ኢትዮጵያኖቹ በ ISIS ሲገደሉ በግድ እንዲያይ የተደረገው ታዳጊ ህፃን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) የ16 ዓመቱ ኤርትራዊ ስደተኛ ናኤል ጎይቶም የኤይ ኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑን እና ኤርትራውያኑን በግፍ ሲቀሉ እና ሲረሸኑ እንዲመለከት መደረጉን ይናገራል…

ታዳጊው ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ከተሰኘው ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደተናገረው፥ ታጣቂው የአይ ኤስ ቡድን ይህን አሰቃቂ ድርጊት አስገድዶ እንዲመለከት አድርጎታል።

ይህ አሰቃቂ ድርጊት ከተከናወነ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከሌሎች አራት ኤርትራውያን ጋር በሊቢያ ታስረውበት ከነበረው ካምፕ ማምለጣቸውንም ተናግሯል።

በእዚህ አረመኔ ቡድን ከመቀላት ለማመለጥ መሞከር አዋጭ መሆኑን የተናገረው ናኤል፥ ከቡድኑ ካምፕ ካመለጡ በኋላ እርዳታ የሚያገኙበት ስፍራ እስኪደርሱ ድረስ ለአራት ቀናት ያህል በሊቢያ በረሃ ውስጥ መጓዛቸውን ይተርካል።

ከአንድ ወር ለሚበልጥ ጊዜ በፅንፈኛው አይ ኤስ ቁጥጥር ስር በነበሩበት ወቅትም “ከመሞት እና እስልምናን ከመቀበል የቱን ትመርጣላችሁ”? የሚል ምርጫ እንደተቀመጠላቸው እና በወቅቱ ሙስሊም መሆንን እንደሚመርጡ እና እንዋጋላችኋለን ሲሉ መናገራቸውንም ያስታውሳል ታዳጊው።

ናኤል ኢትዮጵያውያኑ እና ኤርትራውያኑ በአይ ኤሴስ ከተያዙ በኋላ በአንድ ትልቅ ጉድጓድ መቀመጣቸውንም ተናግሯል ።

ከእለታት በአንዱ ቀንም 47 ያህል ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን ጥቋቁር እና ብርቱካናማ ልብሶችን አልብሰው ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ እንዲሁም ሊቢያ በረሃ እንደወሰዷቸው እና እሱም ይህን ይመለከት ዘንድ አብሯቸው እንደወሰዱት ከዚያም ይህን ጭካኔ የተመላበት ድርጊት እንዲመለከት መደረጉንም ይናገራል።

ታዳጊው በአይ ኤስ እንዴት ተያዘ?

ናኤል እንዴት በፅንፈኛው የአይ ኤስ እጅ እንደተያዘም ያብራራ ሲሆን፥ 10 ኤርትራውያን ሴቶችን እና 8 ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 61 ከሚሆኑ ስደተኞች ጋር ከአንድ ወር በፊት በሱዳን አድርግው ደቡብ ሊቢያን ሲያቋርጡ በአይ ኤስ ታጣቂዎች መያዛቸውን እና ሀይማኖት ነክ ጥያቄዎች መጠየቃቸውን ያስታውሳል።

ከመካከላችሁ ማን ነው ሙስሊም? ብለው እንደጠየቋቸው ነገር ግን ክርስቲያን የሆንነው መስቀል እና ክርስቲያን መሆናችንን የሚያሳዩ መንፈሳዊ ምስሎችን በመያዛችን በወቅቱ ማንነታቸንን መደበቅ አላስቻለንም ብሏል።

በአይ ኤስ ካምፕ ውስጥ ከ300 እስከ 400 የሚሆኑ የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሚገኙ ሲሆን፥ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ተይዘው በካምፑ ውስጥ እንዲገቡ ሲደረግ፣ ሶማሊያውያን ግን መሄድ ወደፈለጉበት እንዲጓዙ ይፈቀድላቸው እንደነበር ይተርካል።

ናኤል ኤይ ኤስን አስቀድመው የተቀላቀሉ እና ለሽብር ቡድኑ የሚዋጉ ሶስት ኤርትራውያን የነበሩ ሲሆን፥ እነሱ ይረዱናል ብለን ስንጠብ ግን ስለኛ ምንም ስሜት አልተሰማቸውም ሲል ታሪኩን ያወጋል።

ናኤልን ጨምሮ ዮሃንስ መብራቱ፣ ቶማስ ገብረህይወት፣ አብርሃም ናይዝጊ፣ አማን ሺሻይ የተሰኙ ታዳጊ ኤርትራውያንም ከአይ ኤስ ካመለጡ እና ከአራት ቀናት አድካሚ የበረሃ ጉዞ በኋላ አንድ ሱዳናዊ አግኝቷቸው በሰሃራ በረሃ በርካታ ስደተኞች ወደሚገኙበት የስደተኞች መጠለያ እንዳደረሳቸው ገልጿል።

ታዳጊው ህይወቱን ማትረፍ ቢችልም ባየው እና በደረሰበት መከራ እና እንግልት ሳቢያ ውስጡ መጎዳቱን ነው የተናገረው።

አይ ኤስ ከ30 ደቂቃ በማያንስ የተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በአለም ዙሪያ ባሰራጨው መልዕክቱ 30 ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ንፁሃን ዜጎችን ገሚሱን በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ሲቀላ፥ ገሚሱን ደግሞ በሊቢያ በረሃ በጥይት በመተኮስ ሲገድል ማሳየቱ ይታወሳል።
ምንጭ፦ http://www.ibtimes.co.uk

Posted on April 23, 2015, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: