበር። ግን እንደ ሰሜኑ በቂ ትኩርት አልተሰጠውም።

5. የሞጆ-ሻሸመኔ-አርባ ምንቭ- ወይጦ መስመር እንደዚሁ፡

Advertisements

Posted on October 18, 2014, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: