ጎጃም-መተከል:- አማራው ተፈናቅሎ ለትግራይ ባለሀብቶች ሰፋፊ የእርሻ መሬት የሚሰጥበት ምድር!

መተከል አውራጃ ጎጃም ውስጥ ከነበሩ አውራጃዎች አንዱ ነበር። ጎጃም እንደመሆኑ መጠን በአብዛኛው አማራ የሚኖርበት ምድር ነው። በተጨማሪም አገው፣ ሽናሻ፣ ጉምዝና ኦሮሞም ይኖርበታል። በዘመነ ወያኔ ይህ አውራጃ ለሁለት ክልሎች ተሰነጠቀ። «አዊ ዞን» የሚባል ተፈጥሮ ወደ አማራ ክልል ውስጥ ሲካተት የተቀረው ደግሞ «መተከል ዞን» ተብሎ ቤንሻንጉል ክልል ሆነ። ሆኖም ግን አዊም ሆነ መተከል ዞን ውስጥ ዛሬም ድረስ በብዛት የሚኖረው አማራና አገው ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲስ ከመተከል ዞን ውስጥ አማራዎች «ወደ አገራችሁ ሂዱ» እየተባሉ እየተፈናቀሉ ይገኛሉ። አሁንም ልብ በሉ — ጎጃምን ከፍለው ቤኒሻንጉል ክልል አደረጉት እንጂ መተከል ጎጃም ነው። ከዚያም አማራዎችን «ወደ አገራችሁ ሂዱ» ብለው አፈናቀሏቸው። አማራው በአገሩ አገር እንደሌለው ጎጃም መተከል ውስጥ ከተፈጠረው ሁኔታ በላይ ሊያሳየው የሚችል ነገር ያለ አይመስለኝም።

መተከል ዞን ውስጥ ሰባት ወረዳዎች አሉ። ድባጤ፣ ቡለን፣ ወንበራ፣ ማንዱራ፣ ግልገል በለስ፣ ፓዌ፣ ማንቡክና ማንኩሽ ይባላሉ።

መተከል ከጥንትም ጎጃም ነው፤ አሁንም አብዛኛው አማራ ነው። በተለይ ግልገል በለስ፣ ፓዌ፣ ማንቡክና ማንኩሽ ከሌላው ጎጃም በሁለም ነገር ተመሳሳይ ነው።
ለምን ሌላ ክልል እንደሆነ ቢያስረዷችሁም የሚገባችሁ አይመስለኝም። ሁለት ምክንያት ግን አሉ። አንደኛው አማራው አማራን ለማዳከም ሆን ተብሎ የጎነጎነ ሴራ ሲሆን ሁለኛው ደግሞ ቦታው ለም ስለሆነ መሬቱ ለትግራይ ባለሀብቶች ተፈልጎ ነው።

ትንጋጉ ጋዜጠኛ Muluken Tesfaw በቅርብ በሚወጣው መጽሀፉ መተከል ውስጥ በአማሮች ላይ ስለደረሰባቸው ግፍና ሰቆቃ በስፋት ይነግረናል።

ዛሬ የመተከል መሬት በሙሉ ትራክተር በያዙ ትግሬዎች ተወሯል። መቀሌና መተከልን መለየት አይቻልም። ከትንሽ እስከ ትልቅ ምግብ ቤቶች የሚወራው ትግርኛ ነው። የትግራይ ጄኔራሎችና ዘመዶቻቸው ጠቅልለው መተከል ዘምተዋል። መተከል ካፍ እስከ ደገፉ ትራክተር ይዘው በገቡ የትግራይ ጀኔራሎች ጢም ብላለች። አማራውን የተፈናቀለበትን ያን ለም የጎጃም መሬት የትግራይ ባለሀብቶች እያረሱት ነው።

ወጣቱ ሆይ! መተከል ጎጃም ክፍለ ሃገር ውስጥ ነበር። የአማራዎች ምድር ነው። ታሪካዊ ይዞታችን ነው። ወያኔ መጣና ቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ አካተተው። ይሆም የሆነበት አማራዎችን ከአገራችን ውጡ እያሉ ተራ በተራ በማፈናቀል ያን ለም መሬት ለትግራይ ባለሃብቶች ለመስጠት ነው። የሆነው ይሄ ነው። ዛሬም የትግራይ ሰዎች ከአውሮፓና ከአሜሪካ እየተጠሩ ከልማት ባንክ ያሻቸውን ገንዘብ በመዛቅ ትራክተር ከኤፌርት ገዝተው መተከልእየገቡ ነው።

ጎጃም-መተከል አማራው ተፈናቅሎ የትግራይ ባለሀብቶች ሰፋፊ እርሻ የሚሰጥበት ምድር!

በአቻምየለህ

Posted on July 26, 2016, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: