Monthly Archives: July 2016

ጎጃም-መተከል:- አማራው ተፈናቅሎ ለትግራይ ባለሀብቶች ሰፋፊ የእርሻ መሬት የሚሰጥበት ምድር!

መተከል አውራጃ ጎጃም ውስጥ ከነበሩ አውራጃዎች አንዱ ነበር። ጎጃም እንደመሆኑ መጠን በአብዛኛው አማራ የሚኖርበት ምድር ነው። በተጨማሪም አገው፣ ሽናሻ፣ ጉምዝና ኦሮሞም ይኖርበታል። በዘመነ ወያኔ ይህ አውራጃ ለሁለት ክልሎች ተሰነጠቀ። «አዊ ዞን» የሚባል ተፈጥሮ ወደ አማራ ክልል ውስጥ ሲካተት የተቀረው ደግሞ «መተከል ዞን» ተብሎ ቤንሻንጉል ክልል ሆነ። ሆኖም ግን አዊም ሆነ መተከል ዞን ውስጥ ዛሬም ድረስ በብዛት የሚኖረው አማራና አገው ነው። (more…)

የወያኔ ደጋፊ ትግራውያን እና ባንዳወች መጋፈጥ ግድ ያለባቸው እውነታ

በህወዓት ትግራይ ፉፁም አድሎዓዊ እና ጨቋኝ ስርዓት የተንገፈገፉት ኢትዮጵያውያን የግፉ ቁና ሲሞላባቸው ወያኔን ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀነው እንሙት ብለው መቁረጣቸው የአደባባይ ሃቅ ሆኗል። በሁለት ጀንበር በጎንደር ያየነው እጅግ የከረረ ውጤት ተኮር ተግባራዊ ትግል ያስተማረን ነገር ካለ መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያ ፋሺስት ወያኔወች እና ባንዳወች እጅግ የከፋ ለመሆኑ ነብይ መሆንን አይጠይቅም።

እኛን ከነካቹህን ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ሶሪያ ትሆናለች የሚለው የህወዓት ፕሮፓጋንዳ ህዝቡ “ጨው ለራስህ ስትል ጣፉጥ…” በኢትዮጵያ መፉረስ ይበልጥ ሊጎዳ የሚችለው ማን እንደሆነ በተግባር ታዮታላቹህ እንጂ ሃጎስ እየገደለ፣እየዘረፈ እና እያሰረ የሚኖርባት አገር የሯሷ ጉዳይ ብሎ በመኖር እና ባለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን የኢትዮጵያ ህዝብ አምርሮ እየተናገረ ይገኛል።

ሃጎሶችም የትእቢት ጣሪያው ላይ በመድረሳቸው ጀሮ ዳባ ልበስ ብለው ተንኮላቸውን ቀጥለውበታል። በዚች ሰዓት በሁሉም አቅጣጫ አርግዞ ያለው ቂም እና ጥላቻ ሊሸመግሉ የሚችሉ አባቶችን ሁሉ ወያኔ ጨርሶ በማጥፋቱ ሽማግሌ እና መካሪ ያጣች አገር ለመሆኗ የአደባባይ ሃቅ ነው።

እናም እናንተ ከእኛ በላይ ላሳር ብላቹህ የተወጠራቹህ የፉሺስቱ ወያኔ ደጋፊወች፣አሽቃባጮች፣ሆድ አደሮች እና ጠባቂወች ሁሉ ይህ በኢትዮጵያ ያንዣበበው የቂም እና ቁጭት ድባብ ወዴት እያመራ እንደሆነ ተገንዝባቹህ መላ መፈለግ ሞኝነት ሳይሆን ብልህነት፣ተሸናፊነት ሳይሆን አሸናፊነት መሆኑን ተረዱ።

%d bloggers like this: