እኛ በመንፈስም በአካልም የታሰርን ነን ( ሄኖክ የሺጥላ )

ጄነራል ዋስይሁን ንጋቱ ፣ “ዕጣ ፈንታ እና መስዋዕትነት” በሚለው መጽሐፍቸው
በ1985 አቡነ ጳውሎስ በማዕከላዊ ማሰቃያ ቤት የሚገኙ ተሰቃዩችን ለመጎብኘት መጥተው እንደነበር ና በዚያም እስር ቤት ውስጥ ፕሮፌሰ አስራት ወልደየስ ታስረው የነበሩ መሆናቸውን ይተርካሉ ….

ታዲያ ታጋይ ( ወይም ተባይ ) ወይም አባ ወይም ( እባብ ) ጳውሎስ ፕሮፌሰሩን ለማናገር ፈልገው ኖሮ ” ፕ/ር አስራት የት አሉ ?ሲሉ ጠየቁ ፤የታሰርነው በአንድ ክፍል በመሆኑና ፕሮፌሰሩን ስለምቀርባቸው እኔ እንድጠራቸው ተጠየቅኩ እናም ፓትርያርኩ እየጠበቋቸው እንደሆነ ነገርኳቸው ፕሮፌሰሩ ፈገግታ እያሳዩኝ‹‹የሞትኩ መስሏቸው ሊገንዙኝ ነው እንዴ የመጡት ?አልሞትኩም፣አለሁ ብሏል በላቸው››ሲሉ መለሱልኝ፡፡
ፓትርያርኩ ፕሮፌሰሩ እንደማይመጡ ሲያውቁ ‹‹እኔ ወዳሉበት እሄዳለሁ››በማለታቸው አብረናቸው ሄድን፡፡አባ ጳውሎስ ፕሮፌሰሩ ጋ ሲደርሱ ሰላምታ ሰጥተው መስቀል ለማሳለም ሲሞክሩ ፕ/ር አስራት ‹‹አባታችን !እኔ በአካልና በመንፈስ የታሰርኩ በመሆኔ ፈጽሞ አላነጋግርዎትም !እርስዎም አያነጋግሩኝም››ሲሉ እምቢታቸውን ገለጹ፡፡
‹‹ምነው ፕሮፌሰር አስራት …አንድ የተማሩ ፕሮፌሰር ሆነው ፣እኔ እርስዎን ለማነጋገር እስር ቤት ድረስ ስመጣ አላነጋግርህም ይሉኛል?››አሉ ፓትርያርኩ ፡፡
ፕሮፌሰሩም‹‹አባ! አሁን እዚህ ቦታ ስለትምህርትና ዕውቀት መጥቀስና መናገር ምን ይረባል? እርስዎም እኮ ዶክተር ነዎት !ከተናገሩኝ ሰውነኝና መልስ መስጠቴ አይቀርም፤ካናገሩኝና መልስ ብሰጥዎት ደግሞ መቀየምዎ ስለማይቀር….አላናግርዎትም፡፡እኔ በአካልም በመንፈስም የታሰርኩ ነኝ››ሲሉ ፓትርያርኩ እስረኞቹን በሙሉ ሳያናግሩ ተመልሰው ሄዱ፡፡

አዎ እኛ በመንፈስም በአካልም የታሰርን ነን ። ከተናገራችሁን መልስ እንሰጣለን ፣ መልስ ከሰጠናችሁ ደሞ ትቀየማላችሁ ። ስለዚህ ተውን ። እኛ እስረኞች ነን ፣ ሀገር የሌለን ፣ እኛ ነፍጠኞች ፣ መሳሪያ ግን የሌለን ፣ እኛ ጉልተኞች ነን ፣ መሬት ግን የሌለን ፣ እኛ አድሃሪዎች ነን ፣ ድህረ ታሪክ የሌለን ። አያችሁ ዘረኛ ካላችሁን መልስ እንሰጣለን ፣ ከትግሬ ወያኔ የባሰ ዘረኛ አለ ወይ ብለን ፣ ገዳይ ካላችሁን መልስ እንሰጣለን ፣ ከናንተ ከትግሬ ወያኔ የባሰ ገዳይ አለ ወይ ብለን ፣ አጥፊ ካላችሁን መስል እንሰጣለን ፣ ልማት የምትሉት የናንተ ድንቁርና ” ልጅ ያቦካው” እንደሆነ ተናግረን፣ እንደ እናንተ ክንዳችን አርበ ሰፊ አይዶለም ፣ የሰራዊታችን ብዛት ተራራ አይደረምስም ፣ ጉልበታችን አፈር ውስጥ ነው ያለው ፣ ያም ሆኖ ወኔያችን አልበሰበሰም ፣ ድምጻችን አልሳሳም ፣ ገጻችን ቢጠወልግም ፣ ደማችን አልሰነፈም ፣ ስራችን አልጠነዛም ፣ ስለዚህ ባናናግራችሁ እንመርጣለን ፣ ከተናገርን ግን የምትሰሙትን ላትወዱት ትችላላችሁ ፣ ስለዚህ ዝም በሉን ።
አሁንም ያልነው እኛ በመንፈስም በአካልም የታሰርን ነን ፣ መንፈሳችን ኢትዮጵያ ለሚል እውነት ተገዞቷል ፣ አካላችን በናንተ አሽክላ ተበልቷል፣ ስለዚህ ተውን ።

እኛ የሚያስጨንቁንን ችግሮች አላቃለልንም ፣ መነሻችን እንጆ መድረሻችን በናንተ ዘረኛ ማንነት ተደናቅፎብናል ፣ ከተናገራችሁን ግን በታሪክ ላይ ያፈሰሳችሁትን ደም ፣ የረጫችሁትን መርዝ ፣ የነዛችሁትን አሉባልታ ፣ የበላችሁትን ትውልድ ሁሉ እንናገራለን ። ለኛ ዳር ድንበራችን ፍቅር ነው ፣ ዘራችን አንድነታችን ነው ፣ ውበታችን መዋለዳችን ነው ፣ ለናንተ ይሄ ሁሉ የአማራ ተራ ወሬ ነው ፣ የ ነገስታት ቀፍዳጅ ልቦና ነው ፣ የ ገዢዎች ደባ ነው ። ስለዚህ በናንተና በኛ መሃከል ትልቅ የታሪክም ፣ የ ሰብአዊ ማንነትም ልዩነት አለ ። ያም ሆኖ ካልተዋችሁን እንናገራለን ፣ ልባችንን ገራምነት እንጂ ፍርሃት እንደማይገራው ፣ ጥፋት እንደማይጋራው አበክረን እንገልጻለን ። ጠሐፊው እንዳለው
ታላቁ፡ሙዐሊም፡ኢብን፡ኣል፡ዐረቢ Interpretation of Longing በሚለው፡ኪታቡ፦
My heart has become capable of every form,
It is a pasture for gazelles and a cloister for Christian monks,
A temple for idols and the pilgrim’s Ka’aba,
The Tables of the Torah and the book of the Koran.
I follow the religion of Love, and whatever direction
Its camels may take, Love is my religion and my faith
ደገኛው፡ሕግ፡ፍቅር፡ነው፡ሲል፣ደገኛውም፡ሃይማ ኖት፡ፍቅረ-ቢጽ፡መኾኑን፡ሲያጠይቅ፥እምነት፡ኹሉ ሕግ፡ኹሉ፡በዚህ፡መካተቱን፡ሲያጸና፡ነው።ሰብእና እንጂ፡ነው፡መሠረቱ፡ለፍቅር፡ዳር፡ድንበር፡የለው ም፡ሲል፡ነው።

አዎ እኛም ድንበራችን ልባችን ፍቅር አለበት ብሎ እስካመነበት ድረስ ነው ፣ ስለዚህ የናንተኑ ቅጥር ለመዝለቅ የሚያስችል ሥሜት አላየንባችሁም ። አርባን ቢስነትን ታሪክ ስታደርጉት ስናይ ትናንትም ዛሬም አዲስ አይደለም ። ሀገሪቱዋን ወደብ አልባ ከማድረግ እስከ የታሪክ እሴቶቻችንን ና መተርኮቹን በኪሎ እስከመሸጥ ይደርሳልና ። ካናገራችሁን የናንተ ሞት የኢትዮጵያ ትንሣዔ እንደሆነ መናገራችን አይቀርም ።

ፓስካልም፡በPensées፡ቁጥር፡257፡ላይ፦
There are only three kinds of persons; those who serve
God, having found Him; others who are occupied in
seeking Him, not having found Him; while the remainder
live without seeking Him and without having found Him.
The first are reasonable and happy, the last are foolish and
unhappy; those between are unhappy and reasonable.

እናንተ እንግዲህ የትኞቹ ትሆኑ ?
ብቻ አትነካኩን ከነካካችሁን ግን መናገራችንን አንተውም !!!

ልዩ ምስጋና ለ ጌታው !!!

Advertisements

Posted on December 13, 2014, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: