የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

• ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ጥሪ አቅርቧል
• ‹‹ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን››..

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹በነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› ዘመቻው ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ ትብብሩ ዛሬ ጥር 12/2007 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል ገልፀዋል፡፡ ‹‹የኢህአዴግ ጨካኝነትና የምርጫ ቦርድ አጋፋሪነት ሊቀጥል ይችላል›› ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሆኖም የትግሉ አላማ ኢህአዴግን ማጋለጥ በመሆኑ የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ትግሉን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ ጥሪ ስናደርግ የፖለቲካ ምህዳሩ ተስተካክሏል እያልን አይደለም፡፡ እኛ አሁንም እያነሳን ያለነው የትግል ጥያቄ ነው›› ያሉት የትብብሩ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ የትብብሩ የትግል አላማ ይህን የተዘጋ ምህዳር ማስከፈት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ትብብሩ ‹‹የትግሉ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆንከው መራጩ ህዝብ ነጻነትና ክብርህን ለማስመለስ በምናደርገው ትግል በንቃት እንድታሳተፍ፣ ዛሬውኑ በመመዝገብ የሥልጣን ባለቤትነትህን የምታረጋግጥበትንና ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት የምትቀጣበትን ትጥቅ ‹‹የምርጫ ካርድህ››ን በእጅህ እንድታስገባ›› ሲል ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እንዲሻሻሉ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች የማይመለሱ ከሆነ እና ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን ብሏል፡፡
ምህዳሩ ተዘግቷል እያላችሁ ህዝቡ ምርጫ ካርድ እንዲያወጣ መጠየቅ አይጋጭም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ‹‹ዜጎች ምርጫ ካርዱን ማውጣታቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ይጠቅማል፡፡ ኢህአዴግ አንድ ለአምስት እየጠረነፈ የምርጫ ካርድ በማስወጣቱ ህዝቡ ተስፋ ሊቆርጥ አይገባም፡፡ ትግሉ ሲጠናከርና ሂደቱ ሲቀርብም ኢህአዴግ እጠቀምበታለሁ ያለውን ሁሉ የማንጠቀምበት ምክንያት የለም፡፡ ለመምረጥም ሆነ ላለመምረጥ ምርጫ ካርድ ማውጣቱ አስፈላጊ ነው፡፡ የመጨረሻ ውሳኔው በሂደቱ የሚወሰን ይሆናል፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አቶ ግርማ በቀለ በበኩላቸው እስካሁን ትብብሩ ያደረገው ትግል ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ጎን የቆመበት መሆኑን ያረጋገጡበት እንደሆነ ገልጸው ሂደቱን ለመወሰን ህዝቡ ምርጫ ካርዱን አውጥቶ መጠባበቅ እንዳለበትና ምርጫ የመግባትና አለመግባት ጉዳይ ለመወሰን ጊዜው ገና መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ምርጫ ከመግባትና ካለመግባት ባሻገር ትግሉን በማጠናከር ኢህአዴግ አንድም በግልጽ በመሳሪያ ብቻ እገዛለው እስኪል አሊያም በምርጫና በመሳሪያ መካከል ያለውን አታላይ መንገድ ትቶ ዴሞክራሲያዊ መንገድን እንዲመርጥ ማድረግ ትልቅ ድል ነው፣ ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር የትግሉ ዋና አላማ የኢህአዴግን አታላይነት ማጋለጥ ነው ብለዋል፡፡bluparty

Posted on January 23, 2015, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: