አውሬዎቹ ISIS ሶች ዛሬ በለቀቁት የ 9 ደቂቃ ቪዲዮ የሁቲ አማጽያንን አንገት ልንቆርጥ የመን ገብተናል ሲሉ ዝተዋል። ዝርዝሩን ከታች ያስቀመጥኩት ሊንክ በመጠቀም አንብቡት።

ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ በየመን የሚኖሩ አያሌ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ መውሰድ መጀመር ይኖርባቸዋል። እግዚኦ! ከስቃይ ላይ ሌላ ስቃይ ፈታኝና አስፈሪ ጊዜ እየመጣብን ነው። በየመን ደራሽ ላጡት ወገኖቻችን ደህንነት ተግተን መጸለያችንን አናቋርጥ!! በየመን የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ነቅታችሁ ራሳቸውን ጠብቁ አደራ። ቢቻል በሕብረት እና በአንድነት የምትኖሩበትንና የምትንቀሳቀሱበትን መንገድ አመቻቹ። በተለይ ደግሞ ለአደጋ ሊያጋልጡ ወደ ሚችሉ አስፈሪ ቦታዎች እንዲሁም ወደ ገጠራማ አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ ታቀቡ። እናንተም ለጥንቃቄ ይጠቅማቸዋል የምትሉትን መልዕክት ሼር በምታደርጉበት ጊዜ አስቀምጡላቸው።