በአየር ሃይል አውሮፕላን ጥቃት ተሰዘነረ -አርአያ ተስፋማሪያም

e8735-ethiopianairforcecargoantonov90 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫነ የአየር ሃይል አንቶኖቭ አውሮፕላን ከመጋየት መትረፉን የቅርብ ምንጮች ያደረሱኝ መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት አቆጣጠር 90 የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪዎችን አሳፍሮ ደቡብ ሱዳን – ሃዲጉሊ የተባለች ግዛት የደረሰው አንቶንቭ አውሮላን ወደ መሬት እየወረደ ባለበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በዲሽቃ በተተኮሰ ሁለት ጥይት በጎን በኩል እንደተመታ ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአብራሪዎቹና ወታደሮቹ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበረ ያመለከቱት ምንጮቹ የተተኮሰው ጥይት ሞተሩ አካባቢ ቢያርፍ ኖሮ አውሮፕላኑ ሊነድ ይችል እንደነበረ አስታውቀዋል። አንቶኖቭ አውሮፕላኑ ባላፈው ሳምንት በአንዱ የሞተር ክፍል ብልሽት ገጥሞት ለሰባት ቀናት በጥገና ላይ እንደሰነበተ ምንጮቹ አስታውቀዋል። በደቡብ ሱዳን በየጊዜው ከሚሰማራው የመከላከያ ሰራዊትና ሰላም አስከባሪ ሃይል የመከላከያ ጄኔራሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከሰራዊቱ እየዘረፉ ኪሳቸው እንደሚያስገቡ የሚታወቅ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን በቅርቡ የምንመለስበት ይሆናል።

Advertisements

Posted on February 14, 2015, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: