Monthly Archives: August 2016

“ቧ! አታ… ከማና ጥኡያት ኢዮም” (“ለካስ ‘እነዚህ አማራዎች’ እንደኛ ጥሩ ሰዎች ናቸው”) – See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16854/#sthash.BVC3veTF.dpuf

ታፈሰ ወርቁ –

ህወሃት ትግራይን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ፣ ገና “የጎንደርን ጦር ደረመሰ፣ ሃሙሲት ደረሰ፣ ጎጃምን አዳረሰ … ይባል በነበረበት ጊዜ፣ አ.አ ከመግባቱ በፊት በጎጃም ትንሿ የዳንግላ ከተማ ውስጥ ስራ ላይ ነበርኩ። በአንድ ሱቅ ውስጥ እቃ ልገዛ ቆሜአለሁ። ወዲያው አንድ የህወሃት ታጣቂ ሱቁ ውስጥ ገባ። አማርኛ አይችልም። ግን እንደ ምንም እየሰባበረም፣ በጥቅሻም ቢሆን ሲጋራ ለመግዛት መፈለጉን ለባለሱቁ ገልጾ የጠየቀውን አገኘ። ጥቂት ቆይቶ አሁን የማላስታውሰውን ነገር በተሰባበረ አማርኛ ተናገረ። ሁለቱ አልተግባቡም። ግራ መጋባታቸውን አይቼ ጣልቃ ገባሁ፣ እና ለሁለቱም ማስተርጎም ጀመርኩ። ሁለቱም ደስ አላቸው። እናም ወሬያችን ደራ። ያ የህወሃት ታጣቂ፣ በጫወታችን መሃል፣ እግራቸው በረገጠበት በአብዛኛው የጎንደር እና ጎጃም ገጠር እና ከተማ ውስጥ ሁሉ ያለው ህዝብ ቤቱ እያስገባ ያበላ ያጠጣቸው እንደነበር የነገረኝን እና በመጨረሻም “ቧ! አታ… እዚአቶም ከማና ጥኡያት ኢዮም” (አንተ! ለካስ እነዚህ [አማራዎች] እንደኛ ጥሩ ሰዎች ናቸው) ያለኝን ሳስበው… ከዚያም ጋር ህወሃት ጫካ ውስጥ ሆኖ፣ አዲስ አበባም ገብቶ አገረ-ገዢ ሆኖ በቆየበት ጊዜ ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ የዘራው የጥላቻ ዘር በቅሎ፣ ተባዝቶ፣ ጎምርቶ እና ለምርት ደረሶ… ህዝቡን በጅምላ እየገደለ እና እያስገደለ፣ በበሽታ እና ድህነት በማፈናቀል እና በጅምላ ግድያ አማራውን እየፈጀ እስካሁን አለ። (more…)

ልፎክር ላገሬ! (ይፍሩ ኃይሉ

ይፍሩ ኃይሉ

“በፈረስ የፈለጉት፤ በዕግር ይገኛል” እንደሚሉ፤ከሃያ አምስት ዓመት በላይ፤በየኢምባሲው፤በዓለም ዙሪያ ዋና ዋና ከተማዎች፤እየዞርን፤ኧረ አለቅን! ኧረ የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራና ስቃይ ተመልከቱን! በዕርዳታ ስም እያላችሁ፤ለገዳዮቻችን፤መትረየስ ከነጥይቱ አትስጡብን! እያልን ጉሮሮአችን እስኪነቃ ድረስ ጮኸን ያላገኘነውን፤ የዓልምን መንግሥታትና የሕዝባቸውን የሚያዳምጥ ጆሮ፤የሚመለከት ዓይን፤ጀግናው አትሌታችን፤ ፈይሣ ለሌሳ፤ብቻውን፤ሁለት እጆቹን አጣምሮ ወደላይ በማንሣት፤ ብቻ፤ዓለም ትኩር ብሎ እንዲያየው አድርጎታል። አሁን ገና፤ዕውነተኛው የአገራችን ወቅታዊ ሁኒታ፤አድማጭና ተመልካች አግኝቷል። የባለ ዝናዎቹ፤የነገረሱ ዱኪ፤የነአብዲሳ አጋ፤የነ ሙሉጌታ ቡሌ፤እንደዚሁም ስፍር ቁጥር የሌላቸው፤የናት አገርህ የኢትዮጵያ ጀግኖች፤ከመቃብር ቀና ብለው፤ ጎሽ ልጃችን! እንደዚህ ነው ጀግና!ይሉሃል። ስመጥሩው አርበኛ፤ክቡር ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ፤ከተያዙበት የአልጋ ቁራኛ፤ ቀና ብለው፤በለሰለሰ ድምጻቸው፤ “የኢትዮጵያ አምላክ፤ ይባርክህ፤ይጠብቅህ! ሳልሞት ይህን አሳየኸኝ፤ስለዚህም ኮራሁብህ!” ይሉሃል። በሚሊዮን ከሚቆጠሩ፤ ኢትዮጵያውያን ወገኖችህ መሃል አንዱ ስለሆንኩ፤በኩራትና በደስታ ተሞልቼ፤ “ማነው ጀግና ጠፋ ያለው!” እያልኩ እኔም እፎክራለሁ።አየህ ወንድሜ! ጀግና ሲነሳ የሚከተለው መዓት ነው። ከእንግዲህ ወዲህ፤ የኢትዮጵያን አትሌቶችና ባለሙያዎች አስተሳሰብ፤ 180 ዲግሪ ለውጠኸዋል። ምሳሌ ሆነሃል። ስምህ በታሪክ ማሕደር ዉስጥ በክብር ተመዝግቧል። እኔም ባለሁበት ሆኜ ነዎር( አርካ ፉኔ) ብያለሁ።እንዲያውም ከማስታወስ ኮሮጂዬ ዉስጥ አንዲት ግጥም ይቺውልህ። (more…)

አዲስ አበባዎች ይነቅላሉ (ዳዊት ዳባ)

ዳዊት ዳባ

የሌሊሳ ተግባር ጀግንነት ነው። ድረጊቱ ትግሉ ላይ ያስገኘው ጠቀሜታ እስካሁን ከተባለለትም የላቀ ነው። ደስታዬንና ምስጋናዬን ለመገለፅ ቃላት የለኝም ። የኢሳት የእስፖርት ጋዜጠኛ ወንድማገኘው እንዲሁ ምስጋና ይገባሀል። ከአምት በፊት ያን ዝግጅትህን ሳዳምጥ እጅግ አድርጌ መውደድ ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን የወንድም ሌሊሳ አይነት ጀግንነት እንደሚሆን ቀድሜ አይቼበታለው። ሰውዝ አፍሪካ ላይ የአለም ዋንጫ ሲደረግ መልካም አጋጣሚ ነበር። “እነሱም እኛም እስፖርቱን ለፖለቲካ {ለኛ ለትግል} ላንጠቀምበት ተስማማን “ የሚለውን ስሰማ አንጀቴ ነበር የተቃጠለው። (more…)

የወልቃይት ጥየቄ ሕገ መንግሥታዊነት (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ መነሳት የጀመረበት ገዜ ጠያቂዎቹ እንደሚሉት ከወያኔ የሥልጣን እድሜ በላይ ነው፡፡ ስሙን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ብሎ ዓላማውን ተግራይን ነጻ ማውጣት አደርጎ የተነሳው ቡድን በለስ ቀንቶት ትግራይን መቆጣጠር ሲችል ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ወደ ቀሪው የኢትዮጵይ ክፍል መስፋፋትን ነው የመረጠው፡፡ አንደኛው ምክንያት ማሸነፍ ከተቻለ በትግራይ ሳይወሰኑ ማእከላዊ ሥልጣን ለመያዝ ሁለተኛው ደግሞ “ነጻ ሊያወጧት የታገሉላትን” ትግራይ ግዛት ለም መሬቶቸን በማጠቃለል ማስፋት ናቸው፡፡ የትግራይ አጎራባጅ የሆኑት ለም የጎንደርና የወሎ ወረዳዎች በወረራ የተያዙት ወያኔ ምንይልክ ቤተ መንግሥት ሳይደርስ ነው፡፡ ይህን ወረራ ዜጎች በዝምታ አልተመለከቱም በእሽታ አልተቀበሉም፣ ነገር ግን ወያኔ አንደም በጡንቻ ሁለትም በህግ ሽፋን በወሰዳቸው የማሰር የመግደልና የመሰወር ርምጃ ተቃውሞውን ለማዳን ችሎ ነበር፡፡ (more…)

«AmOr!» «አሞር!» – የአምባገነኑን የህውሀት/ወያኔን ስርአት ውድቀት የሚያፋጥን የህዝብ ድምጽ ይሆን?

ልዑልሰገድ ወልደየስ ሂርጳ

«AmOr!» «አሞር – የአምባገነኑን የህውሀት/ወያኔን ስርአት ውድቀት የሚያፋጥን የህዝብ ድምጽ ይሆን? (Could «AmOr» will be the final nail in the coffin of TPLF?)

ወደ ዋናው ርዕሴ ከመግባቴ በፊት በቅድሚያ በወያኔ ጥይት በቅርቡ በግፍ ለረገፉት የአገራችን ጀግና ወጣቶች ጥልቅ የሆነ ሀዘኔን እየገለጽኩ፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ፍትህ፤ ዲሞክራሲና ነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ እግዚአብሔር መጽናናቱን እንዲሰጠው ከልብ እመኛለሁ፡፡

ከዛሬ 18-19 ዓመት በፊት ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን (ነፍሳቸውን ይማረውና) በአንድ የአውሮፓ ዋና ከተማ ላይ በተደረገ ትልቅ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የተናገሩትን ምንግዜም አስታውሰዋለሁ፡፡ (more…)

ወልቃይት፣ ያሬድ ጥበቡና ጄኔራል ጻድቃን (በፍቃዱ ደረጀ)

በፍቃዱ ደረጀ

  • ጻድቃን እንደ እኛ ሊያስብ ይችላል፣
  • ህጋዊ ማእቀፎችን እንጠቀም፣
  • አዲስ አበባ አድጋለች መጎብኘት ባልችልም፣
  • የመለስ ጥሩ ስራ ህወሀትን ከሌሎች ድርጅቶች እኩል አድርጎት መሄዱ ነው

ያሬድ ጥበቡ ኢህዴን የተባለውን ብአዴን ከመሰረቱ ግለሰቦች አንዱ ነበር ሲታገል ሲታገል ቆየና ከእለታት አንድ ቀን የአመት እረፍት ተሰጠው ይህንን የእረፍት ጊዜውን በዋና እንደሚያሰልፍ ቀድሞ የተረዳው ወዲ ዜናዊ ተከዜ ላይ ለምን አንዋኝም ሲል ግብዣ አቀረበለት ሳያቅማማ ተቀበለው የመለስ ዜናዊ ጦር እየወጋው ቢሆንም ያሬድ አንዳች ነገር ሳይሰማው ወደ ተከዜ ወንዝ ተጓዘ እንደደረሱም ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ከዛሬ ጀምሮ የኢህዴን አመራር አይደለህም ሁለት ምርጫዎች አቀረበለት… ብርሀኑ ነጋ የሄደበትን መንገድ መርጦም በፓርት ሱዳን አድርጎ ዲሲ መኖር ከጀመረ 30 አመት ሊሞላው የጳጉሜን መጥባት እየተጠባበቀ ነው። (more…)

ኢትዮጵያ፡ ከጭፍን የፖለቲካ ጥላቻ ባሻገር (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የእምነቴ መርሆዎች፡ በአሁኑ ጊዜ ጥላቻ በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በነጻነት፣ በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብት ጥበቃ የተፈረከሰከሰ ግድግዳ መካከል የቆመ ነገር ሆኖ ይገኛል፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ጥላቻን የፖለቲካ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርጎት ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት እየተቀነቀነ ያለው የጭቃ ግድግዳ ጥላቻ በሕዝባዊ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አመጽ ዶግ አመድ እየሆነ በየቦታው ባስደማሚ ሁኔታ በራሱ በዘ-ህወሀት ላይ በመፈረካከስ ላይ ይገኛል፡፡ ክልሎች (የዘ-ህወሀት የአፓርታይድ ባንቱስታንስ አቻ) እንደበረዶ ሲሟሙ እንደ ቅቤ ሲቀልጡ በዓይናችን በብረቱ በመመልከት ላይ እንገኛለን፡፡ ዘ-ህወሀት ላለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል ስልጣንን ጠቅልሎ በስልጣን ማማ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ እንዲቆይ ያደረገው ዋና ምክንያት ጭፍን የጎሳ እና የኃይማኖት ጽንፈኝነት የፖለቲካ ጥላቻን ሲያራግብ በመቆየቱ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በየቦታው ከዘ-ህወሀት የክልል እስር ቤት በሮችን በሰላማዊ አመጽ እየሰበሩ በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ጀግኖቹ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በጥላቻ ጌቶች ላይ በአስደማሚ ሁኔታ በማመጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ (more…)

Home » ጦማሮች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም… » ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው! (ከይገርማል) ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው! (ከይገርማል)

ከይገርማል

አንዳንድ ሰዎች “ለምን ትግሬወችን ከወያኔ ጋር አዳብላችሁ ትወነጅላላችሁ?” ብለው ሲቆጡ አንዳንዴም ሲሳደቡ እያየን: እየሰማን: የጻፉትንም እያነበብን ነው:: እነዚህ ሰዎች ከሁለት የተለያዩ አቅጣጫወች የተነሱ ሊሆኑ ይችላሉ::

የመጀመሪያወቹ የመንግስትን አስነዋሪ: ከፋፋይ: ጨቋኝና ዘረኛ ስርአት በማውገዝ ለውጥ መምጣት አለበት ብለው የሚከራከሩና የሚታገሉ አስር የማይሞሉ ትግሬወችን ስም በመጥቀስ ትግሬን ከወያኔ ጋር ደርቦ መወንጀሉ የእኒህን የጸረ ወያኔ ትግል አራማጅ የሆኑ ትግሬወች ትግል ብላሽ የሚያስቀር ብቻ ሳይሆን በተስፋ መቁረጥ ወደወያኔ እንዲጠቃለሉ የሚገፋ ስለሚሆን የተቃውሞውን ጎራ ይጎዳል የሚሉ የዋሆች ናቸው:: (more…)

በኢትዮጵያ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነውን? (ክፍል አንድ፣ በይገረም አለሙ)

በይገረም አለሙ

ህገ መንግስታዊውን ሥርዓት በሀይል ለማፈረስ የሚል ክስ  በሀገራችን ተራና የተለመደ ነገር ከሆነ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ በስፋት የታወቀው፣ ምን አልባትም የተጀመረው  በቅንጅቶች  ክስ ይመስለኛል፡፡ ለሥልጣን ያሰጋሉ ተብሎ የተገመቱ ዜጎችን በዚህ እየወነጀሉ በመገናኛ ብዙሀን መናገሩንም የጀመሩት አቶ መለስ  ናቸው፡፡ ለነገሩ ከደደቢት እስከ ምንይልክ ቤተ መንግስት የተሰራ የተነገረው ሁሉ የአቶ መለስና  የአቶ መለስ ብቻ አንደሆነ ተነግሮን የለ፡፡ እናም የእኛ የሆነ የምንለውም የምንሰራውም የለንም ሁሉም በአቶ መለስ ተወጥኗል ተነግሯል የእኛ ስራ የሚሆነው  የርሳቸውን ማስቀጠል ነው በማለት አሳፋሪውን ነገር በኩራት የነገሩን ሰዎችም ህገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፍረስ የሚለውን ውንጀላ ቀጥለውበታል፡፡ (more…)

የሕዝብን አመጽ የሚያሸንፍ ኃይል የለም! (ይፍሩ ኃይሉ)

በይፍሩ ኃይሉ

በቅርቡ ”ጎንደር፤ እሳቱን በሣት ያጠፋ ጀግና ነው “ በሚል አረዕስት ባቀረብኩት ሐተታ ውስጥ የወልቃይት ጠገዴን የማነት ጥያቄ ተመርኩዤ ነበር። በዚያ ላይ የጎንደር ቁጣና ያስከተለው፤ ከአትናፍ እስከ አጥናፍ የተቀጣጥጠለ የሕዝብ በውልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ ብቻ የተወሰነ ሣይሆን፤የመላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የልብ ትረታንና ብሶት የነካ በዉድም ሆነ በግድ ወያኔ ከሥልጣን መውረድ አለበት የሚል ነው ። ከእንግዲህ የወያኔን የግፍ ቀንበር የምንሸከምበት ጫንካችን ትልጧልና ከትከሻችን በፍጥነት ይዉርድልን” እያለ ነው የሚጮኸው። ይህ ገና የመጀመሪያው “በቅቶኛልና የአዳምጠኝ” ጩኸት እንጂ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ የደገሰለትን ያወቀው አይመስለኝም። እንደለመደው ያችኑ ያችን የከፋፍለህ ግዛ ዘዴውን እንዳይጠቀም ጎንደር ከኦሮሞው ከመራቁም በላቅይ ‘ የኦሮሞ ሕዝብ ስቃይ የኔም ስቃይ ነው፤ የኦሮሞ ደም ሲፈስ የኔ ደም እንደፈሰሰ እቆጥረዋለሁ “ እያለ ሰንደቁን አንግቦ ሲጮሕበት ወያኔ ወዴት ይሩጥ? ግን ያንኑ የፈረደበትን የትግራይን ሕዝብ ከማወናበድ አልጠቆጠበም። ጥቂት የአማራ ሆዳሞችና ለላንቲካ የተቀመጠው ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ፤”ወልቃይት የትግራይ አካል ለመሆኗ ታሪክ ይመስክራል..” እያሉ ማንዛረጥ ጀመሩ።የጎንደር ሕዝብና የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን ከት ብለው ሳቁ አሁንም እየተንከተከቱ ነው። የወያኔ የቅርብ ወገኖቹና የቀድሞ ታጋዮቹ፤”የደም ዋጋህ ነው” እየተባለ፤ከድሃ እየተነጠቀ ዛሬ ባለቪላ፤ ባለብዙ መኪና፤ባለ ብዙ ኃብት፤አብሮ ከወያኔ ጋራ ወልቃይት ጥገዴም ላይ ሆነ በሥላን ሙጥኝ ማለት ለኔ ይገባኛል ቢል አይፈረደበትም። ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ለግሩ ጫማ ያልነበረው፤ዛሬ የግሩ ጫማ ከጣሊያንና ከስፔይን፤ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ የመጣ ነው። የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት የወያኔ ተጋድይ፤ቁርሱን በልቶ ለምሳውና ለራት፤”ከየት ይመጣ ይሆን?” እያለ ሲጨነቅ የኖረ፤ዛሬ እምብርቱ እስኪገለበጥ በዚግኒና በጢብሲ፤በዶሮወጥና በምንቸት አብሽ ይቀበተታል። ጮማ እንደጎመን የቆርጣል።የኢትዮጵያ ድሃ በጠኔ ሲሰቃይ፤ ወያኔ በቁንጣን ሲፈራገጥ ያድራል። እንኳን ቀምሶት ሰምቶት ያማያውቀውን ዊስኪና ብራንዲ፤ሻምፔኝና ዉድ የወይን ጠጅ ይጎንጫል።ጢንቢራው እስክዞር ድርስ ሰክሮ፤ በየቡና ቤቱ ሽንቱን በሱሪው ላይ ያንዠቀዠቀ፤ ከኪሱ ሽጉጡን አውጥቶ በሰው መያል ጥይት ይተኩሳል። ጸጥታ አስከባሪው ጸጥታውን ያደፈርሳል። የዚህ ዓይነት ባለጌ ከዚህ  ከተንጠለጠለበት ኮርቻ በፈቃዱ ይወርዳል ማለት ዘበት ነው። “ዋይ!ከዚህ ወርጄ እንደገና አጸበለስ ለቀማ የምሄደው?” ነው የሚለው። ይህ የሚወገደው በግድ ገባር ግንብሩን እያሉ በማጋደም ብቻ ነው። ሚያሳዝነው፤ከማራው፤ ከኦሮሞውና ከሌላውም ብሔረሶቦች ተውጣተው፤ከወያኔ ጋራ ለግል ጥቅም ሲሉ ብቻ፤ወገኖቻቸውን ሲገድሉና ሲያስገድሉ፤ከወያኔ ጋራ አብረው ሲዘርፉ የኖሩ ባንዳዎች ዛሬ መሬ ተከፍታ ብትዉጣቸው ይሻላል። ቀኑ የመሸው ለወያኔ ብቻ አይደለም ለሱም ጭምር ነው። ዛሬ እነሱና ወያኔ የታሰፈሩበት መርከብ ይዙዝቸው ሊሰምጥ ከዉቂያኖስ ላይ እየዋለለ ነው።Revolt in Ethiopia (more…)

%d bloggers like this: