ሰበር ዜና ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው ! !

ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ። “ወደ ፖለቲካው የማትመለስ ከሆነ ትወጣለህ… አለበለዚያ እዚሁ ነው የምትሞተው” በማለት አማራጭ ቢያቀርቡለትም፣ ሃብታሙ መሞትን እመርጣለሁ የሚል መልስ የሰጣቸው ሲሆን፣ እየደረሰበት ባለው ስቃይ በጣም እየታመመ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

“እስኪ ትግሉን እናስቀጥላለን የሚሉ ሰዎች ያድኑህ ? “ ሲሉ አሳሪዎቹ በስቃዩ የሚደሰቱ ሲሆን፣ ከባለቤቱ በስትቀር ጠበቃዉም ሁሉ ሳይቀር እንዳያየው ተደርጓል። በተመሳሳይ ሁኔታ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ ፣ በታፈነና አየር በማያስወጣ ክፍል ዉስጥ እንዲታሰር በመደረጉ በተደጋጋሚ ለተቅማጥና ተያያዥ በሽታ መጋለጡን፣ እንዲሁም የመተንፈስ ችግር እንዳለበት ለማወቅ ችለናል።

“የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው ? አንድነት ዉስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት እነማን ናቸው ? “ በሚል ጥያቄ የቀረበለት ዳንኤል ሺበሺ፣ ክብሩን በሚነካ መልኩ እንደሚሰደብም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሃብታሙ አያሌው ፣ በእርሱ ላይ እይደረሰ ያለው ግፍ በማንም ዜጋ ላይ መድረስ እንደሌለበት በመግልጽ “የግፈኛው አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት አለበት” ሲልም ለህዝቡ የትግል ጥሪ አስተላልፏል

issa photo

Advertisements

Posted on October 28, 2014, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: