ተነስ ተነስ ተነስተናል! አንተ ያገሬ ጀግና !!

10940460_407047902792900_1731833579569597840_nBy Issa Abdusemed
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊያንን ከምድረ ገጽ እስከ ወዲያኛው ፈጽሞ ለማጥፋት ለሴኮንዶች እና ለስንዝር ወደ ኋላ የማይሉ መርዘኛ የወንበዴ ቡድኖች እና የርኩስ ሴራቸውን ከእንግዲህ ለመታገስ ወደ ማይቻልበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያን በረጅም የኋሊት ታሪካችንም ሆነ በመጻኢ ዘመናችን ወዲያኛው ገጥሞን በማያውቅ እና ይገጥመናልም ተብሎ በማይጠበቅ የህልውና ጥልቅ ገደል አፋፍ ላይ እናገኛለን፡፡ ለኛ ለኢትዮጵያን መራብ፣ መታረዝ፣ መደንቆር፣ መጠማት፣ በችግር መመታት፣ በወረርሽኝ ማለቅ፣ በድርቅ መመታት፣ በጦርነት ማለቅ፣ ስደት፣ ሥራ አጥነት፣ ውነብድና፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ እስር፣ ድብደባ፣ እንግልት፣ ውርደት፣ሞት፣ መለያየት፣ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ሙስና፣ የፍትህና የነጻነት እጦት፣ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ፣ የትራንስፖርት፣ … ወዘተረፈ ህልቆ መሳፍርት ቀጥተኛ ተጠቂዎች የምንሆንበት ዘመን ከእንግዲህ ያከትማል፡፡
ጥቂቶች ሚሊዮኖችን የዋህ ህዝብን እርስ በእርስ በማባላት የሚቀጥሉበት ዘመን ከእንግዲህ ከህልምነት ሊዘል አይችልም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵየዊ በአሁኑ ወቅት ከፊቱ በስንዝር ርቀት የሚጠብቀውን በየቤቱ የሚንኳኳበት የነጻነት የትግል ችቦ ለማቀጣጠል ተነስቷል፡፡ ይህንን የመላው ህዝብ ትግል ከእንግዲህ በየትኛውም መልኩ ሊያጨናግፍ የሚችል መድራዊ ሀይል እንደማይኖር ለዘላለም መመኪያችን በሆነው ኃያል አምላክ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በተሰጠንም የድል አድራጊነት መንፈስ በሙሉ ልብ በቆራጥነት እና በጀግንነት ታግለን የሚያስከፍለውን መሰዋዕትነት ሁሉ ከፍለን የነጻነት አየር ለመተንፈስ ተዘጋጅናል፡፡
ክቡር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ከእንግዲህ ለራስህ ነጻነት መቆም ያለብህ ራስህ ነህና በአንድነት ሆ ብለህ ለአንዲት ኢትዮጵያ ትንሳኤ በቆራጥነት እና ጀግንነት ተነስ፡፡

ISSAABDUSEMED@GMAIL.COM

Posted on January 24, 2015, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: