በአርበኞች ግንቦት 7 ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!

ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል..

በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ። አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የገነባው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አመራር በዘር የተደራጀ በመሆኑ የሕዝቡን አጠቃላይ ብሶት ደግፎ ሊቆም ይችላል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሠራዊቱ እንደ ተቋም ከተበደለው ሕዝብ ጎን እንዲቆም በመጀመሪያ በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ አለበት። በዚህ አቅጣጫ የሚሠሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ሠራዊቱ ዘረኛ ገዢዎቹን አስወግዶ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም፣ አይገባምም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት በሕዝባዊ አመጽ መታገዝ አለበት የሚለው ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ ተመራጭ እንዲሆን ያደረገው ዋነኛ ምክንያት የሠራዊቱ ዘረኛ አወቃቀር ነው።
በመረጥነው የትግል ስትራቴጂ መሠረት በሁለቱም ግንባሮች – ማለትም፣ በሕዝባዊ አመጽ እና በሕዝባዊ እምቢተኝነት ግንባሮች ሥራዎች መሠራት አለባቸው። ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ እምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ እንዲያደርሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁለቱም የትግል ስትራቴጂዎች አኳያ መደራጀት ይኖርበታል። ሕዝባዊ የአርበኛ ሠራዊት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ሁሉ በኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች፤ በሥራና በመኖሪያ አካባቢዎች በምስጢር የተደራጁ ሕዝባዊ የአርበኛ ሲቪል ክበቦችም በብዛት መደራጀት ይኖርባቸዋል።
በዚህም ምክንያት አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ከህወሓት ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲደራጅ ጥሪ ያቀርባል! እያንዳንዱ ነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ከሚያምነውና ከሚመስለው ወዳጁ ጋር ይቧደን፤ ቡድኑንም በሥርዓትና በሚስጢር ያደራጅ። ከእንግዲህ «ምን እንሥራ? ትግሉን እንዴት እንርዳ?» እያሉ ለሚጠይቁ ወገኖቻችን በሙሉ መልሳችን «ከቻላችሁ ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ» የሚል ነው። ድርጅት ኃይል ነው። መደራጀት በራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ድርጅት ድርጅት የሚሆነው ደግሞ በሥርዓት ሲዋቀርና በሥነ ሥርዓት ሲመራ ነው። ስለሆነም ነፃነት ናፋቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ አደራጅና አስተባባሪ እንዲመጣለት ሳይጠብቅ በራስ አነሳሽነት እንዲደራጅ ይህ ጥሪ ተላልፏል። በሥርዓት የተደራጀ ስብስብ ሲኖር የሚሠራ ሞልቷል። ይህንን መንገርም አያስፈልግም። የተደራጀ ስብስብ ራሱ ሥራዎችን አቅዶ መሥራትም ይችላል። የሚከተሉት ነጥቦች ለአብነት ተዘርዝረዋል..
1. የተደራጀ ስብስብ ጠላትና ወዳጁን ይለያል። የጠላቱን ጥንካሬና ድክመቱን ከራሱ ጥንካሬና ድክመት ጋር መዝኖ የወገን ኃይልን ጥንካሬ የሚያጎለብቱ፤ ድክመቶቹን የሚቀንሱ እርምጃዎችን በመውሰድ አቅሙን ይገነባል።
2. የተደራጀ ስብስብ የጠላትን እንቅስቃሴ እየሰለለ መረጃ ለነፃነት ኃይሎች እንዲደርስ ያደርጋል።
3. የተደራጀ ስብስብ የተቀናጀ የሕዝባዊ እንቢተኝነት ተግባራትን ይፈጽማል። ለምሳሌ፣ በሥርዓቱ የደረሰበትን ምሬት በወረቀት ገንዘብ፣ በአስፋልት፣ በታክሲዎችና በግድግዳዎች ላይ ይጽፋል፤ ገንዘቡን የኤፈርት ንብረት ከሆነው ውጋጋን ባንክ ያስወጣል፤ መዋጮዎችና ግብር ያጓትታል ከዚያም አልፎ አልከፍልም ይላል።
4. የተደራጀ ስብስብ በሥርዓቱ ላይ ለማመጽ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። ሁኔታች ተሟልተው አመጽ ሲቀሰቅስ ደግሞ ትግሉ ግቡን ሳይመታ እንዳይበርድ ፀንቶ ይቆማል።
5. የተደራጀ ስብስብ ወዳጆቹን አስተባብሮ በጥንካሬው ላይ ተመርኩዞ በአካባቢው ባለ የህወሓት ኃይል ላይ ክንዱን ያነሳል።
በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባባሪና መመሪያ የሚጠብቅበት ጊዜ አልፏል። ህወሓት የዘረጋው የአፈና ሥርዓት የጠበቀ ትስስርና ቁጥጥር ያለው ድርጅት ማቆም እንዳይቻል አድርጓል። ስለሆነም ያለን አማራጭ በርካታ ያለዘወትር የበላይ አካል ክትትል ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉ ስብስቦችን በመላው የአገራችን ክፍሎች በአፋጣኝ ማደራጀት ነው። ይህንን ደግሞ ማድረግ ይቻላል። ወቅቱ ህወሓትን ከጫንቃችን ላይ ለማውረድ የምንደራጅበት ነው። ድርጅት ኃይል ነው፤ አደራጅና አስተባባሪ ሳንጠብቅ በራስ ተነሳሽነት ዛሬውን እንደራጅ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Posted on March 23, 2015, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: