የወያኔን የእብሪት ወረራ እስከ መቼ እንሸከማለን!!

በዓለም ታሪክ ውስጥ አምባገነን ገዥዎች ለሥልጣናቸው የሚሰጡት ሕጋዊ ሽፋን ከሁሉም በላይ አዋቂዎች፣ ለሕዝብ
ተቆርቋሪዎች፣የድሆችን እንባ ጠባቂና….

ወዘተ ስለሆነም እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ይሰይማሉ። አንዳንድ
በአመጽ ሥልጣን ላይ የወጡ ቡድኖችና መሪዎች ብዙ ግዛቶችን በጭካኔ አጥቅተው ከያዙ በኋላ ሰው መሆናቸውን
እስከመካድም ደርሰው ነበር። ሆኖም ግን መጨረሻቸው እነሱ እንዳሰቡት ሳይሆን ውጤታቸው ታላቅ ውርደትና
በሕዝብ ዘንድ መጠላትን፣ ውድቀትንና የሕዝብ እልቂትን ከማስከተልና የታሪክ አተላ ከመሆን አላመለጡም፣
አላለፉም። ዛሬ ኢትዮጵያን የሚመራው ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ(ወያኔ) ለይስሙላ እንደሚያናፍሰው ሳይሆን ከመጀመሪያ
ሲመሠረት ታላቁን የትግራይ ሕዝብ ከወገኑና ከሀገሩ ኢትዮጵያ ገንጥሎ በአልባንያ ቅርፅ የተዋቀረች Socialist
Democratic Republic of Tigray ለመመሥረት ነበር። ይህን ጠባብ አላማ የታቀወሙትን የትግራይ ሰዎች በግፍ
አርዷል፣ ብዙዎች ለትምህርት ሄደዋል እየተባለ ቤተሰብ እንኳ በወጉ ሳይቀብራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ በየጣሻው
ወድቀው ቀርተዋል። ለዚህ እኩይ ዓላማ ከሀገሪቱ መደበኛ ጠላቶች ጋር አጥፊ ሴራዎችን በመጎንጎን በትግራይ ሕዝብና
የሃይማኖት ተቅዋማት ላይ እጅግ የረቀቀና ጭካኔ የተሞላበት ግፍና በደል አድርሷል፣ ኢትዮጵያንና ታሪኳን
እናስቀጥላለን በሚሉ የትግራይ ወገኖችና የሃይማኖት መሪዎች ላይ አረመናዊ ጭካኔ ፈጽሟል።
ምንም እንኳ ይህ ሁሉ ግፍ በትግራይ ሕዝብና የእምነት ተቋማት ላይ የተፈጸመ ቢሆንም ዛሬ ያለውን የትግራይን
ሕዝብና የወያኔን ግንኙነት ስንመለከት የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። በተለይ የትግራይ ምሑራን ወያኔን ከመደገፍ አልፈው
ከፋሺስቱ ሙሱሎኒ የተቀዳ የወያኔ በጎሣ የተዋቀረ አገዛዝ አስፈጻሚና ተጠቃሚ በመሆን በእናት አገራቸው ኢትዮጵያ
ላይ ለወደፊት የሚደርሰውን የጎሣ አስተዳደር ጥፋት በጊዜያዊ ጥቅምና ድሎት ለውጠው አገሪቱን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ
እየጣሏት ይገኛል። ይህ በጎሣ፣ በነገድ፣ እየከፋፈሉ አገርን የማጥፋት ዘመቻ የወያኔ አለቆች ተግባር ብቻ ሳይሆን
የትግራይ ምሑራንም ጭምር እየሆነ መጥቷል። በትግራይ ሕዝብ ስም መነገዱ ይቁም ከማለት ይልቅ የትግራይ
ምሑራን አልፈው ተርፈው የወያኔን በዘር የተቀመረ ሥርዓት የሚቃወሙትን በማጣጣል የሚካሄደውን ግፍና ጭካኔ
በመደገፍ በዋናነት ተሰልፈዋል።
ወያኔዎች እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙበት ሕዝብን በመከፋፈል ፣ ልዩነቱ የጠፋ የዘር፣ የጎሣ፣ የሃይማኖት፣ የአውራጃ፣
የቀበሌና የመንደር ልዩነት ግጭቶችን በመፍጠር እርስ በርሳቸው እያፋጁ ሰላምን፣ ልማትን እና ኢትዮጵያዊነትን
ከሕዝብ አርቀው እነሱ የአገሪቱን ሀብት በማጋበስ ከብረዋል።
ወያኔ በዓላማ ያልታገሉለትን የኢትዮጵያ በትረ ሥልጣን በአጋጣሚ ከያዙ 23 ዓመታት ቢያስቆጥሩም ዛሬም
እንደአመሠራረቱ ታላቋን ትግራይ እውን የማድረግ ዓላማ ለማሳካት ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ማለትም በኢኮኖሚ፣
በግዛት ተስፋፊነትና በወታደራዊ አቅም ግንባታ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ፣ ሀፍረትና ይሉኝታ በሌለው
አካሄድ የትግራይን ጎሣ በበላይነት ያማከለ ሥራ አጠናቀዋል።
ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል እንዲሉ ወያኔ ሓርነት ትግራይ፣ ትግራይን ከሚያዋስኑ ክፍለ ሀገራት ከጎንደር፣ ከወሎና አፋር
መጠነ ሰፊ ለም ወረዳዎችን በወረራ ወደ ትግራይ ግዛት አጠቃልለዋል። በተለይ የጎንደር ክፍለ ሀገርን በተመለከት
ወያኔዎች ከሱዳን ጋር የትግራይ ድንበር ለመፍጠር በያዙት እቅድ መሠረት በአካባቢ የሚኖሩት የጎንደር አስተዳደር
ወረዳዎች በተለይ የወልቃይት፣ ጠገዴና ሑመራ አካባቢ ኢትዮጵያውያንን በግፍ አስለቅቀው ለም የእርሻ መሬት
ወረራ ይዘዋል። በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመው ሁሉን አቀፍ ግፍ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፣ በይዘቱ ከኢጣሊያ
ፋሽስት ያላነሰ ግፍ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ ሳይለይ ቀጥሏል። ለዚህም ይመስላል የአካባቢው ህብረተሰብ፡- በሆድም ያላችሁ (የተረገዛችሁ)
በጫንቃም ያላችሁ (የታዘላችሁ) የወያኔን ነገር ትረሱታላችሁ። በማለት የተሰኙት።
ሰሞኑን ደግሞ ወያኔዎች የወረራ አድማስን በማስፋት በአዲስ መልክ በጠገዴ ሠሮቋና በታች አርማጭሆ አብደራፊ
አካባቢ ተጨማሪ ሰፊ የእርሻ መሬት ፍለጋ ዘመቻ ቀጥለዋል።. በትግራይ መንግሥት የሰለጠኑ ሚሊሻዎችና በረከት
ስምዖን የሚመራውና የአማራን ሕዝብ እወክላለሁ በሚለው ሆድ-አደር ብአዴን አስፈጻሚነት የመስፋፋት ዘመቻውን
እውን ለማድረግ በከፋ መልኩ ከፍ ዝቅ እየተባለ ነው። ወረራውን በመቃወም መብታችን ይከበር ያሉትን የሀገሬው
ሰዎች ትግራይ አስልጥነው ባስታጠቋቸው ልዩ ሚሊሻዎች ለማጥቃት ሞረዋል፣ በዚህ ግጭት ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል፣
ውዝግቡም አልበረደም ይቀጥላል።
ወያኔዎች በነደፉት ትግራይን የማስፋፋት አዲስ እና ቀጣይ ዓላማ ካሁን ቀደም በኃይል ይዘው የትግራይ ክልል ነው
ብለው ከወረሩት ዳንሻ ከተማ ወደ ደቡብ ምዕራብ 103 ኪሎ ሜትር በርሃውን አቋርጦ ከአብደራፊ ጋር ለማገናኘት
ብሎም ሰፋፊ የእርሻና የትግራይ ሠፈራ ለማካሄድ ታስቦ ሱር በተባለው የወያኔ የመንገድ ሥራ ድርጅት ጠረጋ
ተጀምሯል። ለዚህ መንገድ ሥራ የሚወጣውን $300 ሚሊዮን ብር ወጪ የኢትዮጵያ መንግሥት መድቧል። በዚህ
ሳያቆም ከሰሜን ወደ ደቡብ የሱዳንን ጠረፍ እያዋሰነ ማለትም ከሑመራ ጫፍ ከልጉዲ ተነስቶ ወደ አብደራፊ
የሚያገናኘው መንገድ በአስፋልት እየተሠራ ነው። የዚህ ወረራ ቅርጽ ሦስት ማዕዘን(Triangle) ቅርጽ የያዘ ሲሆን፣
በዚህ አካሄድ የትግራይ ምድራዊ አቀማመጥ ተቀይሮ በእስራኤልና አረቦች ያለው ካርታ ዓይነት እየሆነ መጥቷል።
ይህም ብቻ ሳይሆን መተማን አልፎ እስከ አባይ ግድብ ድረስ እንሄዳለን የሚል ህልም አላቸው።
ይህ አዲስ ወረራ ለምን አስፈለገ ቢባል፣ ለም የሆነውንና ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን መሬት ወያኔዎች ይዘው ባለቤት
የሆነው የአካባቢው ኑዋሪ ሕዝብ ከውጪ የንግድም ሆነ ሌላ ግንኙነት እንዳይኖረው በብቸኝነት ለመቆጣጠር ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው ዓመት የወያኔ አመራር የነደፈው ትግራይን በ3 ማዕከል የአደራጀ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ
ልማት ለማሳካት አዳዲስ መሬቶች በወረራ መያዝ የግድ ይላል። ይህ የወያኔ ወረራ በአዲስ መልክ የቀድሞው የወያኔ
አለቃ መለሰ ዜናዊ ከሞተ ወዲህ አዲስ ተሰሚነት ያገኘው ስብሃት ነጋ በነደፈው ዕቅድ መሠረት ነው።
የ1967 ዓ. ምን የወያኔ ፕሮግራም መሠረት ያደረገ ስብሃት ነጋ በአዲስ መልክ ትግራይን ተሐድሶ ያስፈልጋታል ብሎ
እየተንቀሳቀሰ ነው። በዕቅዱ መሠረት 3 የትግራይ ዩኒቨርስቲዎችን ማለትም የመቀሌ፣ የአዲግራት እና የአክሱም
ዩኒቨርስቲዎች በዋናነት ተመርጠዋል። በዕቅዱ መሠረት የኬሚካል ኢንጅነሪግን ከአዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር
በማስተሳሰር ደጀና ኬሚካል ኢንዱስትሪ በሚል መቋቋሙን፣ የማእድን ዘርፍ በሽሬ እንዳስላሴና ዓዲዳዕሮን ማዕከል
ያደረገ፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ማዕከልን ደግሞ ዓድዋ በማድረግ ከአክሱም ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሣሰር፣
የብረታብረት ኢንጂነሪንግን እንዲሁ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሳሰር የትኩረት አቅጣጫ ሆነው እንዲሠሩ
እየተንቀሳቀሱ ነው።
ያኔና ተባባሪዎች ግዛትን ለማስፋፋትና ሕዝብን በኃይል ለማፈናቀል ባላቸው ዕቅድ መሠረት በጎንደር ሰሜን-
ምዕራብ ግዛት ጦር ማሥፈር ጀምረዋል። ወያኔዎችና ምሑሮቻቸው ሊገነዘቡት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ አለ፣
የሌሎችን መሬትና ሰላም በወረራ አደፍርሶ የታሰበው የትግራይ ልማት እውን ሊሆን ከቶ አይቻልም። ትርፉ ውርደትና
አጉል የጀብደኝነት ሥራ ሲሆን ውጤቱም አስከፊ ነው። አብሮ ተከባብሮ የሚኖርን እና የሚመሩትን ሕዝብ ሰላምና
አንድነት ኃላፊነት በጎደለው የጀብደኝነት ተግባር ሊያደፈርሱ አይገባም። ከሁሉም በላይ የትግራይ ታላቅነት እና ልማት
በሌሎች ኪሣራ ላይ የተቀመረ ሊሆን አይገባም። በእኛ አመለካከት የትግራይ ሕዝብ እራሱን ከዘረኛው የወያኔ
መንግሥት መለየት አለበት። ይህም ማለት ወያኔ በትግራይ ስም የሚያካሂደውን ተስፋፊነትና ወረራ መቃወም፣ የጎሣ
ፖለቲካን፣ ሚዛናዊ ያልሆነ ዕድገትን እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን በአደባባይ ወጥቶ መቃወም የግድ ይላል።
ወያኔዎች ከዓለም ታሪክ በተለይ ደግሞ በቅርቡ ወደ ታሪክ አመድ ከተለወጠው ሳዳም ሁሴን ተግባር ሊማሩ ይገባል።
ሳዳም ሁሴን ከኩርዶች ግዛት ውስጥ ሰፊ የዘይት ሀብት መኖሩን ሲገነዘብ ልቡ በቅናት ታወረ። ስለሆነም ፕላን አወጣ፣
የንድፉም ዋና ዓላማ የዘይቱን ሀብት ለአረቦች ለማድረግ ነበር፣ ስለሆነም አረቦችን ወደ ቦታው በስፋት አሰፈረ፣
አረቦችም ከኩርዶች በቁጥር እንዲበልጡ አደረገ። ከዚያም አዋጅ አውጥቶ የሕዝብ ቆጠራ አካሂዶ አረቦች ስለበለጡ
የዘይት ክምችት ያለበት ቦታ የአረቦች ክልል ነው ሲል በአዋጅ አጸደቀ። ኩርዶች አዘኑ፣ አቤት ቢሉም ሰሚ ጠፋ። ከ40
ዓመት በኋላ ሳዳም ሲወገድ ብዙ ግፍ በሥፍራው በሰፈሩት አረቦች ላይ ደረሰ፣ አረቦችም ንብረታቸው ወደመ፣
የኩርድን ቦታ ለቀው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነው በመጠለያ በእርዳታ መኖር ጀመሩ። በአረቦችና ኩርዶች መካከል
ሰላም ጠፋ።
የትግራይ ሕዝብ እንደማንኛውም ዜጋ በመረጠው አካባቢ መኖር ይችላል፣ ነገር ግን የሰፈረበትን ቦታ ሁሉ የትግራይ
ግዛት የማድረግ ሥራና ዓላማ ከኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ውጪ ነው። የትግራይ ሕዝብበስሙደላሎችሲደልሉና ከወገኑ
ጋር ሆድና ጀርባ ሲያደርጉት መቃወም አለበት፣የለም እኔን አትወክለኝም፣ ወክለኝም አላልኩም ሲል ድምፁን ማሰማት
አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ወያኔ በትግራይ ስም እንዳሻው መስፋፋቱን ከቀጠለ ውጤቱ ምን እንደሚሆን ከወዲህ
መገመት ይቻላል። ጥሩ እንደማይሆን ደግሞ በእርግጠኝነት መተንበይ ይቻላል። የወያኔ ምሑራኖች እና ገዥዎች የእኛ
ጩኸት ብዙ ጊዜ እንደምታስቡት በወገናችን በትግራይ ሕዝብ ላይ ጥላቻ ኖሮን ሳይሆን የእናንተን የእብሪት ወረራ
ወገናችን መሸከም ከማይችልበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ፣ ጩኸቱም ከምድር አልፎ ሰማይ ድረስ እየተሰማ ስለሆነ ብቻ
ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ23 ዓመታት የወያኔን እኩይ ተግባር በትእግስት ቢያሳልፍም ወያኔዎች ግፍና ጸረ ኢትዮጵያዊነትን
በከፋ መልኩ ቀጥለዋል። ወያኔዎች ኢትዮጵያ የምትባል እንደ አገር መኖርን እስካላቆመች ድረስ የጥፋት ዘመቻቸውን
አያቆሙም። የወያኔ ተግባር የአውሬውን የዝንጀሮን ይመስላል። ዝንጀሮ ከእህል ክምር ውስጥ ገብቶ ሆዱ ቢሞላም
ለሌሎች እንዳይተርፍ በማሰብ ክምሩን እንዳልነበረ አድርጎ ያፈራርሳል። ወያኔዎችም ለመርዘኛ እቅዳቸው
ተግባራዊነት አገሪቱን እየከፋፈሉ፣ እያጋጩና እየቆራረሱ ይገኛሉ። ለዚህም ነው ከሑመራ ጀምሮ በርዝመቱ 1600
ኪሎ ሜትር እና ከ30–50 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለውን ለም የጠረፍ መሬት ለሱዳን በሥጦታ መልክ እያስረከቡ
የሚገኙት።
ያለው አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው። አገራችን ከመጥፋቷ በፊት ወያኔ መጥፋት አለበት።ወያኔ በሰላም፣ በአቤቱታ
አይወገድም። ወያኔ ሊወገድ የሚችለው በተባበረ ኃይል ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
ሊቁ እጅጉ አዳነ አጣናው

Posted on March 15, 2015, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: